Get Mystery Box with random crypto!

ጥበብን በማሾ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tibebnbemasho — ጥበብን በማሾ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tibebnbemasho — ጥበብን በማሾ
የሰርጥ አድራሻ: @tibebnbemasho
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.90K
የሰርጥ መግለጫ

________________________________
________________________________
ሰላም ቶላዋቅ ኢተፋ ነኝ
እንኳን ወደ ቻናሌ በሠላም መጣችሁ።
በቻናሌ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ሃሳብ ለመስጠትና ግጥም ለመላክ @Tibebn_bemasho_bot ይጠቀሙ።
________________________________
________________________________

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-27 11:32:13 #አምኜሽ_ነበረ

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ

#አንባቢ ሮቤል አለማየው
#ዝምተኛው_ሲርሎስ
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
3.1K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 21:15:21
#አምኜሽ_ነበረ

የሰናፍጭ ታህል መጠርጠር ተስኖኝ
አምኜሽ ነበረ የማትከጂኝ መስሎኝ።

አንቺ ግን ከዳሺኝ
እንዳንቺ ያለን ሰው
መቼም እንዳላምን እምነት አሳጣሺኝ።

#ታዲያ.........
ሰውን ማመን ቀብሮ ያለችው ቀበሮ
እውነቷን ነበረ ገብቶኛል ዘንድሮ።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም #ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
3.3K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 20:18:28
#ጥለሽኝ_ስትሄጂ
ብርሃናማው ቀኔን አልብሰሽ ጨለማ
ግዙፍ ያልኩት ተስፋ ቀለጠ እንደ ሻማ

ዛሬን ኑሮ ነገን ማለም
ሄደ ጠፋ ከኔ አለም

ቀኔም መሸ ቀን ሳይበቃ
ሳትደበቅ ጀምበር ጠልቃ።

አዎ ስትሄጂ ስለት ተቀየረ
ነገ ሚባል ነገም ነገ ሁኖ ቀረ

ታዲያ እንዲህ ሁኖ ጊዜ ሲተካካ
ቀበርኩኝ ትናንቴን አሁኔ እንዲፈካ።

አዎ በትናት ትዝታ ዛሬን ለምን ላፍርስ
ትናት ትናት አልፏል በቃ ዛሬን ላድስ

#አዎ_እንዲህ_ሳስብ
ተስፋ ቢሱ ልቤ ተስፋን አዳመነ
ማግኘትን አምጦ ሲቃን አመከነ

ተስፋ ከሌለበት ካንቺ አለም መነነ
ከማጣቱም በላይ ማግኘቱ መዘነ።

አዎ .....
በልቤ ሠሌዳ ተስፋ ተፃፈበት
ሁሁታው ተሽሮ ሠላም ሰፈነበት።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2013 ዓ.ም ገቺ

ይቀላቀሉን
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
3.3K viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 21:39:02 #ይዲዲያ

በዛች ቅዱስ እለት
አንቺን ስመለከት ከመፅዋች መሃል
ቀልቤ ከነፈልሽ በውበትሽ ፀዳል።

ታዲያ
እጅግ ብደነቅም በፈጣሪ ስራ
አይቼ ስወድሽ ከቅዱሱ ስፍራ
አንድም ሐሴት አለው በሌላም መከራ።

መከራው ፍቅርሽ ነው
እንደ አውሎ ነፋስ እምያወዛውዘኝ
ካለሽበት ቀዬ ወስዶ የሚጥለኝ
እንደ እናቴ ኩርፊያ የሚያነጫንጨኝ።

ታዲያ
በውበትሽ ቅኔ መላቅጤን ሳጣ
በዐይኖሽ ስከረር ደስታ ከየት መጣ?

ብቻ
በኑረት ብራና ልቤ አንቺን ይደርሳል
ባለሽበት ትዕይንት እራሱን ይስላል።

ታዲያ
እንዲህ ሁኖ ሳለ ፍቅሬ እንዴት ተሸሸ
የማፍቀረስ ፀዳል ስለምን ጠለሸ?

ብቻ
እውነት ኑሯት ይሆን እያልኩ አስባለው
ይሄን ተከትሎም
ፍቅር ያስፈራኛል
የሚል ዐይነት ምላሽ ከገፇ አያለው።

ደሞ አንዳንደዚህ
ከፍቅር የሚያርቅ ምን እውነት ይኖራል
ከፍቅር እርቆስ እውነት የት እገኛል?

እያልኩ አስባለው
እውነት በማይመስሉ እውነቶች ታጥረ
እየተገረምኩኝ አንቺን በማፍቀረ።

ብቻ
በይ እስኪ ንገርኝ እጠይቅሻለው
ፍቅሬ ይዲዲያ መች አገኝሻለው?

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
2.7K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-12 21:05:37
#ጦቢያ

ሰማይ ላይታረስ ነፋስ ላይታፈስ
እንዳው ለነገሩ ነገር ብጠነሰስ
ትፈርሳለች በሚል ....
በፈረሰ ሃሳብ እምነትህ አይፍረስ።

#ምክኒያቱም.
እንዳው ዝም ብላ ተነስታ የምትፈርስ
አይደለች ሀገሬ በማንም ልክስክስ።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም ገቺ

@tibebnBemasho
@tibebnBemasho
2.9K viewsedited  18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-03 21:06:42 #ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
#አንባቢ ዝምተኛው ሲርሎስ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
2.7K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-16 19:57:32 #እምነትና_እውነት

ገጣሚና አንባቢ ቶላዋቅ ኢተፋ

#ይቀላቀሉን
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
3.4K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 20:57:30 #አንዳንዴ

#ገጣሚ ቶሎዋቅ ኢተፋ
#አንባቢ #ዝምተኛው_ሲርሎስ


@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
3.7K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-04 21:00:02 #እኔ_አንቺን_ስጠብቅ

እኔ አንቺን ስጠብቅ
እልፍ ክረምት አልፎ ዘመን ተሰደደ
አንዱ ጓደኛዬ አግብቶ ወለደ

የሰው ልጅ ከሰይጣን ክፋትን ወረሰ
በሀገሬ ምድር ብዙ ደም ፈሰሰ።

እኔ አንቺን ስጠብቅ
ሰማይ ጠቀስ ህንፃ በሀገሬ ተሰርቶ
በየቦታው ቆሟል ባለቤቱ ጠፍቶ።

እኔ አንቺን ስጠብቅ
ለማመን ቢከብዱም ብዙ ነገር ሆኗል
የ ሀገሬ መሪ ሶስቴ ተቀይሯል
አሸናፊው ታውቆ ምርጫ ተካሂዷል

እኔ አንቺን ስጠብቅ
በስተምስራቅ በኩል ፀሀይ ስንቴ ወጣች
ስደተኛ እህቴ ይሄው ከብራ መጣች።

እኔ አንቺን ስጠብቅ
የስንቱ ደሃ ቤት ሊፈርስ ታቅዷል
ሀገር ለማሳመር ሀገር ተበላሽቷል

እኔ አንቺን ስጠብቅ ኑሮም ተወደደ
እሱን ተከትሎ ብዙ ሰው አበደ።

#ብቻ .......
ያልቀር ቃልሽን አምኖ ትመጭያለሽ ብሎ
ለሚኖረው ልቤ ናፍቆትሽን ስሎ

ቀን አይጨልምበት ሌሊት አይነጋበት
አንቺን ይጠብቃል ያላንዳች መታከት።

#ግና_መቼ_ትመጭያለሽ?

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
#ገቺ 2014 ዓ.ም

ሃሳብ ለመስጠት @Toteda

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
5.4K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 20:55:59 #አንዳንዴ ......
የሕይወት ውጥንቅጥ ባንተ ላይ ሲደፋ
እርምጃህ ተገቶ ስትቆም ያለ ተስፋ

እንኳን መኖር ቀርቶ ስቆ በፈገግታ
መስማት ያዳግታል ዝም ያለን ዝምታ።

#አይዞን

በቶላዋቅ ኢተፋ @Toteda
2014 ዓ.ም ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho
5.0K viewsedited  17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ