Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ እኮ ታላቅ በአል ነው #በዓለ_ጰራቅሊጦስ## ☞ሰኔ 5 እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በዓል በሰላ | የድንግል ማርያም ልጆች!♥ጥያቄና መልስ ቻናል!

ዛሬ እኮ ታላቅ በአል ነው #በዓለ_ጰራቅሊጦስ##

☞ሰኔ 5 እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

☞ቃል የግሪክ ሲሆን ትርጓሜው አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡ይህ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በሃምሳኛው በዐረገ በአሥራኛው ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡
☞ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከጠዎቱ ሦስት ላይ ነበር፡፡

☞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት በተናገረው
አምላካዊ ቃል መሠረት"ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ" ብሏቸው ነበር

ሰዓቱ ሲደርስ የሚያጽናኑበት ብርታት የሚሆናቸው የዕውቀት፤ የኃይል መንፈስ
ቅዱስ ሰደደላቸው፡፡

☞"በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው
ሳሉ ድንገት እንደሚቃጠል ዐውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ በሁሉም መንፈስ
ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሠጣቸው በሌላ ልሣኖች ይናገሩ
ጀመር"(የሐዋርያት ሥራ 2፥1-11)

☞ይህችንም ዕለት ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን በማለት ይጠሯታል፡፡