Get Mystery Box with random crypto!

#ፊቼጨምባላላ የፊቼ ጨምበላላ በዓል እየተከበረ ይገኛል። የበዓሉ ዋነኛ መለያው ሰላም ፤ አንድ | TIKVAH-ETHIOPIA

#ፊቼጨምባላላ

የፊቼ ጨምበላላ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉ ዋነኛ መለያው ሰላም ፤ አንድነትና ፍቅር ሲሆን በዚህ በዓል ተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ ፤ ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል። ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም ፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይም እንዲሰማሩ ይደረጋል።

በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል። እንደ ሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia