Get Mystery Box with random crypto!

ጥቆማ https://t.me/tghamzs በላጭ የሆነው የዓረፋ ቀን እና ከሳምንት ቀናቶች | hamza redi official

ጥቆማ

https://t.me/tghamzs

በላጭ የሆነው የዓረፋ ቀን እና ከሳምንት ቀናቶች ሁሉ በላጭ የሆነው ዕለተ ጁሙዓ በአንድ ቀን አብረው ይውላሉ ይህ ምን አልባትም በሕይወታችን አንድ ጊዜ ብቻ የምናገኘው አጋጣሚ ሊሆን ይችላል።


የአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለ እነዚህ ቀናቶች ቱሩፋት ብዙ የገለፁ ቢሆንም ሁለቱም ቀናቶች ግን ለየት ባለ መልኩ የሚያመሳስላቸው አንድ ትልቅ ነጥብ አለ። እሱም፦

ዱዓ ተቀባይነት ሚያገኝባቸው ቀናቶች ናቸው።

ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓ እንዲህ ይላሉ፦
"خير الدعاء دعاء يوم عرفة"
"ከዱዓ ሁሉ በላጩ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን ዱዓ ነው"

ስለ ጁሙዓ ቀን ዱዓ እንዲህ ይላሉ፦

"فيه ساعة لا يوافقها عبد مسلم، وهو قائم يصلي، يسأل الله شيئًا إلا أعطاه إياه"
"በጁሙዓ ቀን ውስጥ የሆነች ሰዓት አለች በዚች ሰዓት አንድም ሙስሊም የሆነ ባሪያ ቆሞ እየሰገደ ለአላህ ምንም ነገር አይጠይቅም አላህ ያንን ነገር ቢሰጠው እንጂ"


በጣም የሚያጓጓ የሆነ ቀን ነውና ሁላችንም ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን ጭምር በማስታወስ ጣጣችን ጨራርሰን እቺ ቀን የዱንያም የአኼራም ታሪካችን ይቀየርባት ዘንዳ በዒባዳ ለየት ባለ መልኩ በዱዓ እና በፆም ተጠምደን ልናሳልፋት ይገባናል

አላህ ያድርሰን ከተጠቃሚዎችም ያድርገን
አሚን አትሉም


ግን አስበነዋል አስርቱ ቀናቶች እያለቁ መሆናቸውን በነዚህ ቀናቶች ምን ምን ስራሆችን አሳልፈናል
እስቲ ራሳችንን እንገምግም
አላህ ሆይ ጥሩ ስራዎችን ካበዙት ባሮችህ አድርገን

ለማንኛው ያለፈው አልፈዋል አሁን የተቀሩት ቀናቶች ላይ ትኩረት እንስጥ

ሁሌም እንደዚህ አይነት ከይራቶችን ምንተዋወስበትን ይህን
https://t.me/tghamzs
ቻይናል ጆይን ያድርጉ