Get Mystery Box with random crypto!

ቴሌግራም ዴስክቶፕ ወደ stable 2.5.9 ስሪት ዘምኗል ምን አዲስ ነገር አለ: – ለመልእክት | Telegram Info አማርኛ

ቴሌግራም ዴስክቶፕ ወደ stable 2.5.9 ስሪት ዘምኗል

ምን አዲስ ነገር አለ:

– ለመልእክት መልስ (reply) ለመምረጥ ሆትኪ Ctrl + Up / Down አሁን በአስተያየት መስጫ ውስጥም ይሠራል
- ብዙ የዘገዩ መልዕክቶችን የመላክያ ጊዜ የመቀየር ችሎታ (ቢበዛ 20)
- ሁሉንም .webp ፋይሎችን እንደ ተለጣፊዎች (sticker) ያሳያል (በፋይል ማሳያዎች ላይ እንደ ፎቶ ከማሳየት ችሎታ ጋር)
- በቻናሎች ውስጥ ልጥፎችን (ፖስቶችን) ያለ ማሳወቂያ ለመላክ አዝራሩን ለመቀየር የታከለ አኒሜሽን ታክሏል
- በድምጽ ውይይት ውስጥ የአባልን የድምፅ መጠን በአስተዳዳሪ መለወጥ ለሁሉም ሰው ይለውጣል
- የመልእክት ይዘቶን ሲያወጡ error 400: LOCATION_NOT_AVAILABLE ችግርን ማስቀረት መቻል
- ለአዳዲስ የግብዣ አገናኞች ማካተት
- ‘Invite via link’ ቁልፍን ወደ Add members መጨመር
- አሁን ፒዲኤፎች እንደ ፋይሎች ብቻ ይላካሉ
- የተላከ ሚዲያ መለወጥ አሁን በአስተያየት መስጫ ውስጥም ይሠራል
- ለሁሉም ወጪ አገልግሎት መልዕክቶች (service messages) ማረጋገጫ መስጠት
- በዊንዶውስ 10 ላይ በታብሌት ሞድ ውስጥ የዊንዶው መጠን ተስተካክሏል
- በቻናሎች ላይ የተወሰኑ የቪዲዮ መልዕክቶች ማሳያዎች ተስተካክሏል
- አስተዳዳሪዎችን በመደበኛ ግሩፕ ላይ ለባለቤቱ ማከል እና ማስወገድ አለመቻል ተስተካክሏል
- ጥቃቅን ለውጦች እና ማሻሻያዎች

ከ ዋናው ዌብሳይት ወይም ከ GitHub ያውርዱ.

#ወቅታዊ #ዴስክቶፕ #stable