Get Mystery Box with random crypto!

#Update የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ተጠናቆ ለበዓል አከባበር ሥርዓ | TIKH-VAH ethiopa

#Update

የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ተጠናቆ ለበዓል አከባበር ሥርዓቱ ዝግጁ ሆነ።

ከአንድ ወር በፊት የግንባታ ሥራው የተጀመረው የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ መጠናቀቁና ለጥምቀት በዓል ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል የባህረ ጥምቀቱን ገንዳ በአዲስና ዘመናዊ መንገድ የመገንባት ፣ የኤሌክትሪክና የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራዎች እንዲሁም ቅጽረ ጊቢውን የማስዋብና ቡራኬ ማከናወኛ ስፍራዎችን የማስጌጥ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጸበል መርጫ መስመሮች የተገጠሙ ሲሆን ብቃት ያላቸው የውኃ መሳቢያ ሞተሮች ገጠማም ተከናውኖ ዝግጁ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራም ተከናውኗል።

በአጠቃላይ የዘንድሮን የጥምቀት በዓልን በጥሩ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሉ የግንባታሥራዎች፣ የታቦታት ማረፊይያ ቦታዎች፣ የክብር እኝግዶች የሚስተናገዱባቸው ስቴጆችና የድምጽ ማጉያ መስመር ዝርጋታዎች ተከናውኗል።

ቀሪ የግንባታ ሥራዎችና ይዞታውን የማስከበር ተግባራትም በዓሉ ከተከበረ በኋላ ተጠናክረው መቀጠል ይችሉ ዘንድ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

ቪድዮ : 25 MB (Wi-Fi ተጠቀሙ)

@tikvahethiopia