Get Mystery Box with random crypto!

የጥበብ ብዕሬ

የቴሌግራም ቻናል አርማ thepenofwisdom — የጥበብ ብዕሬ
የቴሌግራም ቻናል አርማ thepenofwisdom — የጥበብ ብዕሬ
የሰርጥ አድራሻ: @thepenofwisdom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 96

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-14 20:18:22
በዓሉ ግርማን እንዲህ ድንቅ አድርጎ የሳለዉ " ገብረ መድኅን "ይባላል ። መድኅን የብዕር ስሙ ነዉ ። መድኅን የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነዉ የምትሉትን 0945628547
89 viewsErmias Debasu, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 20:11:12 " ከመጥፎ ህሊና የባሰ ጅራፍ የለም "ይላል ደራሲው በህዝብ ልብ ዉስጥ የሀቅ ምሰሶዉን ተክሏል
"የእግዜር በግ ነዉ የሚያየዉን ሁሉ ይወዳል ፤ በአለም ላይ ለሚያየው ሁሉ ዉበት ልቡ በቂ ቦታ ስለሌለዉ ይጨነቃል ፤ግን ተራ ሟች ነዉ ,,,,እናም ሁሉን ያጣል "እያለ በምናብ አለምፍጥረቱ በፀጋየ ሐይለማርያም ራሱን ነግሮናል ።

የአሟሟቱ ወይም የመሰወሩ ጉዳይ ምስጢር እንደሆነ ሲኖር አለ

አሁን በስሙ ላስተዋዉቃችሁ
ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ
.
ጊዜዉ ያኔ .!! የካቲት 7ት ቀን 1976 ዓ.ም ነዉ ፤ በስነ ፅሁፍ አለም ዉስጥ ሀቅን በብዕሩ የመሰከረው ደራሲና ጋዜጠኛ በአሉ ግርማ ከቤቱ እንደ ወጣ ሳይመለስ የቀረበት ፤ የመሰወሩ ጉዳይ ምስጢር የሆነበት እለት .......

በዓሉ ግርማ በህይወት በስነ ፅሁፍ ዘመኑ በፃፋቸዉ ልብ ወለድ ስራወች ለስነ ፅሁፍ ቤተሰቦች ትዉስታዉን ትቶ አልፏል ።


"ሀሳብ መጨረሻ የለዉም ቁም ነገሩ መኖር ነዉ የኑሮን ጣዕም ፤ ሀሳብ የፈጠረዉ ግብ ላይ ካልደረሰ ዉጤቱ ያዉ ምሬትና ብስጭት ነዉ "በማለት አበራ ወርቁ በተሰኘ ገፀባህርይ ጭብጡን ከጨዋታ ጋር እያዋዛ የሚያጣጥምልን ስራዉ ዛሬም ድረስ በዓሉ ግርማን ያስታዉሰናል ።



ደራሲዉ ጊዜን እና የጊዜን ወደር የለሽ ዋጋ ጉምቱ በሆኑ መፅሐፍቱ ዉስጥ የጊዜን ወርቅነት ይመሰክራል ደራሲዉ በተሰኘ መፅሐፉ ዉስጥም " የጊዜየሚያመለክተዉ ወደ ፊት ብቻ ነዉ "በማለት ዘመን ተሻጋሪ ስራዉን አስነብቦናል ። "ጊዜና ቀጠሮ መከበር አለባቸዉ ከጊዜና ከቀጠሮ ዉጭ የሚሆን ነገር የለም ወቅትና ዘመናት ጊዜና ቀጠሮ ጠብቀዉ ነዉ የሚፈራረቁት የሚሉት የሀዲስ ልብ ወለዱን ገፀ ሰው ፈታዉራሪ ተካን እንዲህ ይስላቸዋል " .....ፈታዉራሪ በቀጠሮ ቀልድ አያዉቁም ባለፈዉ ጊዜ ለምሳ ቀርበዉ ባብዛኛዉ የጎረሰዉ የቀረበለትን ፍትፍት ሳይሆን ፤ፈታዉራሪ ስለ ጊዜ ያላቸዉን ፍልስፍና ነበር ።


"ራሴን በምፈልገዉ መንገድ ለመግለፅ ሳልችል የህይወትን ጉዳና አቋርጨ እንደምሔድ አንዳንዴ ትዝ ሲለኝ መፈጠሬን እጠላለሁ የታፈነች ነፍሴ ስትቃትት ይሰማኛል "እያሰኘ በከአድማስ ባሻገሩ አበራ ወርቁ የሚተርክልን ስራዉ ለብዙዎቻችን ህልሟን ፍለጋ ለምትቃትት ነፍሳችን ማነቃቂያ ይሆኗል ።


በዓሉ በጨረቃ በፀሐይ በከዋክብት ከአድማስ እሰከ አድማስ በተንጣለለዉ በተፈጥርአዊዮ መልከ ምድር ዉበት ይነሸጣል ። ይፅፋልም ። ዉበትን ከጭብጥ ጋር እያዋዛ የአንባቢን ስሜት ከፍ ዝቅ ሔድ መለስ ማድረግ ተክኖበታል ። ለዚህም "ንጉስ ዳዊትን የፈሰችዉ ሰሜናዊት ፅቡቅቲ "እያለ የዉበቷን ልክ ከፍ አድርጎ ምስሏን በቃል የሚከስትልን የፊያሜታ ጊላይን ምስል የመከሰት አቅሙን ያሳየባቸዉ ናቸው ።



በልብ ወለድ ስራወቹ ዉስጥ የፈጠራቸዉ ገፀ ባህርያት በስነ ፅሁፍ አፍቃሪ ዘንድ አይረሴነት አላቸዉ ፤ ድርሰቶቹን ያነበበ ሁሉ እኒያ የማይረሱት ባለ ቀለመ ደማቅ ምናባዊ ምስለ ሰወች ከነ ጭብጣቸዉ በተደራሲያን የትዉስታ በር ብቅ ይላሉ ።


መቼም ቢሆን " መፃፍ የምፈልገው ስለ አለም ዉበትና ስለ ሰዉ ተፈጥሮ መሰረታዊ ጥሩነት ነዉ እንዲሁም ሰዉ በራሱ ደህንነት እንዳያገኝ ስለሚያደናቅፉት ሁኔታወች እና አካባቢዎች ነዉ " እያሰኘ የሚተርክልን የኦሮማይ ዩን ኃይለ ማርያም ካሳይን "አባቴ ይሙት''''!!! " የምትለዋን ፊያሜታ ጊላይን የከአድማስ ባሻገሩን አበራ ወርቁ የሀዲሷን አይናለም ተካ ን የሚዘነጋ አይኖም ።

በዓሉ ስራወቹ በህዝብ ዘንድ የእዉነት የእሙን አሻራቸዉን አንብረዉ የሚያልፉ የቀኝ ምስክሮች ናቸዉ ሀዲስ በተሰኘው ልብ ወለዱ ራሱ ሀዲስ በሚለዉ ገፀ ባህሪዉም "አየሽ ህዝቡ እምነት ጥሎብኛል ይህንን እምነት አጉድየ ብጠፋ የት እደርሳለሁ ። የትም ብደርስ ከገንዛ ህሊናየ ላመልጥ አልችልም ምን ጊዜም ቢሆን ከህሊናየ ገሐነም አልድንም ከመጥፎ ህሊና የባሰ ጅራፍ የለም "እያለ የአደራን ከባድነት የህሊናን ዳኝነት በብዕሩ ከትቦ በማይረሳ ገፀ ባህሪዉ ሀዲስ ሳህሌ በተሰኘ ገፀባህርይ አስነብቦናል ።

ለዛሬ የበዓሉ ግርማ የተሰወ በትን ወይም የሞተበትን ፤ እንደ ወጣ የቀረበትን እለት በማስመልከት የተጫረ ፅሁፌ ይህን ይመስል ነበር ።

የምትሉኝን በ @Ermiasdebassu በኩል ሹክ በሉኝ

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
88 viewsErmias Debasu, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 21:05:53 እንኳን ለላቀው የኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል ዋዜማ (ከተራ) ደረስን።በያላችሁበት አጥቢያ የበዓሉን አከባበር በድምፅ፣ምስልና ተንቀሳቃሽ ምስል አድርሱን።

ለምትሉት ሁሉ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት
111 viewsErmias Debasu, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 20:58:43 ጀርባ ሲጠና ነዉ



"ሎሚ ብወረወር ደረቷን መታሁት ፣
ወየዉ ኩላሊቷን ልቧን ባገኘሁት ። "
ከሚል የአምና ፀፀት ዘንድሮ ተምሬ ፣
ልብሽን ላገኝ ነዉ በጀርባሽ መዞሬ ።
ከኋላ ነዉ እንጅ ከፊት አይገኝም ፣
ሸሽቶ ለሔደ ልብ
ማንጅራት ነዉ ካልሆነ ግንባር አይታይም ።
ሎሚም ብወረዉር
ደረትሽ ላይ እንጅ አያርፍም ከልብሽ ፣
ጀርባ ጀርብ ሆኗል የፊትና ኋላሽ ።
አምናም ብወረዉር ደረትሽ ላይ አርፏል ፣
ልብሽን ሳያገኝ
ደረቱን የነፋዉ ጡትሽ መልሶታል ፣
ማንነቱን ትቶ ልብሽም ኮብልሏል ፣
በእንሶስላ መዋበብ ፣
በአሪቲ ጠረን እያወዱ መሳብ ፣
በአገር ባህል መድመቅ በማንነት መዋብ ።
ለዘነጋዉ ልብሽ ፣
ሎሚ አልወረዉርም መጥቸ ከፊትሽ ።
ባይሆን ከኋላ ነዉ
ልብሽን እንደገኝ ጀርባሽን 'ማጠናዉ ፣
ልብ የማግኘት ምሱ ከጀርባ መዞር ነዉ ።
ጀርባ ሲጠና ነዉ ሎሚ ከልብ የሚያርፍ ፣
አሁን ስለ በዛ ቁል ይዞ እሚሰለፍ ።
ጀርባ ሲጠና ነዉ ሎሚ ከልብ የሚያርፍ ፣
አሁን ስለ በዛ ቁል ይዞ እሚሰለፍ ።
ጀርባ ሲጠና ነዉ ሎሚ 'ሚወረወር ፣
ከጡት መሀል አርፎ ልብ ላይ እንዲሰፍር ።




በኤርምያስ ደባሱ
101 viewsErmias Debasu, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 09:28:26
በረከት ገብሬ ይባላል የ3ኛ አመት የማህበረሰብ ጥናት (sociology )ተማሪ ነዉ ።
ብዕርና ቀለም አገናኝቶ የፈጠራት ድንቅ ፍጡር ነች የጥበብ አፍቃሪያን እነሆ ተጋበዙለት
210 viewsErmias Debasu, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 21:22:04 እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ



እ"ፀ በለስ በልታ ሔዋን ስትሳሳት ፣
ን"ብላ እፀ ህይወት አዳም ያለች መስሎት ።
ኳ"ሄላ ምትመስል በለስን ቀመሰ ፣
ን"ፅህት ህይወቱን ዳዉጃ አለበሰ ፣
ለ"ገነት ተፈጥሮ ከሲኦል ደረሰ ፣
ብ"ትበላ ትሞታለህ የሚል ህግን ጣሰ ።
ር"ህሩህ ክርስቶስ
እስኪወለድ ድረስ ከቅድስት ድንግል ፣
ነ"በረ ርቆ ከገነት ተወርዉሮ ሲኦል ።
ል"ቅ ቀኑ ደርሶ ሲፈፀምትንቢት የነቢያቱ ፣
ደ"ግሞም ተብሎ ሲዘመር
ሰብዓሰገል ሰገዱ ሎቱ ።
ቱ"ሩፈ ሆነ በሰማይ በምድር መድኅን ሆነ ለኩሉ ፣
በ"በረት ተወለደ ዝቅ ብሎ ከሁሉ ፣
ሰ"ማይና ምድርን አስታረቀ በቃሉ ፣
ላ"ይሻር ላይሸረሸር እሙን ሆነልን ቃሉ ።
ም"ህረት ወረደ ለአዳም ከሲኦል ነፃ ወጣ፣
አ"ለምም ተፈወሰ
የዉርስ ሐጢያት ከሚባል ጣጣ ።
ደ"ልዳላ ሆነ መሬቱ የሐጢያት ክምርፈረሰ ፣
ረ"ገበ መረቡ የሰይጣን ወጥመድ ተበጠሰ ፣
ሳ"ለ የማይቸግረዉ መድኃኒአለም ተወለደ፣
ች"ግር መከራዉን ቀርፎ አዳምን ሊያድን ወደደ
ሁ"ሉ የማይሳነዉ አምላክ ቃል ከስጋ ተዋደ ።
92 viewsErmias Debasu, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 21:21:27 አለሜ .....
እንኳን አደረሰሽ ሳልልሽ የቀረዉ ፣
ለአዉደ አመት መድረስሽን አይደለም ጠልቸዉ ፣
አመት በዓል ጠብቆ
እንኳን አደረሰን ስለማልወድ ነዉ ።
ምንም ..እንኳን እጅግ ቢያስደስተን ሁሉ
ስንት ነገር አልፎ መድረስ ለአመት በዓሉ ።
ከአደረስን መድረስ
ከደረስንበት ቀን ፣
ቢባልም አይከፋ እንኳን አደረሰን ።
88 viewsErmias Debasu, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 12:49:50 ያዉ ቃል ነዉ


ምኑ ገርመሽ ያዉቃል ?
ምኑስ ደንቆሽ ያዉቃል ?
ምኑ በሽቆሽ ያዉቃል ?

ንገሪኝ እስኪ ቃል ....

የገረመሽ ቢሆን
የደነቀሽ ቢሆን
ያዉ ቃል ነዉ መንገርያሽ ከእርሱ የሚዘገን ፣
ያዉ ቃል ነዉ ማምለጫሽ የሚያስረሳ እርምሽን ።

ግን እስኪ አንድ ቃል
ንገሪኝ አስኪ አሁን
አሁን !! አሁን !! አሁን.....!!!!!
ታዝበሽዉ ይሆን ?

የሰማዩን ስፋት
የባህሩን ጥልቀት
አድማሱን አሻግረሽ ጋራ ሸንተረሩን
ኮራ ጀነን ያለ ግዘፍ ተራራዉን
አሁን ....አሁን ...አሁን...!!!
ታዝበሽዉ ይሆን ??
ንገሪኝ አንድ ቃል
ምኑ ገርሞሽ ያዉቃል ??

ቢገርምሽ
ቢደንቅሽ
በሽቆሽ ቢሆን እንኳን
ያዉ..!! ቃል ነዉመንገሪያሽ ከእርሱ የሚዘገን
ያዉ ቃል ነዉ ማደርያሽ የሚያስገባ አንገትሽን
ያዉ ቃል ነዉ መፅንኤሽ የሚያስረሳ እርምሽን


ደግሞም ይመስለኛል ...

የሰማዩን መስፋት
አይተሽዉ ተደንቀሽ ተገርመሽ ይሆናል ፣
እንዴት ያለ ባላ ይህ ፀንቶ ይቆማል ?
ብለሽ በመገረም
ብለሽ በመደነቅ አለያም በመብሸቅ ፣
ጠይቀሽ ይሆናል አማርጠሽ ከሽ ሊቅ ።
ግን ያም ቢሆን ሊቁ
ያዉ ቃል ነዉ መንገርያዉ ምስጢረ ረቂቁ ።

የመሬቷ መፅናት ሆና ከባር ላይ ሆና
ሳያሰጥማ ባህሩስ አሰንዴት በቃል ፀና !?
በምንስ ቃል ፀና ?
ብለሽም ይሆናል ብሸቂብኝ ቢልሽ ፣
ግን ለዚህም የሚሆን
ያዉ ..!! ቃል ነዉ መንገርያሽ ።
ያዉ ቃል ነዉ
ያዉ..!!ቃል ነዉ
ሰማይና ምድርን አፅንቶ ያቆመዉ ።
104 viewsErmias Debasu, 09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-05 11:21:45 ሞት ረከሰብሽ ዉድቀትሽ ነገሰ ፣
ጥሩ ወንዝሽ በደም.. ጎር ደፈረሰ ።
ለሰሚዉ ከበደ ስላንቺ ሚወራዉ ፣
ይህን ዘግናኝ ግብርሽ አይታም ከበደዉ ።
ሰዉ ሆኖ መፈጠር ረክሷል በቤትሽ ፣
ነፍስ መብላት ሆነ የሁል ጊዜ ስራሽ ።
አጥፊወችሽ በዙ ላያድኑሽ ቀርበዉ ፣
ትናንት ላሸፈቱት ዛሬ ንግስን ችረዉ ።
ታሳዝኝኛለሽ አንች የደም ሀገር ፣
ህዝብሽ በከንቱ ህይወቱን ሲገብር ።





በኤርምያስ ደባሱ

t.me/Thepenofwisdom

ሰኔ
4:05 /2013

የተደገመ
136 viewsErmias Debasu, edited  08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-05 10:39:35 የአርማሽ መንታ ስሜት



በኤርምያስ ደባሱ



" እኔማ አለሁ እስከ አሁን ተስፋ ሰንቄ ፣
በወንዜ ባገሬ እያለሁ ሀገር ናፍቄ "

እያለ በሚያዜማት ስንኙ የሀገሬን ሰዉ ባይተዋር ሀገር ናፋቂ ልብ ይነካካል ። ሀገር እያለ ወንድማማችነት እንደ ዘሐ ክር እየቀጠነ መጥቷል ፤ ከብረት የጠነከረዉ ኢትዮጵያዊ አንድነት ዉኃ እንዳራሰዉ ልጥ ተዉሸክሽኳል "በወንዜ ባገሬ እያለሁ ሀገር ናፍቄ "የማይል ኢትዮጵያዊ የለም ። ሀገር ኖሮን ሀገር የለንም ባይተዋር ሆነናል ።


የኢትዮጵያዊነት ኩራት የሆነዉ መተሳሰብ ፣ አብሮነቱ ፣ ስንት የተወራለት እንግዳ ተቀባይ ባህላችን እንደ ማለዳ ጤዛ ተኗል ። በኗል ! አሁን ላይ እንግዳ መቀበሉ ቀርቶብናል እንግዳ ተቀባይ የነበርነዉም ዛሬ ለራሳችን ስደተኛ ሆነናል ።
" እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ ፣
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ ።"
ያች የፍትሕ ና የርዕት ሀገር የተባለላት ኢትዮጵያ መምጫዋን ናፋቂወች ሆነናል ።

ጥበብ ገሀዱ አለም ናት ! ቴወድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ ) ይህንን ገሀድ የወጣ አለማችንን በጥበበኛ ብዕሩ ከትቦ በስል አንደበቱ አዚሞ

" ቀን እየሔደ ቀን መጣ ፣
ልቤ ከሀሳብ ሳይወጣ ።
መጥታ ታብሰዉ እንባየን፣
ሀገሬን ጥሯት አርማዬን ። " እያለ ልብ ድረስ ዘልቆ ይደመጣል ።



በያሬድ ተፈራ የሳክስፎን ረቂቅ ዜማ እያዋዛ ከዉሃ በጠራ ድምፁ
"መቼም ከዚህ ምድር ላይ
ሔዶ ነዉ ሁሉም ቀሪ ፣
አገር ናት ቋሚ ሰንደቅ ለዘላለም ኗሪ ። "ሲል በሚስብ ዜማዉ አቆነጃጅቶ የሁሉንም አላፊ ጠፊነት ምስጢር ይገልፅበታል ።


እኔማማማማ....!!! እያለ በረጅሙ እስትንፋሱን ሳብ አድርጎ ከረጅሙ የሀገር ፍቅር የመነጨዉን ምኞት ያወሳበታል ።
"እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ ፣
ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ ።" ቴዲ አፍሮ እንዳለዉም የናፈቃትን ሀገሩ ሲያስታዉስ በሰቀቀን እንባዉ የማይቀድመዉ የለም ። የሀገር ፍቅሩ በእንባ የሚተናነቀዉ ሰዉ የሚመሰክረዉ ሃቅ መሆኑ ነዉ ።


"ወጥተሽ በምስራቅ አንች የአለም ጀምበር ፣
አንድ አርጊንና ጠላትሽ ይፈር ።"በሚላት ስንኙ የምስራቅ አፍሪካዋ ኢትዮጵያ በድል አድራጊነቷን ጠላት አሳፋሪ መሆኗንም ያወሳልበታል ።


ያሬድ ተፈራ በሚራቀቅበት ሳክስፎን በረከት ተስፋዚንም በሊድ ጊታሩ እየተጠበበ በሚያጅበዉ የቴወድሮስ ካሳሁን አሸወይ ድምፅ
"ሀገር ለክብሩ ሲጣራ
ከፍ ያደረግነዉ ባንዲራ
ዘመም ሳይል ቀን ጎድሎ
ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ "እያለ ኢትዩጵያን ዉዷን ሀገሩ በሰዉኛ ዘይቤ ያናግራታል ። ዉዷ ሀገሩ ግን አልመለሰችም አሁን ገናናት ቀን ጎድሎባታል ባንዲራዋም ዘመም ብሏልና !


"........ አገር የሞተ 'ለት ወዴት ይዴት ይደረሳል ?"እንዲል ባለ ሀገር ቴዲም
"የአርበኞች የድል ችቦ ለትዉልድ እንዳበራ
መኖር ላገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ "ይላል ።
ሰርጌና ሞቴ በሀገሬ ይሏል ይህ ነዉ በአገር ሲኖር ሰላም በንግስናዉ ማማ ሲከብር ሞትም ሰርግነዉ ። ቴዲ ይህንኑ በዜማ እያዳወረ ይነግረናል ።



" አመት አወደ አመት ድገመን ሲሉ
ልጆች በቀየዉ ችቦ እያበሩ
መስቀል ፋሲካዉ ዒድ እንቁጣጣሽ
አዉደ አመት አይሆን አንች ካልመጣሽ " የሚልላትን በእናት የምትመሰል ሀገሩ በተመጠነ ግጥምና ዜማዉ እያሽሞናሞነ ሁኚ መስከረም ያሰኘናል ።

ወርኀ መስከረም አዲሱን ዘመን በተስፋ ብርሀን እንደምታፈካዉ ሁሉ ቴዲም
" ዘመን አድሰሽ በፍቅር ቀለም
ብቅ በይ ኢትዮጵያ ሁኝና መስከረም " በሚል ጣፋጭ ስንኙ ያዋቀራት ለጆሮ በሚጣፍጥ ቃና ሲዜም የመስከረምን ፅዱልነት ያጎናፅፋል ።


ሙዚቃ ከተባለ አይቀር ይሔ ነዉ !!

"እንበል አሲዮ ....አሲዮ
ናና ቤሌማ .....ቤሌማ

ብቅ በይና ሆነሽ ሙሽራ
ይብቃን ስደቱ ይብቃን መከራ "

እያሰኘ አጥንት የሚሰረስር ብሶትን በሚነካካ ዜማዉ
"እኛስ ከመንገድ ላይ ጠፍተን መች አወቅነዉ
ብንሔድ ብንሔድ አንደርስም ገና ነዉ በማባረኪያችን ከመንገድ ላይ ዝለን
አይበቃም ወይ ማሳል በዘር ጉንፋን ታመን "

ሲልም ያክልበታል ፤ በል ሲለዉ ግን አዬደለም
" የጀግኖቹ ልጅ አንተ ነህና
ከገር ወዲያ ሞት ሞት የለምና " ብሎ ማለቱ
" ሰዉ በሀገሩ ወይራ ነዉ " ነገር ግን ከሀገር ወዲያ ሞት ሞት የለም እንኳንስ ወይራ ይቅርና ልጥም ሲደላ ነዉ "ባገሬ እያለሁ ሀገር ናፍቄ !!"ይሆናልና ነገሩ ።

ሆኖም ግን
"ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት
ማንም አይገታዉ የተነሳ ለት " ያለዉም ሌላዉ እዉነታ ነዉ ። የተነሳለት የማይገታዉ ኢትዮጵያዊነት ቀና ማለቱም የማይዘነጋ ነዉ
" ቀና በል አሁን
ቀና በል ቀና " መባሉም ለዚህ ነዉ ።


" ብዙ ነሽ አንች ሀገሬ የሞላብሽ ታምራት
ምኩራብሽ የተፈራ የነፃነት ቤት " የሚላት ሀገሩን ታሪኳን ከዜማ ጋር ድርና ማግ አድርጎ
"ትናንት እንደ ጀምበር እያዩት ከአይን ይርቃል
ኢትዮጵያ እንድትመጭ ስንት ቀን ይበቃል ?"
ሲልም ይጠይቃል ።

" ኢትዮጵያ እንድትመጭ ስንት ቀን ይበቃል " ግን የኢትዮጵያ መምጫ መቼ ይሆን ? ከመፅሐፍ ቅዱስ እስከ ቁርዓን ስሟ የሚጠራዉ "ኢትዮጵያ " መምጫዋ የራቀ አይመስልም ።

"ኢትዮጵያዊነት ቀን አለዉ ገና
ስምሽን በክፋ ያነሳሽ ጠፍቶ
አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ
እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል "ሲል ሃቁን ነዉ አንድ ቀን የኢትዮጵያ ትንሳኤ የማይቀርበት ቀን አለ !!
ስንቱ ተሰደደ ይብቃን ሐዘን ለቅሶ
አንድ ሆነሽ ኢትዮጵያ ባየን ፍቅር ነግሦ " ሲል የተመኘዉ ፍቅርም መንገሱ የማይቀር ነዉ ።


ቴወድሮስ ካሳሁን "አርማሽ ከፍ !!ይበል " ያላት ኢትዮጵያ ከፍፍፍ ብላ የምትታይበት ቀን የራቀ ቢመስልም ቅርብ ነዉ
"ዘር ያበቀለዉ ታጭዷል መከራዉ የኢትዮጵያዊነት አሁን ነዉ ተራዉ "ማለቱም ለዚህ ይመስላል ።


በቅዱሱ መፅሐፍ "ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን አይለዉጥም "እንደተባለዉ ኢትዮጵዊነት ትናንትም ዛሬም ነገም የማይቀየር ነዉ ለዚህም ደግሞ
"ጥንት አባቶችህ ያቆዩህን
ከፍ አርገህ ይዘህ ባንዲራህን
ቀና በል አሁን !" ሲል ያስታዉሳል ፤ ያነሳሳል ፤


እንደ አድናቆት ይቆጠርልኝ ዘንድ እንዲህ ስል ስንኝ ልቋጥርለት
" እንደ ማር ወለላ ምላስ ላይ ይጥማል ፣
እንደ ቀዝቃዛ ዉሃ ጉሮሮን ያርሳል ፣
እንደ ወዳጅ ከንፈር ልብ ያረሰርሳል ፣
ልብ ድረስ ዘልቆ እንደ ደም ይረጫል ፣
ጆሯችንንማ መቼም አክሞታል ።


ለዛሬ ፅሁፌን በዚህ ቋጨሁ !!!


የምትሉኝን ለመቀበል @Ermiasdebassu የሚለዉን መስመር ከወራሪ ሀይል ነፃ አድርጌ አጥብቃችሁ አለሁ ።

ሌላም ሰፊ መንገድ ከሻታችሁ ወደ እዚህ ቤት አባወራ ዝለቁ ፦ በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት
114 viewsErmias Debasu, 07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ