Get Mystery Box with random crypto!

ለምን ኤሪክ ቴን ሃግ በማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ክፍል ላይ ክርስቲያን ኤሪክሰንን ለመተካት ሜሰ | የኛ-MANCHESTER-UTD 🔴

ለምን ኤሪክ ቴን ሃግ በማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ክፍል ላይ ክርስቲያን ኤሪክሰንን ለመተካት ሜሰን ማውንትን መረጠ

ማንችስተር ዩናይትዶች የኤሪክ ቴንሀግ አማካይ ክፍልን ለማደስ ከቼልሲው ሜሰን ማውንት ጋር በግል ስምምነት ላይ ደርሰዋል ማውንት በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የዩናይትድ ተጫዋች ሊሆን ይችላል ክርስቲያን ኤሪክሰን ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከአብዛኞቹ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች በበለጠ ግልጋሎት ሰቷል

ኤሪክሰን በጥር ወር የቁርጭምጭሚት ጉዳት አጋጥሞታል ይህም እስከ ኤፕሪል ድረስ ከሜዳ እንዲርቅ አስገድዶታል ነገር ግን ከጉዳት ሲመለስ ያሳየው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በዝውውር መስኮቱ ዩናይትድ አዲስ ወጣት አማካኝ ማስፈረም ቅድሚያ የሚሰጠው ለምን እንደሆነ አሳይቷል

ምንም እንኳን የ31 አመቱ ተጫዋች ስኬታማ ፈራሚ ቢሆንም በቅርብ ጊዜ የተዳከመ መስሏል
ኤሪክሰን ለ90 ደቂቃ ያህል ተጭኖ መጫወት አይችልም በኤፍኤ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ተቀያሪ ተጨዋች መሆኑ ምንም አያስደንቅም ኤሪክሰን 2023 ከገባ በኋላ በፕሪምየር ሊጉ 13 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ ሲሆን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር ሙሉ 90 ደቂቃ መጫወት የቻለው እሱም በጥር ወር ከአርሰናል ጋር ነገር በሊጉ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በአራት አጋጣሚዎች ብቻ ከ80 ደቂቃ በላይ የተጫወተው

በኤሪክሰን ጉዳይ ሊረዱት የሚችሉ የአካል ውሱንነቶችን በሚገነዘበው ቴንሀግ በጥንቃቄ ነው ተጨዋቹን እያየዘው ያለው ይህ ሰው ከሁለት አመት በፊት የልብ ህመም ካጋጠመው በኋላ እግር ኳስ መጫወት ለመቀጠል ያለውን እድል በተአምር ነበር ያስቀጠለው ኤሪክ ኤሪክሰንን በነጻ ዝውውር ለማስፈረም መወሰኑ አስደናቂ ነበር በዚህ አመት ባሳየው ብቃት ይህንን ፊርማ ማድነቅ ተገቢ ሲሆን ነገርግን በ2023/24 የውድድር አመት ላይ ግን ኤሪክሰን ጨዋታዎችን ጀማሪ ለመሆን ብቁ እንደማይሆን ግልፅ ነው

ዩናይትዶች ከቼልሲው አማካኝ ሜሰን ማውንት ጋር በግል ውል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የኤሪክሰንን ሚናም ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል አንዳንድ ደጋፊዎቸ በማውንት ላይ ጥርጣሬ አለባቸው ነገር ግን እሱ አብሮዋቸው ለሰራቸው አሰልጣኞች ቁልፍ ተጫዋች ነበር እና አዲስ የተሾመው ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በስታምፎርድ ብሪጅ ቢይዘው እንደሚመርጥ ተነግሯል ነገር ግን ተጨዋቹ ክለቡን መልቀቅ ነው ምርጫው

የማውንት የመከላከል ስራ ጥሩ ነው ቴንሀግ በአማካይ ክፍሉ ብዙ ጉልበትን ይፈልጋል ይህንንም ማውንት ይሰጣል የ24 አመቱ ኮከብ ለቡድኑ ተለዋዋጭነትን ያመጣል የእሱን ቁጥሮች ከኤሪክሰን ጋር በፕሪምየር ሊግ ማነጻጸር አስደሳች ነው ማውንት ለካሴሚሮ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፍፁም ተጣማሪ ሊሆን ይችላል እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወደ መስመር አጥቂ አውጥተህ ማጫወት ትችላለህ እንዲሁም ብሩኖን እየተካ በ10 ቁጥር ሚና መጫወት ይችላል

ይልቁንም አበረታቹ ነገር ባለፉት አመታት በእያንዳንዱ የቁጥሮች መለኪያ ማውንት ከኤሪክሰን ይበልጣል ዩናይትዶች የኮብሃምን ምሩቅ ፍላጎት ማሳየት ለዛ ትክክለኛ ምክንያት ነው ማውንት ሁለገብ የመሀል ሜዳ ተሰጥኦ ያለው እና በቴንሀግ ወደ ትልቅ ደረጃ ሊደርስ ይችላል።

COME ON UNITED
        #GGMU #MUEF

ቲክቶክ  ላይ የኛ Manutd ላይ ፎሎ አርጉን

በተስማሚ ዜናዎቻችና  ጣፋጭ ቪድዮቻች ይዝናኑልን
የሊንኩን ማስፈንጠሪ በመጫን ይቀላቀሉን

http://tiktok.com/@the_red_forever_mv