Get Mystery Box with random crypto!

የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch

የቴሌግራም ቻናል አርማ theideaofs — የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch
የቴሌግራም ቻናል አርማ theideaofs — የዘር ሐሳቦች/ Yezer Hasaboch
የሰርጥ አድራሻ: @theideaofs
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.31K
የሰርጥ መግለጫ

እያንዳንዱ ሐሳብ ዘር ነው

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-16 01:23:30 #ለሌሎች_መኖር_ስንጀምር_ህይወት_ውብ_ትሆናለች!!

ለራስህ መኖር ስትጀምር ጎበዝ ትባላለህ፥ ለሌሎች መኖር ከጀመርክ ግን ታላቅ ትሆናለህ!!

ህይወት የሚያምረው ለራስ በመኖር ብቻ ሳይሆን ለሰዎች መኖር ስንጀምር ነው። እጃችን የተፈጠረው ለመጉረስ ብቻ ሳይሆን ለማጉረስም ጭምር ነውና። ራስ ወዳድነት እና ብልጣብልጥነት በገነነት አለም ለሌሎች ስለ መኖር ማውራት ሞኝነት ቢመስልም መኖር ግን ያለው ለሌሎች በመኖር ውስጥ ነው። የአንዳችን መኖር ለአንዳችን እጅግ አስፈላጊ ነው። ለሌሎች መኖርን መቆረስን ያየነው ከክርስቶስ ህይወት ነው።

እግዚአብሔር በገንዘብ ሲባርከን ለሌሎች ማካፈል እንድትችል የበረከት ዕድል ሰቶናል ማለት ነው። ይህ ባሉን በሁሉም ባሉን ነገሮች ይሰራል። ትክክለኛውን በረከት የምናገኘው ለሌሎች በመኖር ጭምር ውስጥ ጭምር ነው።

“ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።”
— ማርቆስ 12፥31
..........
ዘሪሁን ግርማ

የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
https://t.me/theideaofs
247 views22:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 14:40:46

328 views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 22:11:52 #ከመላመድ_መናናቅ_መጠበቅ!!

ከሰው ጋር መቀራረብ አብሶ መስራት እና ይበልጥ መተዋወቅ እጅግ ጠቃሚ ነው። ለሰው አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መሐል ሰውን ማወቅ፥ አብሮ መስራት ህብረት ማድረግ ነው። ከሰው ጋር መስራት ደግሞ መላመድ የሚባልን ነገር ያመጣል። መላመድ በራሱ ችግር ባይኖረውም በመላመድ ውስጥ በጣም መቀራረብ አለና ያኔ ሰውየውን መሰልቸትና መናናቅ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

'ሰዎች በጣም ስትቀርባቸው የሚንቁህ በጣም ስትርቅ የሚያከብሩህ' ምክንያቱ ሰትቀርባቸው አንተንና የአንተን ነገር ስለሚላመዱ እና መላመድ ደግሞ ሚዛናዊ ሰው ካልሆነ መናናቅና መሰላቸትን ስለሚያመጣ ነው። ይህን ለማወቅ ሰዎች በሩቅ ሲያውቁህ ስላንተ ያላቸው ግምት ከፍ ብሎ የነበረ ከነበረና እያገኙህ ሲመጡ ግን ከቀለልክባቸው እነዚህ አይነት ሰዎች የመላመድ በሽታ ውስጥ ናቸው።

መላመድ እጅግ ጥሩ ነው። እንደ በሰለ ሰው ከተጠቀምንበት ሰዎችን ለማወቅና ለመረዳት እና ለመርዳት ይጠቅማል። ማወቅ ያለንብን ቀረብ ብለን ስናየው ማንኛውም ሰው የራሱ የሆነ ክፍተት አለው። ወደ ማንኛውም ሰው ከመቅረባችን በፊት ስለ ሰዎች ያለንን 'የተጋነነ' አመለካከት ማስተካከል ከቀረብነው በኃላ በሚዛናዊነት መሔድ ያስፈልጋል። የመላመድ ሌላው ችግር በሰዎች ውስጥ ያለውን እቅም እንዳይቀበል ማድረጉ ነው።

ሰዎች ሌሎች ሰዎች እንዲቀርቧቸው የማይፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ። ምክንያቱ ደግሞ የመላመድ በሽታ የሚያመጣውን ችግር ስለማይፈልጉ ነው። ለበሰለ ሰው መላመድ የመፋቀር በር ነው። ሰውን በጣም ባወቅነው ቁጥር ልንወድው እንጂ እንድንንቀው አይገባም። ከሰዎች ጋር ያለ ልክ ተቀራርበህ እና ተላምደህ ከሚያሳዩህ ነገር የተነሳ ከመጣላት ተራርቆ ተዋዶ መኖር ሌላኛው አማራጭ ነው።

ዘሪሁን ግርማ

የቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
https://t.me/theideaofs
501 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 04:05:12 እያንዳንዱ ሐሳብ ዘር ነው
560 views01:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 20:27:48
576 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 20:41:30 ሰዎች ስለ አንተ በማያውቁበት ጊዜ ስለ ራስህ ብዙ አታውራ!! ስለ አንተ ሲያውቁም አውቀዋልና አታውራ። በህይወት ምሳሌነትህ ታወቅ!!
754 views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 19:44:35 #ንጽህና_ከጸሎት_ይቀድማል!!

አንድ በቅርበት የማውቀው ወጣት አገልጋይ አለ ይህ ልጅ አባቱም አገልጋይ ናቸው። ልጁ በተደጋጋሚ ሲጸልይ ያዩታል። አንድ ቀን ልጃቸውን "ጸሎት ብቻ አታብዛ ህይወትህ ንጹህ እንዲሆን ትጋ" እንዳሉት አጫውቶኛል። በጸሎት ንጽህና እንደሚጠበቅ አምናለሁ። ከዛ በላይ ግን አኪያሄድን እንደ እግዚአብሔር ቃል በማድረግ ይጠበቃል። ጸሎት ለግልም ለአካሉም እጅግ አስፈላጊ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብዙዎቻችን ጸሎት፣ የአንዳንዶቻችንን ይቅርታ፤ የብዙዎች ንስሃ ሳይ ጥያቄ ይፈጥርብኛል። ጸሎት በማብዛት ብቻ ህይወት አይጠራም እግዚአብሔር ራሱ የማይሰማው የጸሎት አይነትና ህይወት አለና።

የህይወታችን ንጽህና እንደ ቃሉ ብንሰራው ይቅርታችን የእውነት፤ንስሃችን የፍሬ ፤ ፍቅራችን ያለ ማስመሰል፤ አኗኗራችን ለጌታ ቢሆን ጸሎታችን ታላቅ አቅም ይኖረዋል። "በተሳሳተ መንገድ ላይ ቆመን የምናበዛው ጸሎት ለውጥ አያመጣም።" አቋቋማችንን፤ አረማመዳችን ማጥራት ለጸሎታችን ታላቅ ሐይልን ይሰጣል።

ጸሎታችን መንገዳችንን ከማስተካከል ጋር ቢሆን፤ ይቅርታ ስንጠያየቅ ከልባችን ቢሆን፣ ንስሃ ስንገባም ከመመለስ ጋር ቢሆን ለምድሪቱ ለቤተክርስቲያንም ታላቅ ለውጥ ይሆናል። ጸሎታችን ከእውነተኛ ልብ ጋር ቢሆን ፍሬያችን የበዛ ይሆናል።

ዘሪሁን ግርማ
የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ!!
https://t.me/theideaofs
767 views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 06:49:44
907 views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 06:49:27 #የመዘምራን_አለቃና_እረኛ #መጋቢ_ደበበ_ለማ
ዘሪሁን ግርማ

እኛ ስንጠራው "ጋሽ ደቤ" (በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር) እንለዋለን። በጣም የተወደደ የቤተክርስቲያን አባት፥ የመዘምራን አባት የተወደደ እና በመዘምራን (Choirs) አንጻር እጅግ በብዙ ሺዎች ዘማሪያን ያፈራ እና ቀዳሚ ፈር ቀዳጅ ከምንላቸው ነው ጋሽ ደቤ። በቅርቡ ዘማሪ ሳሚ ተስፋሚካኤል 'ስላገለገልከን እናመሰግናለን' ብሎ ባዘጋጀው የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ካባ አልብሶ አመሰግኖታል። ጋሽ ደቤ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የመዘመራን አለቃ ሆነህ በብዙ ዘማሪያን ስላፈራህ፥ ስላገለገልከን እኛም እናመሰግናለን። የጋሽ ደቤ አገልግሎት ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ስለ ስራው ስራ ሁሉ ለማውራት አይደለም። እሱን በተመለከተ "የተፈጸመ ጥሪ" በመጋቢ ደበበ ለማ ቦጋለ የህይወት ታሪኩንና፥ የአገልግሎት መንገዶቹን ጽፎልናል። ገዝተን እናንብብ። እኔ ጥቂት ስለ ጋሽ ደቤ የማውቀውን

መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ " መጋቢ ደበበ ለማ በአዲስ አበባ በቀድሞው የጽዮን መዘምራን፥ በመሪነትና በሙዚቃ ተጨዋችነት ያገለገለ ወንድም ነው። ብዙዎቹን ዝማሬዎች በቃሌ አጥንቻለሁ።
በአገልግሎቱ ስር ያደጉ ብዙዎች፥ መጋቢ ደበበን እንደ አባት ያዩታል..." ያላሉ።

ሐዋሪያው ዳንኤል ጌታቸው ደግሞ "...ከደበበ ጋር ከልጅነት ጀምሮ የምንተዋወቅ ሲሆን፣ በኃላም በእግዚአብሔር ቤት አብረን አድገናል። በተለይም የላይኛይቱ ጽዮን በመባል በምትታወቀው ጸሎት ቤት፣ ከሌሎች ወንድሞች ጋር በመሆን ጌታን ስናገለግል በዚያ ወቅት ነበር ለእኔና ለፓስተር ደበበ የአገልግሎት ጥሪ የደረሰን። 1961-1964 በነበረን አስደናቂ ጊዜ የጌታን ክብር ዐብረን ተለማምደናል።" ይላሉ።

ጋሽ ደቤ ጌታን የተቀበለው በ1959 ሲሆን በጌታ ጥሪን ተቀብሎ ማገልገል የጀመረው በ 1967 ነበር። ጌታን እንደተቀበለ ጌታን እሱን ለአገልግሎት የሚፈልገው በመዘምራን አገልግሎት አቅጣጫ እንደሆነ ነገሮታል "አንተ የመዘምራን አለቃና እረኛ ነህ.." እንዳለው ጋሽ ደቤ አጫውቶኛል።

ጋሽ ደቤ ለአገልግሎት የጌታን ጥሪ ከተቀበለበት ጀምሮ የአገልግሎቱን አቅጣጫ በዝማሬ፤ በሙዚቃ እና ኳየሮችን በማደራጀት ላይ አተኩሮ ላለፉት አርባ አምስት አመታት በላይ አገልግሏል። በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ የጋሽ ደቤን ያህል መዘምራንን ያደራጀና፥ ብዙ ዝማሬዎችና መዘምራንን ያፈራ ሰው በታሪክ አላውቅም። በግሌ አለ ብዬ አላምንም።

#የመዘምራን_ህብረቶች (Choirs) ጋሽ ደቤ በሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የተቋቋሙ የC መዘምራን 115 ፣ D' መዘምራን 240 ፣ E' መዘምራን 240፣ ኢዮሳፍጥ መዘምራን 280 ፣ የኮተቤ ሙሉ ወንጌል መዘምራን 30 መዘምራንን ያቀፉ ኳየሮችን መስርቶ አደራጅቷል። ጋሽ ደቤ በየ ክፍለ ሃገር እየሄደ የተለያዩ ኳየሮችን እያሰለጠነ የመዘምራንን ህብረት (Choirs) አደራጅቷል። ጋምቤላ፥ ሆሳዕና፥ ደሴ፥ መቀሌ፥ ደምቢዶሎ፥ ነቀምቴ፥ ሃዋሳ፥ ኦሞ ሸለቆ፥ ሾኔ አርባምንጭ፥ ባኮ፥ ፊንጫ ይገኙበታል። ጋሽ ደቤ "የተፈጸመ ጥሪ" የተሰኘውን የህይወት ታሪኩን እንዲሁም በዝማሬ ዙሪያ "አምልኮ መዝሙርና መዘምራን" የሚል መጽሐፍ ጽፏል። ይህ መጽሐፍ ወደ ኦሮምኛ ጭምር ተተርጉሞ ይገኛል። ጋሽ ደቤ አኮሪዲዮን እየተጫወተ ያገለግላል።


#የሶሎ_ዘማሪያን ጋሽ ደቤ አሁን በሶሎ ዘማሪነት የምናውቃቸው ዘማሪንንም አፍርቷል ከእነዚህ መሐል "...ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል፥ ዘማሪ ዮሴፍ ካሳ፥ ዘማሪ ወድማየሁ የልቤ፥ ዘማሪ ኤፍሬም ዳኜ፥ ዘማሪ ዮሐንስ በላይ፥ ዘማሪ ሔኖክ አዲስ፥ ዘማሪ ሳሙኤል ንጉሴ፥ ዘማሪ አማኑኤል በፍቃዱ እና እጅግ እና ወደ 20 የሚጠጉ ሶሎ ዘማሪያን በዚህ አገልግሎት እንዲወጡ ጋሽ ደቤ ብዙዎቹን አስተምሯል።

መጋቢ ደበበ ለማ (ጋሽ ደቤ) ለ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን፥ አጠቃላይ በአገራችን ላለው የዝማሬ አገልግሎት ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ብዙ ፍሬዎችንም አፍርቷል። መላው የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናትን ጠቅሟል። ጋሽ ደቤ ስላገለገልከን እናመሰግናለን። እንወድሃለን።
758 views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 11:18:21
945 views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ