Get Mystery Box with random crypto!

☞ነሐሴ 7 በእመቤታችን ፅንሰት አመታዊ መታሰቢያዋ ቅድስት ድንግል ማርያምን ያስገኘችልን ቅድስት | የድንግል ማርያም ልጆች!♥ጥያቄና መልስ ቻናል!

☞ነሐሴ 7 በእመቤታችን ፅንሰት አመታዊ መታሰቢያዋ ቅድስት ድንግል ማርያምን ያስገኘችልን ቅድስት ሀና ማርያምን ከፍ ከፍ እናድርጋት፡፡
☞የድኅነት ብላቴና ብፅዕት ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡
☞የይቅርታ ብላቴና ብላቴና ብፅዕት ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡
☞የልዕልና ብላቴና ብፅዕት ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡
☞የጽድቅ ብላቴና ብፅዕት ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡
☞የክብር ብላቴና ብፅዕት ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡
☞ሐዳስ ጣዕዋ ለተባለች እመቤታችን እናት የሆንሽ ብፅዕት ሐና ሆይ ሰላምታ
ይገባሻል፡፡
☞ብፅዕት ሐና ሆይ ከባሕር የምታሻግሪ የሕይወት መርከብ አንቺ ነሽ እልሻለሁ፡፡
☞የዓለሙ ሁሉ መድኀኒት የምትሆኝ የማርያም እናት ቅድስት ሐና የሥጋና የደም
ፍጥረታትና የሰማይ መላዕክት ባንቺ ታደሱ፡፡
☞ቅድስት ሐና ሆይ ካማረ ከማኅሌት መጠራት ይልቅ ለስም አጠራርሽ ሰላምታ
ይገባሻል፡፡
☞ቅድስ ሐና ለአፍሽና በረዶ ለሚመስሉ ጥርሶችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ቅድስት ሐና ሆይ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ለጠባችው ለጡቶችሽ
ለአንቺ ጉንጭ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ቅድስ ሐና ሆይ ድንግል ማርያም ለተሸከመ ለሆድሽና ንጹሕ ለሆነው ለልብሽ
ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ለሐሳብሽ ምሳሌ የማይገኝለት ቅድስት ሐና ሆይ የምድር ፍጥረታትና የሰማይ
ፍጥረታት ሁሉ ባንቺ ይመካሉ ባንቺ ይደሰታሉ፡፡
☞ቅድስ ሐና ሆይ ለኅንብርትሽና ለተመረቀው ድንግል ማርያምን ለተሸከመው
ማኅፀንሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ቅድስት ሐና ሆይ በማይጠፋ የግምጃ ልብስ ለሥጋሽ መገነዝ ሰላምታ
ይገባል፡፡
☞የማርያም እናት የእየሱስ ክርስቶስ አያት ሐና ሆይ ድንገት እናንጠራ ለንሰሐ
ጥቂት አቆይኝ እንጂ ሞትስ በዓለም አይተወኝም፡፡
☞ድርሳነ ኢያቄብ ወሐና
☞07/2014 ዓ.ም