Get Mystery Box with random crypto!

ስኮት ማክቶሚናይ ኤሪክ ቴን ሃግን በጣም የተለየ የሚያደርገውን ነገር ገልጿል 'በማንችስተር በተለ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

ስኮት ማክቶሚናይ ኤሪክ ቴን ሃግን በጣም የተለየ የሚያደርገውን ነገር ገልጿል

"በማንችስተር በተለያዩ አሰልጣኞች ስር ሰርቻለው ሁሉም አሰልጣኝ የራሱ የሆነ ሀሳብ አለው ግልፅ ነው ቴንሀግ ያለው ነገር ከሌሎች አሰልጣኞች
በጣም የተለየ ነው ነገር ግን እኔ እንዳልኩት ይህ እግር ኳስ ነው ሁልጊዜ አንተ ኳሱን ብቻ እንድታስብ ያረግሀል

"በሜዳ ላይ ስለ አዳዲስ ሀሳቦች እና መሰል ነገሮች እንድታስብ ያረግሀል ይህ ለተጨዋቾች ጥሩ ነው ከእግር ኳስ ጋር ለመሆን በጣም ጥሩው መንገድ ይህ ነው ክፍት አእምሮ እና ወደ እያንዳንዱ ጨዋታ መሄድ ዝግጁ መሆን ቴንሀግ አንድ ነገር እንድታረግ ከፈለገ ወደህ ታደርጋለህ በተቻለን መጠን ከኤሪክ ለመማር እንሞክራለን ለኔ እንደማስበው በጣም ጥሩ ነው በአንድ አመት ውስጥ ወድጄዋለሁ

"በዚህ አመት ጥቂት ግቦችን አስቆጥሬያለው ጎል ስታስቆጥር ሁሌም ልዩ ነው ነገር ግን ከዚህ የበለጠ ጎሎችን ማስቆጠር አለብኝ ጥሩ ቦታ ላይ እገኛለሁ በግራ እና በቀኝ እግሬ ኳሶችን መምታት እችላለሁ ይህም በእርግጠኝነ ግቦችን ማስቆጠር እንድችል ያረገኛል እንደማደርገውም እርግጠኛ ነኝ

"ለመጫወት እድሎችን ባገኘሁ ቁጥር የበለጠ ልለወጥ እንደምችል ይሰማኛል በማንችስተር ደስተኛ ነኝ ይህንን ክለብ እወዳለሁ ምንም ይሁን ምን ቢፈጠር ምንም ያህል ደቂቃ ብጫወት አሁንም በየቀኑ ጠንክሬ እሰራ እና ለቡድኑ የምችለውን ሁሉ እሰጣለሁ።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv