Get Mystery Box with random crypto!

የካሌብ ጽሑፎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ thehabesha0 — የካሌብ ጽሑፎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ thehabesha0 — የካሌብ ጽሑፎች
የሰርጥ አድራሻ: @thehabesha0
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይድረስ:-
ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያውያት!
በእግዚአብሔር ስም ሰላምታዬን አቀርብላችኋለው"
የኢትዮጵያ መካነ አእምሮ ወደሚገኝባት ወደ ኢትዮጵያዊነት የእውቀት መዲና ለመጓዝ ፈቃደኞች የሆናችሁ ሁሉ ኑ!
ወደዚያ የሚያደርሳችሁ በመንፈስ ቅዱስ የሚነዳ የውይይት ሠረገላ ይኧው ተዘጋጅቶ ቀዳማዊ ጉዞውን ሊጀምር ይጠብቃችኋልና ተሣተፉ!
---ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት---

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-05 22:23:22
ኔፍሊም እነማን ናቸው?
#በካሌብ_ፅሁፎች
እጭር ዶክመንተሪ ፅሁፍ በቅርብ ቀን ለናንተ አደርሳለሁ
share & Join @kalebo19King
➸ @TheHabesha0
➸ @TheHabesha0
➸ @TheHabesha0
4.1K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 20:16:59 ውድ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች በጠቅላላ ይሄ ቻናል ሊያመልጣችሁ አይገባም ቻናሉ እንዲህ ይለናል



❍✰✦ አንብብ ባታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና ነው ብታነብ ደግሞ በዙሪያህ ያላየሃቸውን ብዙ ነገሮች ማየት ትጀምራለህ
━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━━
ህይወት አስቸጋሪ ናት ማሰብ የማትችል ከሆንክ ደግሞ የበለጠ ታስቸግርሃለች የተላያዩ ፅሁፎችን እና መጽሐፎችን ባማረ መልኩ በተለያዩ መንገዶች እናቀርባለን

ስለተደበቁ ምስጢራት እንዲሁም ስለ ጥንታዊና ያልተደፈረው ታሪካችን ፣ማንነታችን... ከአዳም (አድማኤል ኪሩብ) እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ድረስ ከዛም አልፎ እስከ አሁን ሰሞነኛ ጠቅላይ ምኒስቴርና ፕሬዝዳንቶች ድረስ ሳንፈራ ሳንደብቅ ፊትለፊት በእውነት ፊት እናያለን እንገልጣለን

ስለ ሃገር ፍቅር እና
ኢትዮጵያዊነት በሰፊው የሚቀነቀንበት

የልተበረዘ ያልተቀላቀለ ትክክለኛው የሃገራችን ታሪክ የሚያገኙበት እና እስከ ፍልስፍና ጥግ ድረስ በሃሳብ እና እውቀት የምንነጉድበት ቻናል ነው ቶሎ ግቡ እና ተመልከቱት ያልተመቸው የመውጣት መብቱ የተጠበቀ ነው

በርግጠኝነት ትወዱታላችሁ እውነት ነፃ ታወጣለች ቅንነትም በእጥፍ ትከፍላለች ....

ቻናሉ የተመቸው ለወዳጅ ዘመዱ ሁሉ በመጋበዝ ቅንነቶን ያሳዩ ተደራሽነታችንንም እናስፋ

#የካሌብ_ፅሁፎች

ቻናሉን ለመ ላ ል

@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0

እምዬ ኢትዮጵያ ትንሣኤሽን ያሳየን
..... ....
1.1K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 20:04:37
ነፃ ጥቅል ከኢትዮ ቴሌኮም !

- ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

- ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።

- ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

- ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

- 1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

- 45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

- 100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

- የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

- (ማስታወሻ ፦ ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)

- ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።


══════❁✿❁ ═════════

ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት

@TheHabesha0
@TheHabesha0
900 views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 01:25:22 #የካሌብ_ጽሑፎች

...አንዳንዴ ሊያጠፋን የተላከ መቅጸፈት የሚመስለን ከችግራችን ሊጋርደን የመጣ መለአክ አድርገን መቀበልና ማመን ጥሩ ነው....ችግር ያልነው ከከፋው ችግር ሊያድነን ነው የሚመጣው....አንድ ታማሚ የግድ ትንሿን የመርፌ ስቃይ መቋቋም ይኖርበታል ትልቁን ፈውስ ለማገኘት ..... ሁሉም ነገር ለበጎ ነው..የሚባለው እንዲሁ አይደለም በታላቅ ምክንያት ነውና! ክፉን መልኳም ነው ስንለው አቅም ያጣል..ልብ ካለው ልቡ ይነካል..በህይወትችን ውስጥ እኛ ክፉ ያደረግናቼው እንጂ በራሳቼው ብቻ ክፉ የሆኑ ነገሮች የሉም ከሳጥናኤል በቀር! ሞትም ቢሆን ላወቀበት ጸጋ ነው.....ላላወቀበት ግን ኑሮም ሞት ነው ... ከልምድ እንዱሁ ከመኖር በምክንያት እና በማስተዋል የምኖርበትን ዘመን እግዚአብሔር ይስጠን..ጥበብና ማስተዋሉን ያድለን... መልካም ምሽት


@Kalebo19King

#Join & #Share

@TheHabesha0
4.8K views22:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 23:43:51 ሰላም ለሁላችሁም የእናቴ ልጆች እንደምን አላችሁ? #ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረ_ገጽ_ነው። መልካም ቆይታ

ከህይወት ብዙ ተምሬያለሁ

ብስለት የሚመጣው ከሚያጋጥሙን ተሞክሮዎች ዓይነት እና ከተሞክሮዎቹ ከቀሰምናቸው ትምህርቶች እንጅ ካከበርናቸው የልደት በዓሎች ብዛት እንዳልሆነ ተምሬያለሁ።

እንዳንዴ የቱንም ያህል ለሌሎች ብጨነቅ እና ግድ ብሰጥ አንዳንዴ አንዳንዶች በመልሱ ግድ ላይሰጡ እንደሚችሉ ተምሬያለሁ።

ቤተሰብ ሁልጊዜም መከታ ድጋፍ እንደማይሆን ተምሬያለሁ። ጓደኞች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆን አልፎ አልፎ ማስቀየማቸው እንደማይቀር ተምሬያለሁ። ባስቀየምናቸው ሰዎች ይቅር መባል በቂ ያለመሆኑንና ራስንም ይቅር ማለትም እንደሚያስፈልግ ተምርያለሁ።

መታመንን ለመግንባት ዘመናት እንደሚያስፈልግ ፤ ለማውደም ግን ሰከንዶች ብቻ እንደሚበቁ ተምሬያለሁ።

አንዳንድ ጊዜ ተንሸራትተህ ስትወድቅ ይረጋግጡኛል ብለህ የምትጠብቃቸው እና የምትፈራቸው ሰዎች ብድግ አድርግው በማንሳት እንደሚያስገርሙህ ተምሬያለሁ።

በአስተዋይነት "እምቢ" ማለት ሁልጊዜም
የንፉግነት ምልክት ያለመሆኑን “እሺ” ማለትም ሁልጊዜ ምግባረ ሰናይነትን እንደማያሳይ ተገንዝቢያለሁ።

ራስን ከጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ከጥላቻ የምንገላገልበት ብቸኛ መንገድም የአለፈውን ጊዜ ረስተን ከአሁን ጋር እርቅ ማድረግ ስንጀምር እንደሆነ ተምርያለው።

መልካም ምሽት! ቻናሉን ላልተቀላቀሉ አእምሮአዊያን ሰዎች ሁሉ በቅንነት ይጋብዙ

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0

እንደተለመደው ማንኛውንም ጥያቄና አስተያየታችሁን በ @Kalebo19King ላይ ብታደርሱኝ በተቻለኝ መጠን ለመመለስ እሞክራለሁ።
5.6K views20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:58:30 ሰላም ለሁላችሁም ውድ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያውያት #የካሌብ_ጽሑፎች የቴሌግራም_ድህረገጽ_ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? ረዘም ካለ ጊዜ በኋላ እንደተመለስኩ አውቃለሁ
መቼም ሰላም፣ፍቅር፣አንድነት እና በጎ ነገሮች የምንሰማና የምናይበት ጊዜ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ምን አልባት ሰላም ነው፣የተለመደ ነው እና የመሳሰሉትን የራስ አጥፊ ሞኝ ሰው ትርክት በየአቅጣጫው መስማታችን እየተለመደ ከመሆኑም አልፎ ሕይማኖት ሲፈርስ እምነት ሲለወጥ ዘር ሲቆጠርና ሲያየጥፍ በአይናችን እያየን ነው ግን ግን እኔ ታናሻችሁ የገባኝና የተረዳሁትን ልንገራችሁ እስኪ ልብ በሉ እውነትን ካልወደድንና ካልተቀበልን መጨረሻችን መጥፎ ነውና እንደቀልድ በእሳት መለብለባችን እንዲሁም በግፍ መበላታችን የማይቀር ይሆናል። ይህ ፈራሽ ስጋ ከነፍሳችን መለየቱ እንኳን ግድ የለም ደሞዛችን ነው። ነገር ግን ያለጊዜ መቀጠፍ እና መነቀልም አለ እና አስተውሉ።

በእርግጥ በዚህ ጊዜ እንደምናውቀው ሁሉም መምህር እና መካሪ ሆኗል
''መኖር የከበደው መምህር''"
ወይም ነጻ ያልወጣ ነጻ አውጪ እንደማለት ነው። እናም መስማት የማይወድ አማራጩ ሁሉን መቀባጠር ነውና ሰውንም ራሳችሁንም ታዘቡ!!! ተማሩ

#ታሪክ የሌለው ህዝብ ታሪካዊ ስራ ለመስራት አይጓጓም። ነፃነትም የማያውቅ ህዝብ ነፃነቱን ለማግኘት አይደክምም። #ኢትዮጵያ አስደናቂ የሆነ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ነፃ ሀገር ስለሆነች ልጆቿ ታሪኳን ዐውቀው የነፃነቷን ጉልላት ጠብቀው እንዲኖሩ ግዴታቸው ነው። አንድ ወጣት የሀገሩን ታሪክ ሳያውቅና ሳያጠናቅቅ የአውሮጳንና የአሜሪካንን ታሪክ ለማሳመር ቢሞክር < በቅሎ አባትህ ማነው? ቢሉት ፈረስ አጎቴ ነው> ይላል እንደሚባለው የሚያሳፍር ይሆናል።"

#ይህ_የካሌብ_ጽሁፎች_ነው። የቴሌግራም_ድህረገጻችንን_ ከታች ያለው Link በመጫን ይቀላቀሉን።

@TheHabesha0 @TheHabesha0


ኢትዮጵያ ምድረ ገነት የአለማት በር!
1.5K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 20:39:51 ሰላም ለሁላችሁም ውድ #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ቤተሰቦች እንዴት መምሻችሁ?
ይህን ከታች የምታነቡትን ምክር/ጥበብ ቢጤ ማንበብ ብዙ መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነው የተባለላቸው እጅግ ጠቃሚ ነገሮችን ከተለያዩ ቦታዎች ሰብስቤ በአንድላይ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ ከዚህ በፊት በቻናሉ እንደለቀቅኩት የሚታወስ ነው እና ወደ እለቱ ጽሑፍ ልምራችሁ

መልካም ንባብ.....

በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።

የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።

ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።

የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።

ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።

ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።

ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።

እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።

ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።

በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።

የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።

ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!

መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።

ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።

ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።

ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።

ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።

ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።

እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።

የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ።

ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት

@TheHabesha0
@TheHabesha0
9.6K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:11:13 ሰላም ለሁላችሁም ውድ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያውያት #የካሌብ_ጽሑፎች የቴሌግራም_ድህረገጽ_ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? እንዴትስ አመሻችሁ..!

<< አንድ ሕዝብ ወይም ማኅበረሰብ በጥቅሉ ፈሪ፣ ጠማማ፣ ሰነፍ፣ ገብጋባ ወይም ሌላ ሊባል አይችልም። እነዚህ ጠባዮች የግለሰብ ጠባይ ናቸው። ኅብረተሰብ ወይም ማኅበረሰብ የግለሰቦችን ጠንካራ ጠባይ በማቀናጀት ለተሻለ እሴትና ሞራል የተፈጠረ ተቋም ነው። በዚህ እድገቱ ከግለሰብ ላቅ ያለ ጠባያት ያሉት ነው። ስለሆነም አንድን ሕዝብ ወይም ሕብረተሰብ ፈሪ፣ ጠማማ፣ ገብጋባ፣ ማድረግ ኅብረተሰብ የዕድገት ውጤት መሆኑን አለመረዳት ነው። የማንኛውም ሕዝብ መገለጫ ጠንካራው የግለሰብ ጠባያት ናቸው። የግለሰብ ደካማ ጠባያት የሕዝብ ወደ መሆን ከተቀየረ ማኅበረሰቡ አርጅቷልና ፈርሶ መሰራት ይኖርበታል ማለት ነው።

በመሆኑም እንደ ታናሽና ታላቅ ወንድም ሲበላ ሲጠጣ የሚነገርን ተረብ ቁም ነገር አድርጎ የሕዝብ መለያ ጠባይ አድርጎ መውሰድ ማይምነት ነው። በሌላ በኩል እንዲህ ያለውን የወንድማማችነት ለከትን የፖለቲካ ካባ አልብሶ የብሔር ቁርሽ ማነሳሳት እጅግ አሳፋሪ ነው። ብሔርተኞች እንዲህ ያለውን ነገር ሲያገኙ የጭቆና ካባ አልብሰው ሕዝብን ሊያሰላልፉበት ይችላሉ። ብሔርተኝነት በሰፊ ሜዳ መሮጥ የማይችሉ ድኩማን የሚጠጉበት የጨለማ ዋሻ ነውና። >>



ምንጭ ፦ "መርበብት...ገጽ 149-150
ደራሲ ፦ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ

፨ ከላይ ያሰፈርኳትን የመጽሐፍ ክፍል ባነበብኩ ቁጥር ሁሌም የማስታውሰው የኛን አገር የብሔር ማልያ ለብሰው የሚጫወቱ ድኩማንን ነው። እነሱ ለብቻቸው ቢሆኑ ወይም ብቻቸውን ቢጠፉ ችግር አልነበረውም ግን ብዙ ተከታይ መንጋዎች አሏቸው ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ እንዳለው "መንጋጋት እንጂ ማንጋት" የማይችሉ። የሚገርመው ደግሞ የነሱ ክፉ ሃሳቡ ከመልካሙ አተያይ በፈጠነ መልኩ መሰራጨቱ እና ሀይ ባይ ማጣቱ ነው። ምን ይደረግ እንግዲ አንድ በርሜል ውሃ በአንድ ብልቃጥ መርዝ አይደል የሚበከለው! ትንሽ ያልናቸው ድከማን ትንሽ ሃሳቦቻቸውን የሚሸከሙላቸው የአስተሳሰብ ወዛድሮች ከስራቸው እንደ አሸን ፈልተዋል አምላካችን እሱ በጎውን ዘመን መልካሙን ዘመን ያምጣልን እኔ በዚሁ አበቃሁ

ይህ #የካሌብ_ፅሁፎች ነው።

ስለመረጡን አክሮታችን ላቅ ያለ ነው! ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ከታች አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ልብ ቅርጽ መሀል ያለውን ሰማያዊ ሊንክን በመንካት #Join ያድርጉ ድህረገጹ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል ሆኖ ካገኙት ሌሎችም ይቀላቀሉን ዘንድ በቅንነት #Share #Forward በማድረግ አብረውን ይቀጥሉ

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0
3.7K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 20:12:15
#አስደንጋጭ_ዜና

የዝንጀሮ ፈንጣጣ፡ በ11 አገራት 80 ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል! - የዓለም ጤና ድርጅት

በ12 ሀገራት በዝንጀሮ በሽታ የተጠቁ ከ80 በላይ ተጠቂዎች መኖራቸው ተረጋገጧል። የዓለም ጤና ድርጅት ሌሎች 50 ተጨማሪ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም የጤና ድርጅት የትኛውንም ሀገር ስም ሳይጠቅስ ተጨማሪ ሰዎች ላይ  ሊገኝ እንደሚችል አስጠንቅቋል።ኢንፌክሽኑ በዘጠኝ የአውሮፓ አገራት እንዲሁም በአሜሪካ ፣ በካናዳ እና በአውስትራሊያ ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል።

የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት እንደገለጸው ይህ ያልተለመደ የቫይረስ ኢንፌክሽን ቀላል እና አብዛኛው ሰው በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሊያገግም ይችላል ብለዋል። ቫይረሱ በሰዎች መካከል በቀላሉ የማይሰራጭ ሲሆን ይህም ያለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ያደርገዋል። ለጦጣ በሽታ የተለየ ክትባት ባይኖርም ለስሞል ፖክስ የሚዘጋጀው ክትባት 85 በመቶ መከላከል የሚችል ሲሆን ሁለቱ ቫይረሶች በጣም ተመሳሳይ ናቸው ተብሏል።

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
5.3K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ