Get Mystery Box with random crypto!

Andre Onana .... ኢንተር ሚላን የሚፈልገው 50 ሚዮ አካባቢነው ይህን ገንዘብ ላቀረ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

Andre Onana ....

ኢንተር ሚላን የሚፈልገው 50 ሚዮ አካባቢነው ይህን ገንዘብ ላቀረበ ክለብ ኦናናን ለመስጠት ወደኋላ አይሉም
ከሰሞኑ ቴንሀግ ልጁን አሳምኖታል የሚሉ ወሬወች ከሰማን በኋላ ትናንት ደሞ የተጨዋቹ ኤጀንት በማንቸስተር ከተማ ተገኝቶ ከዩናይትድ ጋር ንግግሮች ሲደረጉ እንደነበር ምንጮች በማስረጃ አስደግፈው አወሩ ....

Di marzeo ወኪሉ ከዩናይትድ ጋር መነጋገሩን አረጋግጧል
Fabrzio ም በተመሳሳይ ወኪሉ ከዩናይትድ ጋር መነጋገሩን አረጋግጧል የተጨዋቹ የግል ጉዳዮች በሙሉ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ሲሆን የሚጠበቀው የዩናይትድ እና ኢንተርሚላን ስምምነት ነው ዩናይትድ ኢንተር የሚጠይቀውን ለመክፈል ፍላጎት አላቸው አከፋፈሉግን በረዥም ጊዜ ውል እና ክፍያው የረዥምጊዜ ቆይታ ያለው እንዲሆን ይፈልጋሉ ....

አንድሬ ኦናና 1.90 የሚረዝም ግዙፍ ግብጠባቂነው እሱ በእግሩ ስላለው የመጫወት ኳሊቲ ማውራት ድካምነው ትርፉ እንዴውም ከልኩም አልፎ ሚቀብጥበትጊዜ አለው እጂግ በጣም በልበ ሙሉነት በጥልቀት መሀል ሜዳውላይ ልንመለከተው ሁሉ እንችላለን አንዳንዴ እሱን ስመለከት የቀድሞው የኮሎምቢያ ሌጀንድ ሬኒ ሂጎይታ ትዝ ይለኛል ሂጉዊታን በወቅቱ አላየሁትም የሱን ብዙ ቪዲዮ ግን አያለሁ በእርግጥ ሂጉዊታ ድሪብል እያደረገ ጎል ላግባ የሚል የጠገበ እብድነው

ዋናው ነገር ዩናይትድ ኦናናንም አገኜ ኮስታ ወይም ሌላ ግብጠባቂ ያብቻ ለውጥ አያመጣም ለውጡ ሚመጣ በእግሩ መጫወት ለሚችል ግብጠባቂ የሚመች ቡድን መስራት ነውና ቴንሀግ እንደ ኦናና አይነት ግብ ጠባቂ ካገኜ ቡድኑን በደምብ መስራት እና ከኋላ ለሚጀመረው ኳስ ምቹ ሁኔታዎችን መመስረት አለበት

ኦናና በኢንተር እንኳን በአስተማማኝ ሁኔታ በቋሚነት እየተጫወተ አልነበረም በሴሪኤ በተለይ ብዙ ጌሞች አላገኘም ምናልባት የቡድኑ ቅርፅ ለኦናና ነገሮችን ምቹ ስላላደረገ ሊሆን ይችላል ወይም ኦናና ከልክ በላይ ከኋላ መቅበጡን ጠልተው ሊሆንም ይችላል

ነገርግን አንድሬ ኦናና እጂግ አስደናቂ ኳሊቲ ያለው በእግሩ የሚጠበብ ግብጠባቂነው ።


COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv