የኤርትራ መንግሥት 46 እስረኞችን ለቀቀ። በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ #ኤርትራ ተወስደው በኤርትራ መንግሥት ታስረው ከነበሩ የትግራይ ተወላጆች ውስጥ 46ቱ በዛሬው ዕለት ተለቀው ሽራሮ ከተማ ገብተዋል። የሽራሮ ከንቲባ አቶ ሙሉ ብርሃነ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድርገጽ በሰጡት ቃል ፥ እስረኞቹ በኤርትራ የጋሽ ባርካ ዞን መቀመጫ በሆነችው የባረንቱ ከተማ ታስረው የቆዩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ዛሬ ጠዋት በ”አይሱዙ” ተሽከርካሪ ተጭነው ሽራሮ እንደገቡ ተናግረዋል። በእስር ላይ የቆዩት የትግራይ ተወላጆች “ ምህረት ተደርጎላቸው ” የተለቀቁ ሲሆን ይህም በኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት እና በኤርትራ ሰራዊት መካከል ሲካሄድ በቆየ ንግግር መሆኑን ከንቲባው ገልጸዋል። እስረኞቹ ተለቅቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው፤ በጦርነቱ ጊዜ “ ከባድ የሆነ ወንጀል ያልፈጸሙ ናቸው ” በሚል ምክንያት ነው። በኤርትራ እስር ላይ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች መካከል አሁንም ያልተፈቱ አሉ። የዛሬው እርምጃ የቀሩትም እንደሚለቀቁ “ ተስፋ ሰጪ ነው ” ሲሉ የሽራሮ ከተማ ከንቲባ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። @tikvahethiopia 231.8K views18:20