Get Mystery Box with random crypto!

' አደጋዉ እጅግ አሰቃቂ ነበር ' - ኢኒስፔክተር  ተስፋዬ ደምሴ በቅርቡ በመኪና አደጋ በርካታ | TIKVAH-ETHIOPIA

" አደጋዉ እጅግ አሰቃቂ ነበር " - ኢኒስፔክተር  ተስፋዬ ደምሴ

በቅርቡ በመኪና አደጋ በርካታ ልጆቿን አጥታ ገና ሀዘኗ ያልወጣላት ሀዋሳ ዛሬም ሌላ ሀዘን አስተናግዳለች።

በዛሬዉ እለት ከሰዓት መነሻዉን ከሀዋሳ ያደረገ " ዶልፊን " የሚሰኘው ተሽከርካሪ ከቅጥቅጥ አዉቶብስ ጋር " ሀዊላ ወረዳ ቱላ አዋሳኝ " ሲደርስ በመጋጨቱ በህይወት እና በንብረት ላይ አደጋ ደርሷል።

የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶችም ቀላልና ከባድ አደጋ አስተናግደዋል።

አሁን ላይ ተጎጅዎች በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘዉ ሪፈራል ሆስፒታል እርዳታ እያገኙ ይገኛሉ።

የሟች ቁጥርን በተመለከተ ለጊዜው የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አልተቻለንም።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አደጋው በተመለከተ ባወጣው መረጃ መጀመሪያ 15 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ቢገልጽም በኃላ ላይ ቁጥሩ 4 ብሎ ቀይሮታል (እስካሁን ያለውን)።

በአደጋው ዙሪያ ያነጋገርናቸው የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ " አደጋዉ እጅግ አሰቃቂ ነበር " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ለጊዜው የሟቾችን ትክክለኛ ቁጥር በተመለከተ መረጃ ለመስጠት አልወደዱም።

አደጋዉ ሀዋሳ አዋሳኝ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ፤ አሁን ላይ በሚታወቀው በርካታ ተሳፋሪዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

ዝርዝር ማብራሪያዉን የሚመለከታቸዉ አካላት ለማህበረሰቡ እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia