Get Mystery Box with random crypto!

ተጠቃሚዎች ለምን የቴሌግራም ማስታወቂያዎችን መፍራት የለባቸውም ፓቬል ዱሮቭ የቴሌግራም ማስታወቂ | Telegram Info አማርኛ

ተጠቃሚዎች ለምን የቴሌግራም ማስታወቂያዎችን መፍራት የለባቸውም

ፓቬል ዱሮቭ የቴሌግራም ማስታወቂያ እንዴት እንደሚሰራ ተናገረ

1. በቻት ሩም ወይም አንድ ለአንድ - personal chat እና ግሩፕ ውስጥ ማስታወቂያዎች አይኖሩም፡፡ እንደ @durov ባሉ ትላልቅ አንድ ለብዙ ቻናሎች ውስጥ ብቻ ነው የሚኖረው፡፡ ቴሌግራምን እንደ ማህበራዊ አውታር ሳይሆን እንደ መልእክት መለዋወጫ ብቻ የሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያዎችን በጭራሽ አያዩም ፡፡

2. ተጠቃሚ አያነጣጥርም ማለትም የተጠቃሚ መረጃዎች በመውሰድ የቱ ማስታወቂያ ለየትኛው ተጠቃሚ መታየት እንዳለበት አይወስንም።

3. ይህ ቀድሞውኑ ባለው የቴሌግራም ማስታወቂያ ላይ እንደ ማሻሻያ ነው ፡፡ የይዘት ፈጣሪዎች (content creators) ቀድሞውኑ ማስታወቂያዎችን እየተጠቀሙ ነው። ለተጠቃሚዎች አሉታዊ ተሞክሮ የሚፈጥሩ ጣልቃ ገብ ማስታወቂያዎችን የሚያስተዋውቁ ብዙ የሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ቦታዎች ብዙ ጊዜ የተዘበራረቁ የገበያ ቦታ ይሆናሉ፡፡ ቴሌግራም ይህንን ሁኔታ ለቻናል ባለቤቶች በግላዊነት (privacy) ላይ ያተኮረ አማራጭን በመስጠት ያስተካከላል ፡፡

ተጠቃሚዎች ከማስታወቂያ መርጠው መውጣት ይችላሉ ፣ ግን እንደ ፓቬል ዱሮቭ ገለፃ በግላዊነት ላይ ትኩረት በማድረግ ማስታወቂያ ለቻናል ባለቤቶች መፍጠር ጥሩ መንገድ ነው።

«ዋናው ግባችን በፋይናንስ የተቋቋሙ ፣ ዘላቂ የሆኑ እና ለተከታዮቻቸው በተሻለ ሁኔታ የሚሠራውን ስትራቴጂ የመምረጥ ነፃነት ያላቸው የይዘት ፈጣሪዎችን (content creators) መፍጠር ነው። ባህላዊ ማህበራዊ ግንኙነቶች ከመጠን በላይ የመረጃ አሰባሰብ እና የማታለያ ስልተ ቀመሮችን በመጠቀም ተጠቃሚዎችን እና አሳታሚዎችን ለረጅም ጊዜ ሲበዘብዙ ቆይተዋል። » - ፓቬል ዱሮቭ