Get Mystery Box with random crypto!

ሚሥጢሩ(The Secret)

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_law_of_attraction1 — ሚሥጢሩ(The Secret)
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_law_of_attraction1 — ሚሥጢሩ(The Secret)
የሰርጥ አድራሻ: @the_law_of_attraction1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 482
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ በመልካም አስተሳሰባቸው ራዕያቸውን፣ሕልማቸውን እንዴት ማወቅ እንደሚችሉ እንዲሁም የአእምሮኣችንን ሚስጢራዊ ክፍል የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎችን የራዕይ ጉዞዋቸውን እናቀርባለን።የማማከር እና የማሰልጠን አገሎግሎትም በ @Abresh129 ( 0961252565 ) ላይ በኦድዮ፣በቪዲዮ እንዲሁም በጽሑፍ ይቀርባሉ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-03 06:49:02
የምትሰሙትን ሰው ለይታችሁ እወቁ!

አጭርና ግልጽ ምክር፡- ውጤቱን አብሯች በማይሸከም ሰው ወሬ፣ ግፊትና አጉል ምክር ምክንያት አንድን ውሳኔ አትወስኑ፡፡

ከፋም ለማም፣ ሞላም ጎደለም፣ ተሳካም አልተሳካም ውጤቱን እናንተው የምትሸከሙትን የግል ውሳኔያችሁን መወሰን ያለባችሁ እናንተው ናችሁ፡፡

በተለይም የሕይወታችሁን አቅጣጫ እስከወዲያኛው የሚለውጥን ምርጫና ውሳኔ ስታደርጉ የማን ሃሳብና ምክር በሕይወታችሁ ስፍራ ሊያገኝ እንደሚገባው በሚገባ ለይታችሁ እወቁ፡፡ ምንም እንኳን ግራ በገባችሁ ጉዳይ ላይ መካሪ የመፈለጋችሁ ሁኔታ ትክክለኛ ሂደት ቢሆንም፣ ለምን አይነት ሰው ወሬና ግፊት ምላሽ ልትሰጡ እንደሚገባችሁ ግን ራሳችሁ ካላወቃችሁበት በኋላ የምትጸጸቱበትን አቅጣጫ ከመከተል አታመልጡም፡፡

ፍክት ያለ ቀን ይሁንላችሁ
@Abresh129
@the_law_of_attraction1
101 viewsedited  03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 15:58:07 Watch "Gradutation" on YouTube




@the_law_of_attraction1
211 viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 10:32:26 ሶስቱ “ማንነቶቼ”
(“የማንነትህ መለኪያ” ከተሰኘው የደ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ከስነ-ልቦና እይታ አንጻር ሶስት አይነት ማንነት እንዳሉን ማሰብ እንችላለን፡-

1. ራሴ “እንዲህ ነኝ” ብዬ የማስበው

እኔ በራሴ ላይ ያለኝ ተጽእኖ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህ ከሆነበት ምክንያቶች ዋነኛው ብዙውን ጊዜ ከራሴ ጋር ስለማሳልፍና ብዙ ነገሮችን ለራሴ የመናገር እድሉ ስላለኝ ነው፡፡ ይህ ልቀይረውና ሌላ አማራጭ ልፈልግለት የማልችለው እውነታ በመሆኑ በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ራሴው በእኔው ላይ ከለጠፍኩበት ዋጋ አልፎ በመዝለቅ ወደ ትክክለኛው መስመር እስከሚገባ ድረስ ትክክለኛ መለኪያን እንዳላዳበርኩ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የሰውነቴ ዋጋ የማይለዋወጥ እንደሆነና እኔው በፈቃዴ ግን የተለያዩ የዋጋ ተመኖች እንዲለጠፉብኝ መፍቀድ እንደምችል ማስታወስ የግድ ነው፡፡

2. ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሚነግሩኝ

ሰዎች ካለማቋረጥ መልእክትን ወደ እኛ ይልካሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቃል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሁኔታ፡፡ በተለይም የመደብ ልዩነት ከባህሉ ጋር ተገምዶ በሚገኝበት እንደኛው አይነት ማሕበረሰብ ውስጥ ጀርባችንን፣ የወቅቱ ሁኔታችንን፣ ያለንና የሌለንን በመደመርና በመቀነስ ካለማቋረጥ ማንነታችን ላይ ተመን ይለጥፋሉ፡፡ ይህ ዋጋ ደግሞ አንዴ ከፍ ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ይላል፡፡ ይህንን ሁኔታ በተገቢው ሚዛናዊነት የማስተናገዱ ግዴታ እኔው ላይ ነው ያለው፡፡ ሰዎች በእኔ ላይ የሚለጣጥፉት የዋጋ ውጣ ውረድ በማንነቴ ላይ ተጽእኖ የሚያመጣው እኔው ራሴ ስፈቅድለት ብቻ እንደሆነ ማስታወስ የግድ ነው፡፡

3. እውነተኛውና ትክክለኛው ማንነቴ

እውነተኛው ማንነቴ ማለት እኔው በራሴ ላይ ወይም ደግሞ ሌሎች ሰዎች የለጠፉብኝ ተመን (Price) ሳይሆን ሰው በመሆኔ ከፈጣሪ የተሰጠኝ ዋጋ (Value) ነው፡፡ ይህ የመጨረሻ ስልጣን ያለውና ሁሉንም ትቼ ላምነው፣ ላሰላስለውና ልለማመደው የሚገባኝ እውነት ነው፡፡ ይህ የማንነቴ ዋጋ በምንም ሁኔታ ሊቀንስም ሆነ ሊጨምር አይችልም፡፡ ይህንን ዋጋ በጥረቴ ልጨምረውም ሆነ ላሳድገው አልችልም፡፡ ለዚያ ሊቀነስም ሆነ ሊጨመር ለማይችለው ከፈጣሪዬ ለተቀበልኩት የከበረ ዋጋ ላለው ማንነቴ የሚመጥን አመለካከትና የኑሮ ዘይቤ የመከተሌ ሁኔታ ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡

እንግዲህ አንድ ሰው በራሱ ማንነት ላይ ያለው ዋጋ የተዛባ መሆኑን ለማወቅ ካሉን መመዘኛዎች መካከል አንዱ በችግሮቹ ላይ ያለውን አመለካከት በማጤን ነው፡፡ የተቃኘና ትክክለኛ ራስ-በራስ ምልከታ ያለው ሰው እለት በእለት በሚገጥመው ችግሩ ላይ ያለውም ምልከታ ሚዛናዊና አዎንታዊ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ችግር ሲገጥመው የወደቀ አመለካከት ያለው ሰው በቅድሚያ በራሱ ላይ ያለው አመለካከት አለመስተካከሉን አመልካች ነው፡፡

የኑሯችሁ ሁኔታ በተለዋወጠ ቁጥር በማንነታችሁ ላይ ያለችሁን አመለካከትና ለራሳችሁ የምትሰጡትን ግምት አትለዋውጡ፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፉም የማንነታችሁ ዋጋ ያው ነው!

ድንቅ ቀን ተመኘሁላችሁ

@Abresh129
@the_law_of_attraction1
255 views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 10:30:49
200 views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 17:22:51 https://t.me/the_law_of_attraction1
284 views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 17:18:55
መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ!

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መኖራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እሞታለሁ በሚልፍ ፍርሃት ታስራችሁ ከምትኖሩ ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይመረጣል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መነገዳችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እከስራለሁ በሚል በፍርሃት ታስራችሁ ከምትነግዱ በአዎንታዊነት ተነቃቅታችሁ በትነግዱ ይሻላል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መማራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ፈተና እወድቃለሁ በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምትማሩ እችለዋለሁ በሚል እምነትና ትጋት ብትማሩ የላቀ ነው፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም አንድን ሰው ማፍቀራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ይገፉኛል በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምታፈቅሩ ጤናማ በራስ መተማመን ይዛችሁ ብታፈቅሩ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ! ቀና ብላችሁ መኖር ስትጀምሩ ደግሞ መፍራት ታቆማላችሁ!

ቀና ብላች ኑሩ እንጂ አትፍሩ!

@Abresh129
@the_law_of_attraction1
272 viewsedited  14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 22:52:37
የአሊባባ ኩባንያ መስራች የሆነው ጃክ ማ አነቃቂ ንግግሮች...

"እኛ የገንዘብ እጥረት የለብንም፡፡ እኛ ያለብን እጥረት ለህልሙ የሚሞት ባለ ራዕይ ነው።"

" አለማችንን መለወጥ ከፈለግን በቅድሚያ እራሳችንን መለወጥ ይገባናል፡፡"

"ከሁሉም ነገር በላይ ሊኖርህ የሚገባ ነገር ቢኖር ትዕግስት ነው፡፡"

"ተስፋ መቁረጥ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ምክንያቱም ተስፋ ካልቆረጥክ አሸናፊ ልትሆን የምትችልበት እድል ሊኖርህ ይችላል፡፡"

"ከተቀናቃኞችህ ልትማር ይገባል፡፡ ነገር ግን መኮረጅ ፍፁም የለብህም፤ ኮርጅና መጨረሻህ ይሆናል!፡፡

"በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስኬታማ መሆን ከፈለክ፤ ሌሎችን ልታነቃቃ ይገባሃል፤ ሌሎች ከአንተ የተሻሉ ሰዎች እንዳሉም ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ይሄን ማድረግ ከቻልክ ስኬታማ መሆን ትችላለህ፡፡"

"ስለ ተቀናቃኖችህ ማሰቡን አቁም፡፡ ስኬታማ መሆን ከፈለክ ትኩረትህን ደንበኞችህ ላይ ብቻ አድርግ፡፡"

"የእኔ ስራ በርካታ ሰዎች ስራ እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡"

"ሁሉም ሰው ህልም ሊኖረው ይገባል፡፡"

@Abresh129
@the_law_of_attraction1
277 viewsedited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 08:56:54
286 views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 07:46:17
#አዲስአበባ የአልፋ ሁለተኛው ቅርንጫፍ በመገባደድ ላይ ይገኛል። ማነው እዚህ ውስጥ ለመሰልጠን የቆልረጠ?


@Abresh129
0961252565 contact me for full information
285 viewsedited  04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 07:45:48
የኃያል ሂደት ስልጠና
253 views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ