Get Mystery Box with random crypto!

ሕንዳዊያኑ ወላጆች የልጅ ልጅ አልወለዱልንም ሲሉ ብቸኛ ልጃቸውን እና ባለቤቱን ፍርድ ቤት አቆሙ | Think Abyssinia

ሕንዳዊያኑ ወላጆች የልጅ ልጅ አልወለዱልንም ሲሉ ብቸኛ ልጃቸውን እና ባለቤቱን ፍርድ ቤት አቆሙ

ሳንጄቭ እና ሳድሃና ፕራሳድ እንደሚሉት ልጃቸውን ለማሳደግ የነበራቸው አንጡራ ሃብት አፍስሰውበታል። የበረራ ትምህርቱን እንዲከታተል ከመርዳት ባለፈም ድል ባለ ድግስ እንደዳሩት አስታውቀዋል።

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የልጅ ልጅ ካላገኙ 650 ሺህ ዶላር ካሳ ከልጃቸው እንደሚፈልጉም አስታውቀዋል። ያልተለመደ ነው የተባለው ክስ "ስነ-ልቦናዊ ጉዳት" በማድረስ በሚል የቀረበ ነው።

አባት ፕራሳድ ያላቸውን ጥሪት በሙሉ ልጃቸው የአውሮፕላን አብራሪ እንዲሆን 65 ሺህ ዶላር ወጪ አድርገው አሜሪካ እንደላኩት ተናግረዋል ሲል አል አይን ቢቢሲን ጠቅሶ ዘግቧል ።


• @ThinkAbyssinia •