Get Mystery Box with random crypto!

#ይዲዲያ በዛች ቅዱስ እለት አንቺን ስመለከት ከመፅዋች መሃል ቀልቤ ከነፈልሽ በውበትሽ ፀዳል። | ጥበብን በማሾ

#ይዲዲያ

በዛች ቅዱስ እለት
አንቺን ስመለከት ከመፅዋች መሃል
ቀልቤ ከነፈልሽ በውበትሽ ፀዳል።

ታዲያ
እጅግ ብደነቅም በፈጣሪ ስራ
አይቼ ስወድሽ ከቅዱሱ ስፍራ
አንድም ሐሴት አለው በሌላም መከራ።

መከራው ፍቅርሽ ነው
እንደ አውሎ ነፋስ እምያወዛውዘኝ
ካለሽበት ቀዬ ወስዶ የሚጥለኝ
እንደ እናቴ ኩርፊያ የሚያነጫንጨኝ።

ታዲያ
በውበትሽ ቅኔ መላቅጤን ሳጣ
በዐይኖሽ ስከረር ደስታ ከየት መጣ?

ብቻ
በኑረት ብራና ልቤ አንቺን ይደርሳል
ባለሽበት ትዕይንት እራሱን ይስላል።

ታዲያ
እንዲህ ሁኖ ሳለ ፍቅሬ እንዴት ተሸሸ
የማፍቀረስ ፀዳል ስለምን ጠለሸ?

ብቻ
እውነት ኑሯት ይሆን እያልኩ አስባለው
ይሄን ተከትሎም
ፍቅር ያስፈራኛል
የሚል ዐይነት ምላሽ ከገፇ አያለው።

ደሞ አንዳንደዚህ
ከፍቅር የሚያርቅ ምን እውነት ይኖራል
ከፍቅር እርቆስ እውነት የት እገኛል?

እያልኩ አስባለው
እውነት በማይመስሉ እውነቶች ታጥረ
እየተገረምኩኝ አንቺን በማፍቀረ።

ብቻ
በይ እስኪ ንገርኝ እጠይቅሻለው
ፍቅሬ ይዲዲያ መች አገኝሻለው?

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho