Get Mystery Box with random crypto!

 #Update '...ታጋችዋን ታዳጊ ለማስለቀቅ ከከተማ እስከ ክልል የተቀናጀ የክትትልና ምርመራ | TIKVAH-ETHIOPIA

 #Update

"...ታጋችዋን ታዳጊ ለማስለቀቅ ከከተማ እስከ ክልል የተቀናጀ የክትትልና ምርመራ ስራ እየሰራን ነው። በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችም አሉ " - የዓድዋ ከተማ ፓሊስ

የዓድዋ ከተማ ፓሊስ በታጋቿ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማብራሪያ ሰጥቷል።

መጋቢት 10/2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ ልዩ ቦታ ዓዲ ማሕለኻ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ የተሰወረችው ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ከታገተች 24 ቀናት ተቆጥሯል።

የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ ተስፋይ  ኣማረ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም በስልክ በሰጡት መረጃ ፥ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባትን የተማሪ ማህሌት ተኽላይ አጋቾችን በቁጥጥር ስር ለመዋል ፓሊስ ጥረት እንያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

የታዳጊዋ መታገት በማስመልከት በተሰቦችዋ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ሪፓርት ካደረጉበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ፓሊስ ጉዳዩ ለደቂቃ ያህል ችላ እንዳላለው የገለፁት የፓሊስ ዋና አዛዡ ፥ " ' ፓሊስ ለእገታው ትኩረት አልሰጠውም ' ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆችና በሚድያዎች የሚሰራጨው መረጃ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ይህን ያህል ከባድ የውንብድና ወንጀል ተፈፅሞ ፓሊስ እንዴት ችላ ይለዋል ? " ሲሉ የጠየቁት ዋና አዛዡ ተስፋይ አማረ ፥ ከከተማው እስከ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በመቀናጀት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ለመያዝ ሌት ተቀን እየተሰራ ነው ብለዋል።

" ታዳጊዋን ያገቱ ሰዎች ከእገታው በፊት ለረጅም ጊዜ ሲከታተሉዋት የቆዩ መሆናቸው ከቤተሰቦችዋ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል " ያሉት ዋና አዛዡ ፥ " የተወሰኑት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል። ለሚድያ መግለጫ ስላልሰጠን ብቻ ስራችን እየሰራን እንዳልሆነ ተደርጎ መውሰድ አግባብነት የለውም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በታዳጊዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ በተደጋጋሚ መረጃ ያደረሰ ሲሆን ከቀናት በፊት ቤተሰቦቿ በሰጡት ቃል ፥ አጋቾች ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው በጠየቁበት ዕለት ድምጿን ከሰሙ በኃላ ዳግም እንዳላገኟት እነሱም እንዳልደወሉ ፣በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች እንኳን እንደማያውቁ ፤ በዚህም መላው ቤተሰብ በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረው ነበር።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia