Get Mystery Box with random crypto!

መልስ የለም!! ነገሩ እንዲህ ነው፣ ግሌዘሮች ዩናይትድን ለመሸጥ እስከአሁን ድረስ ከሼክ ጃሲም ጋ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

መልስ የለም!!

ነገሩ እንዲህ ነው፣ ግሌዘሮች ዩናይትድን ለመሸጥ እስከአሁን ድረስ ከሼክ ጃሲም ጋር ንግግር ላይ ናቸው፣ ሼክ ጃሲም የመጨረሻ ያሉትን 5ተኛ ዙር ጨረታ ካቀረቡ በኋላ ነገሩ በሙሉ ወደ ኳታር ዞሯል፣ ግሌዘሮችም ንግግራቸውን ከሼኩ ጋር አድርገው ራትክሊፍን ትተዋቸዋል። ታዲያ የቀረበላቸው 6 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አንሶ የታያቸው ግሌዘሮች ሼክ ጃሲምን በእጅ አዙር ገንዘብ ለማስጨመር፣ ለራትክሊፍ ደብዳቤ ይልካሉ።

ደብዳቤውም ከሼክ ጃሲም ጋር እየተደራደርን ነውና፣ ከሼኩ የተሻለ አቅርበህ ዩናይትድን ውሰደው የሚል ነው፣ ራትክሊፍ ካቀረበ ሼኩ ይጨምራሉ ነው ስሌቱ፣ ነገር ግን ግሌዘሮች የጻፉት ደብዳቤ፣ ተቀባይነት አላገኘም፣ ዛሬ ነገ እያሉ ነገሩን አንጓተው ቢጠብቁም፣ ራትክሊፍ አቅማቸውን አውቀው፣ ዝምታን መርጠዋል፣ የግሌዘሮች ደብዳቤም መልስ አልባ ሆኗል።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv