Get Mystery Box with random crypto!

#ትዝብት በ #ካሌብ_ጽሁፎች .........ትውልድ እንታደግ ሰላም ለሁላችሁም በያ | የካሌብ ጽሑፎች

#ትዝብት በ #ካሌብ_ጽሁፎች


.........ትውልድ እንታደግ


ሰላም ለሁላችሁም በያላችሁበት ይሁን!

የነገ ሀገርህ የዛሬውን ትውልድ ትመስላለች ....ኢትዮጽያዬ አወዳደቁዋ እንዳይሆን ሆንሳ ...የነገዋን ኢትዮጽያ አሻግሬ ስስል ምነው ልቤ ሰጋ... ትውልዱ ሱሰኝነት ፣ዘረኝነት እና ሴሰኝነት በሚባሉ ትብታቦች ተተብትቦ የክፋት ሸቀጥ ማራገፍያ ሆነሳ ??! ኧረ ሀገራችንን ከሞት ጉዞ ትውልዱን አንቅተን እንመልሳት ...ወደ እሱነቱ ጥግ ወደ ማንነቱ ከፈፍ እንጎትተው ......ተምሳሌት ወይም መምህር ከሚባሉትስ ምነው ትውልዱ ቁልቁል እንዲንደረደር እና ያለ እውቀትም የሞት ዛፍን እንዲመኝ፣ በድንቁርና በክፋት እንዲወድቅ ፣የክህደት የጥላቻ እና የሴራ ቃላትን አሰሙ፣አስተማሩ/ያለ እፍረትም ለቀቁብን ስንጠፋም ለ፩ ዓላማ ተሰልፈዋልና በደስታ አፌዙብን ?! .....ምንአለበት ትውልዱ ለሀገሩ ለባህሉ ተገዢ እንዲሆን ብንጥር?! ....በተራቆተ ገላ ላይክ ሽመታ ከምንጋልብ ...ምነው የጎጥ ግንብ ሰርተን ከምናባላ ፍቅርን ሀሁ ብንል....የነገር አተላ ድፍድፍ ከምንደፈድፍ ምናለ ትውልዱን ከራሱ ከእምነቱ ከባህሉ ለማስረቅ ደፋ ቀና ብንል ምናለ?.

የከበረው እና ድንቅ ፍጡር የሆነው የሰው ልጅ ያውም /የኢትኤል ልጅ/.....በጭስ ማግ ናላውን ከሚያዞር .....በጫት ደንዝዞ ከሚኖር በውሸትም ፍልስፍና ተለክፎ ኑሮውና ህይወቱ ከሚመነምን....እናም ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብለን ከምናይ ለሐገራችን ነፃነትን ፥ ፍቅር ለመቸር ብንሯሯጥ ለችግረኛው እና እስረኛውስ በቂ እውቀት በመስጠትም ሆነ በምንችለው እየረዳን ከባርነት ነጻ የሚያወጣውን መንገድ ብንመራ....

እናም እኔ እላለሁ ሰው ሆነን ሰውን ሰው ብናደርገው በውስጣችን የገባውን ክፋት ገድለን?

ኧረ ምነው ሀገሬ ልባም ጠፋብሽ???!

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ ይህንን ጦማር ስጽፍ ብዙ ፈጣሪ የሚያውቃቸው እና ከእኛ እጅግ ርቀው ራሳቸውን አግልለውም ሆነ ሰውረው ያሉ የሰው ልጅ ሰዎችም እንዳሉ ልብ ይሏል! በቀጣይ ስንገናኝ በጥያቄያችሁ መሰረት ስለ  የጀርመኑ ናዚ አርማ እና ስዕለ ኪሩብ ! ከኔፍሊሞች እና ፮፮፮ አባላት ጋር የሚያገናኘውን ነገርም አጠር ባለ መልኩ የማደርሳችሁ ይሆናል እኔ #ዓጼ_ካሌብ @Kalebo19King ነኝ ማንኛውም ሐሳብ፣ጥያቄም ይሁን አስተያየት በውስጥ መስመር ማቅረብ ትችላላችሁ አብነሮነታችሁ አይለየን።


ልብ ካለህ ቀድመህ ራስህን በኋላም ትውልዱን አድን!



ኢትዮጵያሁን 
አፍሪካሁን
ሰው ሁን

#ይሄ_የካሌብ_ጽሁፎች ነው

ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል

@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0