2021-03-05 21:17:15
ኖርዊች ሲቲ አስቶንቪላና ማንችስተር ዩናይትድ፣ ከሊጉ አናት ተቀምጠው፣ እንደገና የተዋቀረውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ለመጀመሪያ ግዜ ከፍ ለማድረግ ይፋለማሉ፣ በፈርጊ እንደገና እየተዋቀረ፣ በወጣቶችና በአንጋፋ ተጨዋቾች የተገነባው ዩናይትድ፣ ከቪላም ከኖርዊችም ወርዶ 10ኛ ደረጃ ተቀምጧል፣
ምንምኳን በሊጉ ጅማሬ ጥሩ የነበረ ቢሆንም፣ ዲዮን አንጋፋው ብሪያን ሮብሰን፣ ጉዳት አሰተናገዱ፣ በሊጉ ለሁለተኛ ተከታታይ አመታትን የሊጉ ወጣት ተጨዋች የተባለው ጊግስ የቻለውን ቢያደርግም፣ ክለቡን ወደ 10 ከመንሸራተት ለመታደግ አልቻለም፣ ማርኪዩዝ በ 15 ጎሎች ከፍተኛ ጎል አግቢ ነው፣ ስቲቭ ብሩስ ዩናይትድን በአንበልነት ይመራል፣
የቡድናቸው ወደ 10ኛ ደረጃ መውረድ፣ የከፍተኛ አጥቂዎች መጎዳት ራስ ምታት የሆነባቸው ፈርጊ፣ በጥር የዝውውር መስኮት ኤሪክ ካንቶናን አስፈረሙ፣ በሊጉም አሸናፊነታቸውን ቢመልሱም በ ኤፍ ኤ ካፕ ከሼፊልድ ጋር 1 አቻ አጠናቀው፣ በመለያ ምት ከ 5ተኛው ዙር ተሰናበተ፣
ነገር ግን፣ የሀያሉ ሰው፣ ክላስ ኦፍ 92 የቡድን ግንባታ፣ ከፍተኛ ብርሀን ይታይበታልና፣ በርካቶች በቀጣይ አመታት፣ ዩናይትድን ማቆም ከባድ እንደሆነ ተነበዩ፣ በነ ስኮልስ ጊግስ፣ ቤካም፣ ጋሪና ፊል ኔቭል፣ የመሳሰሉ ወጣቶችን ከነ ማርክዩዝ ስቲቭ ብሩስ ብሪያን ሮብሰን ከመሳሰሉ አንጋፋወች ጋር ያዋሀዱት ሰር አሌክስ ቡድናቸው ከ 10ኛ ደረጃ በመስፈንጠር ወደ 2ኛ ከፍ አለ፣
በከፍተኛ ወኔ በአልሸነፍ ባይነት የቀጠለው ዩናይትድ፣ በካቶና ምትሀተኛ እግሮች ታግዞ የሊጉ የመሪነት ክብርን ከቪላ ተረከበ!! ከተሰቀለ መውረድ የማይወደው ዩናይትድ፣ በአንጋፋው ሰው የአሸናፊነት ስነልቦና፣ በወጣቶቹ አሸናፊነት ታግዞ፣ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ፣ በ 10 ነጥብ በመምራት ቪላን አስከትሎ የሊጉ ሻንፒዮን ሆነ።
በዚህ የተነቃቁትን ወጣቶች፣ በቀጣዩ አመት ኪኖን ጨምሮ አንዳንድ ተጨዋቾችን በመጨመር፣ ዩናይትድ ላይፈርስ ተገነባ፣ በመሀልም ክፍተቱ እየታየ፣ እነ ሮኒ፣ ፈርዲናንድ፣ ቪዲች፣ ቫንስትሮይ፣ ኤቭራ፣ ሹማይክል፣ ቫንዴርሳር፣ ካሪክ፣ ሮናልዶ፣ ቤርባቶቭ፣ ቴቬዝ፣ ኦውን ሀርግሬቭ፣ ፍሌቸርና፣ ሌሎችም ኮከቦች በየግዜው ወደ ዩናይትድ በመምጣት የዩናይትድ ሀያልነት፣ የፈርጊን ክላስ ኦፍ 92 የቡድን ግንባታ በማስቀጠል፣
የተቀናቃኞቻቸውን አከርካሪ በምትሀተኛ እግሮች በመስበር፣ ዩናይትድን ላይወርድ ከድል ዙፋን ከፍ አደረጉት፣
#ማንችስተር_ዩናይትድ_GGMU
#GGMU #MUEF
ሼር/Join
በቴሌግራም @the_red_forever_mv
ግሩፓችንም @man_united_forever
𝙀𝙫𝙚𝙧𝙮 𝙜𝙖𝙢𝙚, 𝙚𝙫𝙚𝙧𝙮 𝙜𝙤𝙖𝙡, 𝙤𝙣𝙡𝙮 𝙤𝙣 በየኛ ማንችስተር ዩናይትድ የ YouTube ቻናል (Ethio Man United) ሰብስክራይብ በማረግ አዝናኝ ጊዜ ያሳልፉ በማንችስተራዊ ስራዎቻችን
Subscribe በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ
http://www.youtube.com/channel/UCT0Z6i9B-WLL9DSNRyr7jvQ
Don't forget subscriber our channel”
211 viewsAbd Abd, 18:17