Get Mystery Box with random crypto!

የ20ኛው ክፍለ-ዘመን ዋና አብዮተኛ ሄንሪ ፎርድ የ20ኛው ክፍለዘመን ዋና አብዮተኛ ነው። 20ኛ | Tesfaab Teshome

የ20ኛው ክፍለ-ዘመን ዋና አብዮተኛ

ሄንሪ ፎርድ የ20ኛው ክፍለዘመን ዋና አብዮተኛ ነው።

20ኛው ክፍለ-ዘመን የጎምቱ አብዮተኞች ጊዜ ነበር።
አብዮተኞች በሰው ልጅ አኗኗር ላይ ስር-ነቀል ማሻሻያ ለማምጣት የሚታገሉ ናቸው።

በ20ኛው ክፍለ-ዘመን ከተነሱት አብዮተኞች ውስጥ ሄንሪ ፎርድን የሚያክል ለውጥ ያመጣ አብዮተኛ ግን የለም። አዎ! በትክክል አንብበሃል፤ ፓትሪክ ሄንሪ ሳይሆን ሄንሪ ፎርድ ነው ያልኩት። ሄንሪ ፎርድ ባለ መኪና ኩባንያው፣ ኢንዱስትሪያሊስቱ!

ሄንሪ ፎርድ በሰው ልጅ ህይወት ላይ ከዘርፍ ዘርፍ ተዛማች ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ ብዙ ስር-ነቀል የማኔጅመንት ስትራተጂካዊ ውሳኔዎችን የወሰደ የኢንዱስትሪ አብዮተኛ ነው።

ፎርድ ጠብመንጃ ሳያነሳ፣ ሰራዊት ሳያሰልፍ የብዙ ሰዎችን ህይወት ከነበረበት ከታችኛው መደብ ወደ መካከለኛው መደብ ያሸጋገረ ኢንዱስትሪያሊስት ነው።

ካርል ማርክስ በንድፈ-ሃሳብ ቀርጾት፣ ቭላድሚር ኢልዪች ኡልያኖቭ (ሌኒን) መሬት አውርዶት ጓዶቹ ቦልሼቪኮች ያላመጡትን የሰው ልጅ የኑሮ ማሻሻያ በሰለጠነ እሳቤ ማሻሻል የቻለው ሄንሪ ፎርድ ነው።

ሄንሪ ፎርድ የአውቶሞቢል ኢንዱስትሪ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ኢንተርፕሪነር፣ ካፒታሊስት፣ ማኔጀር፣ ኢኖቬተር፣ ኢንዱስትሪያሊስትና ሥራ-መሪ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው።

እ.አ.አ. በ1908 ፎርድ በመጀመሪያ ያወጣት ሞዴል ቲ (Model T) አውቶሞቢል ዋጋዋ 850 ዶላር ብቻ ነበር። ይህ በጊዜው ከነበሩት መኪኖች ዋጋ እጅግ ቅናሽ ነበር። ፎርድ ግን በዚህ ብቻ ሳይረካ በቀጣይ የአመራረት ስርዓቱ ላይ ትልቅ ኢኖቬሽን በማድረግ በ1916 የመኪናውን ዋጋ ወደ 350 ዶላር ዝቅ አደረገው። ቀጥሎም በ1927 ዋጋውን ወደ 290 ዶላር አወረደው። Unbelievable!

ለዚህ ዋና ምክንያቱ ደግሞ፣ የአንድ መኪና ማምረቻ ጊዜን ከ80% በላይ መቀነስ በመቻሉ ነው።

ፎርድ በዚህ ብቻ ሳይቆም ሠራተኞቹ መኪና መግዛት እንዲችሉ የሰዓት ደመወዛቸውን ከእጥፍ በላይ አሳድጓል። በዚህም ደሞዛቸውን ከ2.35 ዶላር ወደ 5.00 ዶላር የሰዓት ክፍያ አሳደገው። የተለየ እሳቤ!

ሠራተኞቹ የእረፍት ጊዜ እና የመዝናኛ ጊዜ እንዲያገኙ የሥራ ሰዓታቸውን በቀን ከነበረበት 9:00 ሰዓት ወደ 8:00 ሰዓት ዝቅ አደረገው። የሥራ ቀናቸውንም በመቀነስ ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት ቀን አደረገው።

ፎርድ የዊክ-ኤንድ ሃሳብን ያመጣ ነው። ከዚያ በፊት በሳምንት 40:00 የሥራ ሰዓት አልነበረም፣ ከፍ ያለ ነበር።

ሞዴል ቲ መኪና በ290 ዶላር፣ ዊክ-ኤንድና፣ 40:00 ሰዓት የሳምንት የሥራ ሰዓት፣ 5.00 ዶላር የሰዓት ክፍያ በማምጣት ፎርድ የአዲሱን ዘመን አኗኗር ለውጦታል። Wow!

ቀደም ሲል የመኪና ባለቤትነት የሀብታሞች ጥጋብ ማሳያ ተደርጎ ይቆጠር የነበረው፣ በ1927 ከግማሽ በላይ የሚሆነው የአሜሪካ ቤተሰብ ባለመኪና መሆን ቻለ።

የአውቶሞቢል አጠቃቀም ማደግ ደግሞ ለጎማ፣ ለአስፋልት፣ ለመስታወት፣ ለብረት፣ ለነዳጅና ለሌሎች ብዙ ኩባንያዎች ማበብ ምክንያት መሆን ቻለ።

በዚህም ፎርድ ለመካከለኛ ገቢ ማህበረሰብ (Middle-Class) ለሚባለው የህብረተሰብ ክፍል መስፋፋት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። ለራሱም ከፍ ያለ ሀብት አግኝቶበታል። ባለበት ይመቸው!

ለዚህ ነው ሶሻሊዝም ድህነትን ሲያሰራጭ፣ ካፒታሊዝም ግን ሀብትን ያራባል የሚባለው።

ኢኖቬሽን ሁሌም ይለምልም!

የፎርድ ኩባንያ ወኪሎች ግን ልታናግሩኝ ይገባል።

Duce luce paca

@Tfanos