Get Mystery Box with random crypto!

Telegram Info አማርኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tginfoam — Telegram Info አማርኛ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tginfoam — Telegram Info አማርኛ
የሰርጥ አድራሻ: @tginfoam
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የ @tginfoen የአማርኛ ግልባጭ ነው።
የመወያያ ግሩፕ: @tginfoamchat
ለ Beta መረጃዎች: @betainfoam
ያነጋግሩን: @infowritebot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-04 21:22:11 ቴሌግራም የiOS ውድድር እያዘጋጀ ነው።

በዚህ ሳምንት ቴሌግራም ለiOS ሶፍትዌር ዴቨለፐሮች 50,000 ዶላር ሽልማት ያለው ውድድር ያስታውቃል።

እንደ ተገለፀው ከሆነ የዚህ ውድድር አሸናፊው የቴሌግራም ቡድንን  የመቀላቀል እድልም አለው።

#ውድድር
9 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 12:50:03 ከእንግሊዝኛው ቻናል @tginfoen ልጥፎችን ወደ አማርኛ ለመተርጎም ፈቃደኛ ሠራተኞችን እንፈልጋለን። እርስዎ ወይም ጓደኞችዎ እና የሚያውቋቸው ሰዎች ሊረዱዎት ከቻሉ - ለ@infowritebot ይፃፉ እና ወዳጃዊ ዓለም አቀፍ ቡድናችንን ይቀላቀሉ።
24 views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 22:51:53 በዓለም አቀፍ የቴሌግራም የመረጃ ሰርጦች ውስጥ እገዛ ያስፈልጋል

ለ 8 ወሮች ፣ ተርጓሚዎች ቴሌግራም መረጃን ከ3ዐ በላይ ወደሆኑ ቋንቋዎች ማስፋፋት ላይ በንቃት ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡ ይህ ሊሳካ የቻለው ስለ ቴሌግራም የሚወጡ ዜናዎችን ወደ ሀገራቸው ቋንቋ በሚተረጉሙ በጎ ፍቃደኞች አማካኝነት ነው።ለዚህም እናመሰግናለን፡፡

ሆኖም፣ አንዳንድ ሰርጦች (Channels) ተጨማሪ ተርጓሚዎች ያስፈልጋቸዋል፦

አማርኛ ፦

@tginfoam እና @betainfoam
ህንድኛ
@tginfohi እና @betainfohi
Karakalpak ፦
@tginfokaa እና @betainfokaa
ማላይኛ ፦
@tginfoms እና @betainfoms
ማላያላምኛ ፦
@tginfoml እና @betainfoml
ሮማኒያኛ ፦
@tginforo እና @betainforo
ቀለል ያለ ቻይንኛ ፦
@tginfocn እና @betainfocn

ወደ እነዚህ ቋንቋዎች በመተርጎም እኛን ለመርዳት ከፈለጉ ወይም አዲስ ቋንቋ ለማቅረብ ዝግጁ ከሆኑ በግብረመልስ መስጫ bot @infowritebot ውስጥ ስለእርስዎ ያሳውቁን።

@Tginfoworld ላይ የሁሉንም ቋንቋዎች ዝርዝር ማየት ይችላሉ።
312 views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 10:16:20
የክልሎች የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ስርጭት

ቴሌግራም በፋይናንስ ሪፖርታቸው ላይ የተጠቃሚ ስርጭትን በክልል አቅርቧል

መረጃው:
• እስያ - 38%
• አውሮፓ - 26%
• መካከለኛው ምስራቅ - 17%
• ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ - 12%
• አፍሪካ - 7%

በፊት ከፓቬል ዱሮቭ በተገኘ መረጃ መሠረት ከቴሌግራም ተጠቃሚዎች 11% ከሕንድ እና 7% ከሩሲያ ነው።

#ስታቲስቲክስ
367 views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-19 17:04:55
በክለባውስ ፓቬል ዱሮቭ የለም

ባለፉት ጥቂት ቀናት ደንበኞቻችን በክለባውስ ውስጥ ያለው የ @durov መለያ በእውነቱ የፓቬል ዱሮቭ ነው ብለው ጠይቀውን ነበር፡፡

ለዱሮቭ ቅርብ በሆነ አንድ መረጃ መሠረት ፓቬል በክለባውስ ውስጥ መለያ የለውም፡፡
298 views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 19:05:49 Telegram Info ዓለምን እየተቆጣጠረ ነው

ልክ በ 10 ቀናት ውስጥ Telegram Info 20 አዳዲስ አካባቢያዊ ቻናሎችን ከፈቷል ፡፡ አሁን @tginfo ከ 30 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል ፡፡ በመላው ዓለም የእኛ ፈቃደኛ የሆኑት አንባቢዎቻችን ይህ ለእርስዎ ምስጋና ሊሆን ይችላል።

አስደሳች ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ ቻናሎቻችን አሉ ፡፡

ቻይንኛ
@tginfocn - @betainfocn
ጀርመንኛ
@tginfoger - @betainfoger
ጣልያንኛ
@tginfoita - @betainfoita
ፋርስኛ
@tginfoper - @betainfoper
ፖርቱጋልኛ
@tginfobr - @betainfobr
ስፓኒሽ
@tginfoesp - @betainfoes

ሁሉም 30+ ቻናሎች በ @tginfoworld ይገኛሉ ፡፡

እንደ በጎ ፈቃደኝነት በመቀላቀል እኛን ለመርዳት ከተነሳሱ @infowritebot ይጻፉ።
239 viewsedited  16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 18:58:01 ቀጣዩ የቴሌግራም ዝመና

በቴሌግራም ሎካላይዜሽን መድረክ ላይ በአዳዲስ ቃላት ምክንያት በሚቀጥለው የቴሌግራም ዝመና ላይ ለ iOS መተግበሪያ ስለ አንዳንድ አዳዲስ ባህሪዎች መረጃ ታየ ፡፡

ምን ምን አዲስ ነገር አለ:
- የብሮድካስት ውይይቶች (አስተዳዳሪዎች ብቻ ሊጽፉ ይችላሉ ፣ ያልተገደበ ተሳታፊዎች) ፣ ለምሳሌ @broadcastchat
- በውይይት ውስጥ በሰዓት ቆጣሪ ላይ ራስ-የሚያጠፉ መልዕክቶች- @fastestchat
- የፕሮፋይል ፎቶን ወይም የፕሮፋይል ቪዲዮን ሪፖርት የማድረግ ችሎታ
- ለእያንዳንዱ ውይይት ተለዋዋጭ የማሳወቂያ የድምፅ ቅንብሮች
- ጊዜያዊ የግብዣ ሊንኮች ፣ የ QR ኮድ መፍጠርያ
- የ iOS መተግበሪያ ዊጀቶች

ሁሉም የተዘረዘሩት ባህሪዎች በቀጣዩ ዝመና ላይ በ Android መተግበሪያ ውስጥም ይታያሉ።
163 views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 02:01:07 ቴሌግራም ዴስክቶፕ ወደ stable 2.5.9 ስሪት ዘምኗል

ምን አዲስ ነገር አለ:

– ለመልእክት መልስ (reply) ለመምረጥ ሆትኪ Ctrl + Up / Down አሁን በአስተያየት መስጫ ውስጥም ይሠራል
- ብዙ የዘገዩ መልዕክቶችን የመላክያ ጊዜ የመቀየር ችሎታ (ቢበዛ 20)
- ሁሉንም .webp ፋይሎችን እንደ ተለጣፊዎች (sticker) ያሳያል (በፋይል ማሳያዎች ላይ እንደ ፎቶ ከማሳየት ችሎታ ጋር)
- በቻናሎች ውስጥ ልጥፎችን (ፖስቶችን) ያለ ማሳወቂያ ለመላክ አዝራሩን ለመቀየር የታከለ አኒሜሽን ታክሏል
- በድምጽ ውይይት ውስጥ የአባልን የድምፅ መጠን በአስተዳዳሪ መለወጥ ለሁሉም ሰው ይለውጣል
- የመልእክት ይዘቶን ሲያወጡ error 400: LOCATION_NOT_AVAILABLE ችግርን ማስቀረት መቻል
- ለአዳዲስ የግብዣ አገናኞች ማካተት
- ‘Invite via link’ ቁልፍን ወደ Add members መጨመር
- አሁን ፒዲኤፎች እንደ ፋይሎች ብቻ ይላካሉ
- የተላከ ሚዲያ መለወጥ አሁን በአስተያየት መስጫ ውስጥም ይሠራል
- ለሁሉም ወጪ አገልግሎት መልዕክቶች (service messages) ማረጋገጫ መስጠት
- በዊንዶውስ 10 ላይ በታብሌት ሞድ ውስጥ የዊንዶው መጠን ተስተካክሏል
- በቻናሎች ላይ የተወሰኑ የቪዲዮ መልዕክቶች ማሳያዎች ተስተካክሏል
- አስተዳዳሪዎችን በመደበኛ ግሩፕ ላይ ለባለቤቱ ማከል እና ማስወገድ አለመቻል ተስተካክሏል
- ጥቃቅን ለውጦች እና ማሻሻያዎች

ከ ዋናው ዌብሳይት ወይም ከ GitHub ያውርዱ.

#ወቅታዊ #ዴስክቶፕ #stable
117 views23:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 16:36:31 የመጀመሪያው ዙር የ Android ገንቢዎች ውድድር ተሳታፊዎች ስራዎች በውድድሩ ዋናው ድረገፅ ላይ ታይተዋል ፡፡

ዳኞቹ የውድድሩን ውጤት ለማሳተም በዝግጅት ላይ እያሉ የቀረቡትን ስራዎች በ ውድድሩ ድረገፅ ላይ ማየት ይችላሉ ፡፡

ለመመልከት አንድ ተሳታፊ ይምረጡ እና “DOWNLOAD .APK” ቁልፍን ይጫኑ።

መተግበሪያዎቹ በሶስተኛ ወገን ገንቢዎች የተፈጠሩ በመሆናቸው የራስዎን መለያ መጠቀሙ አይመከርም

#ውድድር
82 viewsedited  13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-11 18:20:57 ተጠቃሚዎች ለምን የቴሌግራም ማስታወቂያዎችን መፍራት የለባቸውም

ፓቬል ዱሮቭ የቴሌግራም ማስታወቂያ እንዴት እንደሚሰራ ተናገረ

1. በቻት ሩም ወይም አንድ ለአንድ - personal chat እና ግሩፕ ውስጥ ማስታወቂያዎች አይኖሩም፡፡ እንደ @durov ባሉ ትላልቅ አንድ ለብዙ ቻናሎች ውስጥ ብቻ ነው የሚኖረው፡፡ ቴሌግራምን እንደ ማህበራዊ አውታር ሳይሆን እንደ መልእክት መለዋወጫ ብቻ የሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያዎችን በጭራሽ አያዩም ፡፡

2. ተጠቃሚ አያነጣጥርም ማለትም የተጠቃሚ መረጃዎች በመውሰድ የቱ ማስታወቂያ ለየትኛው ተጠቃሚ መታየት እንዳለበት አይወስንም።

3. ይህ ቀድሞውኑ ባለው የቴሌግራም ማስታወቂያ ላይ እንደ ማሻሻያ ነው ፡፡ የይዘት ፈጣሪዎች (content creators) ቀድሞውኑ ማስታወቂያዎችን እየተጠቀሙ ነው። ለተጠቃሚዎች አሉታዊ ተሞክሮ የሚፈጥሩ ጣልቃ ገብ ማስታወቂያዎችን የሚያስተዋውቁ ብዙ የሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ቦታዎች ብዙ ጊዜ የተዘበራረቁ የገበያ ቦታ ይሆናሉ፡፡ ቴሌግራም ይህንን ሁኔታ ለቻናል ባለቤቶች በግላዊነት (privacy) ላይ ያተኮረ አማራጭን በመስጠት ያስተካከላል ፡፡

ተጠቃሚዎች ከማስታወቂያ መርጠው መውጣት ይችላሉ ፣ ግን እንደ ፓቬል ዱሮቭ ገለፃ በግላዊነት ላይ ትኩረት በማድረግ ማስታወቂያ ለቻናል ባለቤቶች መፍጠር ጥሩ መንገድ ነው።

«ዋናው ግባችን በፋይናንስ የተቋቋሙ ፣ ዘላቂ የሆኑ እና ለተከታዮቻቸው በተሻለ ሁኔታ የሚሠራውን ስትራቴጂ የመምረጥ ነፃነት ያላቸው የይዘት ፈጣሪዎችን (content creators) መፍጠር ነው። ባህላዊ ማህበራዊ ግንኙነቶች ከመጠን በላይ የመረጃ አሰባሰብ እና የማታለያ ስልተ ቀመሮችን በመጠቀም ተጠቃሚዎችን እና አሳታሚዎችን ለረጅም ጊዜ ሲበዘብዙ ቆይተዋል። » - ፓቬል ዱሮቭ
105 viewsedited  15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ