Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETH

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikfahethiopia — TIKVAH-ETH T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikfahethiopia — TIKVAH-ETH
የሰርጥ አድራሻ: @tikfahethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.20K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ ዜና በ tikvah ከማንም በፊት ያገኛሉ።
#share በማድረግ ይተባበሩን
Contact @Beki_Boy
Buy ads: https://telega.io/c/tikfahethiopia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-08-25 07:58:43
ሰበር

በመቐለ በሚገኘው የአለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ውስጥ የነበረ 570ሺ ሊትር ነዳጅ መዘረፉ ተሰማ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ፤ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ ዛሬ ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ጥዋት በትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) መጋዘን መዘረፉን ገልፀዋል።

ዱጃሪች ፤ " ዛሬ ጥዋት የትግራይ ኃይሎች መቐለ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል በመግባት 12 የነዳጅ ታንከር 570,000 ሊትር ነዳጅ ውስደዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

በቦታው የነበረው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቡድን ዘረፋውን ለመከላከል ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት ተናግረዋል።የተዘረፈው ነዳጅ ለሰብዓዊ ድጋፍ ፣ ምግብ፣ ማዳበሪያና ሌሎች አስቸኳይ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚውል ነበር ያሉት ዱጃሪች " ነዳጁ በመዘረፉ በመላው ሰሜን ኢትዮጵያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ለመድረስ የሚሰራው የሰብዓዊው ድጋፍ ስራ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል" ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰብዓዊ ስራ ሊውል የነበረው ነዳጅ ላይ የተፈፀመውን ዝርፊ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

@tikfahethiopia
1.0K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:23:38 የግንባር ውሎ

የጠላት ኃይል በራያ አላማጣ ወረዳ ሰሌን ውሃ ቀበሌ፣በአማራ ክልል በራያ ቆቦ ወረዳ ዞብል አዋሳኝ በራማ ኪዳነ ምህረት እና በአፋር ክልል ያሎ ወረዳ በዱባል እንዲሁም ቦዲቲ በሚባሉ ቦታዎች ቆርጦ ለመግባት የነበረውን ታጣቂ ምኞች ከንቱ የሚያስቀር ምት ገጥሞታል።

ዞብል የሚገኘው የወገን ኃይል በከባድ መሳሪያ ጭምር ጠላትን አንገት የሚያስደፋ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛል።

በአላማጣ የሚገኙ የቡድኑ አመራሮች በመንግስት አካላት ክትትል ውስጥ መግባታቸውን፤ ምናልባት በጥቂት ደቂቃዎች በላይነሽ አመዴ ብስራት ይዛ ብቅ ልትል ትችላለች የሚል ወሬ ተሰምቷል።

ድል ለሀገራችን

@tikfahethiopia
960 views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:08:10 መረጃ

ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ
ሕወሃት ጦርነቱን ገና ከመጀመሩ  ጠጋግኖ ያሰለፋቸው ታንኮችና መድፎች እየተበላሹ ከጥቅም ውጭ እየሆኑ ሲሆን፡በዛሬው የውጊያ ውሎ በርካታ ታጣቂዎቹን አስጨርሶ በርካቶችንም ተማርከዋል። ገና ካሁኑም የተተኳሽ እና የነዳጅ እጥረት እንዳጋጠመው የታወቀ ሲሆን በዚህ ምክንያትም በርካታ ታጣቂዎቹ ለመከላከያ ሰራዊት እጅ እየሰጡ ይገኛሉ፡

በሌላ በኩል

ህውሃት ከመከላከያ በትር ለማምለጥ ሲል ሠራዊቱ ወደ ኋላ ሲሸሽ እንዳይዳከተለው የዋጃ ድልድይን ሰብሮ መንገድ ዘግቶ እንደሚገኝ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ሲጀመር መከላከያው ካልታዘዘ ወደ አለማጣ አይገባ? ከግራ ቀኝ ሲዘንብበት ድልድይ መፍትሄ መች ይሆናል።

መፍትሄው ሠላም ብቻ ነው።ራሱ ሞቶ ሀገሩ ለማፅናት ቆርጦ ከተሰለፈ ሠራዊት ጋር መላተም አይገባም ነበር።ለማንኛውም መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ፊት ከተባለ የድልድይ መሰበር አያስቀረውም።
(ዋሱ)

@tikfahethiopia
928 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:04:32
ሰበር መረጃ!!
ለህወሃት የጦር መሳሪያ ጭኖ የኢትዮጵያ የአየር ክልል ጥሶ የገባ አውሮፕላን መምታቱን አየር ኃይሉ አስታወቀ

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል::

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ትናንት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል። በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

@tikfahethiopia
863 views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:19:16
ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተላለፈ ጥሪ!

የትግራይ ወራሪ ሃይል በራያ ግንባር ጦርነት ከፍቷል። በራያ ግንባር በምዕራብ በኩል በጀመዶ መሃጎ እና ወደ ጊዳን መስመር ከፍተኛ ዉጊያ ከፍተዋል። በራያ ግንባር በምስራቅ በኩል ወደ አፋር ድንበር አካባቢ ቦተሊ እንዲሁ ጦርነት ከፍቷል።

ስለሆነም ሁሉም ህዝባችን ከጥምር ሃይሉ (መከላከያ ልዩ ሃይል ፋኖ እና ሚሊሻ) ጎን በመሆን በትጥቅና ስንቅ ጭምር ደጀን እንዲሆንና ትግሉን እንዲቀላቀል ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

@tikfahethiopia
888 views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:24:31
ህወሓት ወታደራዊ ጥቃት ተከፍቶብኛል አለ!

በትግራይ ደቡባዊ አቅጣጫ ወታደራዊ ጥቃት ተከፍቶብኛል ሲል የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳ በትዊተር ገለፀ።ጌታቸው ረዳ ባሰፈረው ፅሁፍ እንደገለፀው “ለአንድ ሳምንት በቆየው ወታደራዊ ትንኮሳ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻዎች እንዲሁም ከወሎ የተሰባሰቡ የፋኖ አባላት ተሳትፈውበታል፤ አሁንም የፌደራል ሰራዊቱን ያሳተፈ መደበኛ ያልሆነ ከባድ ጥቃት ተከፍቶብናል” ብሏል።

የህወሓት ሰራዊት የመከላከል እርምጃ መውሰድ ጀምሯል ጌታቸው ረዳ አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት ህወሓት በተሰጠው መግለጫ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በደደቢት ግንባር በኩል ጥቃት ቢከፈትብኝም ምንም የመልስ እርምጃ አልወሰድኩም ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።በፌደራል መንግስቱ በአሸባሪነት የተፈረጀው ቡድን ባለፈው ሳምንት ተከፍቶብኛል ያለውን ጥቃት መንግስት ሀስተኛ መረጃ ነው ማለቱም ይታወሳል።ዛሬ በደቡባዊ ትግራይ ክፍል ተከፍቷል ስለተባለው ጥቃት ይህ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ከፌደራል መንግስት የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም።

@tikfahethiopia
906 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 10:31:57
በግብጽ ሜኑፊያ ግዛት ነዋሪ የሆነዉ የ21 ዓመት ወጣት ፍቅረኛዉ የነበረባትን የትምህርት ፈተና ማለፍ ባለመቻሏ ትምህርት ቤቱን በእሳት አጋይቷል፡፡የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደገለጸው በእሳት አደጋዉ የሞተ ሆነ የተጎዳ ሰው የለም ብሏል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን እጮኛው የትምህርት ቤቱን ፈተና መዉደቋ ክፍል እንድትደግም የሚያስገድዳት ሲሆን ይህ ደግሞ የሰርጋችንን ቀን ይገፋብናል ሲል ተናግሯል። ድርጊቱን ከፈጸመ በኃላ ከአካባቢዉ ተሰዉሮ የነበረ ሲሆን የዓይን እማኞች ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፍ ዴሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡

@tikfahethiopia
885 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:13:04
#ቦረና

በኦሮሚያ ፣ ቦረና በድርቅ ሳቢያ በርካታ ወገኖቻችን ዛሬም ችግር ላይ ናቸው። እነዚህ ወገኖች በድርቁ ምክንያት ያላቸውን ከብቶች ስላጡ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚኖሩት።

በድርቅ ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ያሉ ወገኖች ሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ሰጥተው የነበረ ሲሆን ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው።

(በድብሉቅ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች)

የ7 ልጆች እናት ወ/ሮ ጂሎ ጉራቻ ፦

" የዘንድሮው ድርቅ የነበሩንን ከብቶች እና ሁሉንም ንብረቶችን ነው ያወደመብን። ባዶ እጃችንን ስንሆን ወደዚህ መጣን ፤ እዚህ ከመጣን በኃላ በምግብ እና ውሃ እጥረት እየተቸገርን ነው። በተለይም ህፃናት ነፍሰጡር ሴቶች፣ አዛውንቶች በምግብ እጥረት እየተጎዱ ናቸው። እኛ እዚህ ከሰፈርን ከ6 ወር በላይ ሆኖናል። በመጠለያው በጣም ብዙ ቤተሰቦች ነው ያሉት። በቆይታችን አንዴ ብቻ ነው ለተወሰኑ ቤተሰቦች የምግብ ድጋፍ የተሰጠው እንጂ ምንም አላገኘንም። ስለዚህ በጣም ችግር ላይ ውስጥ ነው ያለነው። "

የ6 ልጆች አባት ዳለቻ ዲዳ ፦

" ምንጠጣው ውሃ በጣም የቆሸሸ ነው። እንስሳት ሲሞቱ ከሚጣሉበት ነው ልጆቻችን የሚቀዱልን። በዛ ላይ የመፀዳጃ ቦታም የለንም። እንዲሁ በበሩ ደጃፍ ነው ይህ ሁሉ በዚህ የሰፈረው ህዝብ የሚፀዳዳው ስለዚህ የበሽታ ወረርሽኝ ፍራቻ አለብን። ሌላው የመጠለያ ቦታና ላስቲክ ሰጥተውናል። ይህ ላስቲክ #ብርድ የሚከላከል አይደለም። እናም በጣም ችግር ውስጥ ነን። "

የልጆች እናቷ ትዬ አደንጌ ፦

" #ብርዱ_በጣም_አስቸጋሪ_ነው። ለምግብ ፍለጋ ነው ከእሳት አጠገብ የምንነሳው። በዛ ላይ የምንለብሰው ልብስ የለንም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Borana-08-23 #ገልሞ_ዳዊት

@tikfahethiopia
951 views11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ