Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለሁላችሁም ቤተሰቦች ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት ዛሬ ትላንት በነገርኳችሁ መሰረት ስለ | የካሌብ ጽሑፎች

ሰላም ለሁላችሁም ቤተሰቦች ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት ዛሬ ትላንት በነገርኳችሁ መሰረት ስለ የጀርመኑ ናዚ አርማ እና ስዕለ ኪሩብ! ጥቂት ላውራችሁ..ተከተሉኝ..መልካም ንባብ...

የምስጢር ማህበረሰብ በመባል የሚጠሩት የስማዝያ ጭፍሮች በተለያየ ዘመን ወደሃገራችን በመግባት የተለያዩ ቅርሶችን መጽሀፍትን መንፈሳዊ አንድምታ ያላቸውን ጠልሰሞች ከሃገራችን መበዝበዛቸው አሁንም እየበዘበዙ እንዳሉ በተደጋጋሚ ለመግለጽ ሞክሬያለሁ፡፡ ታዲያ ለዚህ ስውር ደባ እንደ ማስረጃ ከማቅረባቸው ጠልሰማት አንዱ ስዕለ ኪሩብ የተሰኘውን ጠልሰም ነው፡፡ የምስጢር ማህበረሰቡ አንድ እጅ የሆነው የጀርመኑ የናዚን ቡድን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ አካላት ሰዋስቲካ ብለው የሰየሙትን ምልክት ለጦር ሃይላቸው አርማ ሲጠቀሙ በመመልከታችን የኛ እንዳልሆነ ለዘመናት ተቀብለን አምነናል እንዲሁም ተምረናል፡፡ እውነቱ ግን ይህ አይደለም የምስጢር ማህበረሰቡ መንፈሳዊ ጥበቦች እና ምስጢራቶችን ተቀራምቶ ዓለምን ለመግዛት ለዘረፋ ከተሰማራባቸው ሀገራት ቀደሚ ስፍራ የምትይዘው ኢትዮጵያ ስትሆን ከተወሰዱብን ጠልሰሞች መካከልም በነርሱ አጠራር ሰዋስቲካ የተሰኘው ጠልሰማችን ነው፡፡ ይህ ጠልሰም የስድስት ሺህ ዓመት ታሪክ ባላት በጥንቷ ኢትዮጵያና በጥንታዊ መጽሀፍቶቻችን ስዕለ ኪሩብ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ኢዮር በተሰኘችው የእሳት ዓለም ውስጥ የሚገኙ የመላእክት ነገዶች ናቸው፡፡

፩. በመጀመሪያው ምስል እንደምትመለከቱት የውጭ አካላት በተለይም የጀርመኑ ናዚ ጦር እንደራሱ በማስመሰልና ስዋስቲካ ብሎ በመሰየም ተጠቅመውበታል።

፪. በሁለተኛውና ሶስተኛው እንደምትመለከቱት ግን ይህ ጠልሰም የእኛ የኢትዮጵያውያን ማለትም በላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተክርስቲያን በግድግዳው ላይ በግልፅ ተቀምጦ እናገኘዋለን። ስሙም ስዕለ ኪሩብ ይባላል። ስለዚህ ጠልሰም ጠለቅ ያለ ማብራሪ በሌላ ክፍል የማቀርብላችሁ ይሆናል ለዛሬ በዙሁ አበቃሁ እኔ ዓጼ ካሌብ ነበርኩ ። ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ በ @kalebo19king ላይ አድርሱኝ ድህረገጹንም በቅንነት ለሌሎች ያጋሩ መልካም ምሽት።

ታድያ ይህ ጠልሰም የእኛ ነው ወይንስ የእነሱ? የሚለውን ለሁላችሁም አንባቢያን እተወዋለሁ

ፈጣሪ ቅድስት ሐገራችን በምህረቱ ይቅር ይበላት ከልጆቿም መከራና ስቃይ ይገላግላት!

ይህ #የካሌብ_ጽሑፎች የቴሌግራም ድህረገጽ ነው

ኢትዮጵያ ሁን 
አፍሪካ ሁን
ሰው ሁን

ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል

@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0

................................................