Get Mystery Box with random crypto!

#የላሟ እና የአላህን ፈሪው ልጅ ታሪክ ክፍል#2 ልጁም እናቱ እንደነገረችው | አስ–ሱናህ

#የላሟ እና የአላህን ፈሪው ልጅ ታሪክ
ክፍል#2

ልጁም እናቱ እንደነገረችው ወደ ተባለው ተራራ ሄዶ ልክ አላህን በሚጠይቅ ጊዜ ጥጃዋን እንዳየች ላም ከጫካ ውስጥ ወጥታ እየጮኸች በመምጣት ወደሱ ቀረበች ። በሚያስገርም መልኩ ያያት ሁሉ በመልኳ እንደሚደነቅና እንደ ሚፈዝ በቁርአን ውስጥ /በምዕራፍ ሁለት አንቀፅ 69 / ላይ «ለሚያያት ሁሉ የምታስደስት ናት» በሚል ተገልጻለች ።ከዚያም በሰውኛ ቋንቋ «አባትህ ለአላህ አደራ ሰጥቶኝ የሄደው እኔን ነው በጀርባዬ ወጥተ እንደ ፈረስ ጋልበኝ» ስትለው «እኔ እናቴ አላዘዘችኝም ቀንዷን በገመድ አስረ አምጣ ነው ያለችኝ» ሲላት «የእናትህን ትእዛዝ ባታከብር ኖሮ እኔም ለፈተና እንጂ ለመጋለብ አልተፈጠርኩም የትም በረሃ ለበረሃ ይዤክ እሄድ ነበር»አለችው።

ጊደሯን እየጎተተ ወደ እናቱ ጋ ይሄዳል። እንደማንኛውም ሰው ጊደሯን ጠዋት ወጥት ማታ ስትገባ የጎረቤት ሰዎች «ጊደሯ ስትወጣ እና ስትገባ አንዳንድ ጥፋት አደረሰችብን» እያሉ ሲያሰሙ እናት አላህን ፈሪ ስለነበረች ይህች ጊደር ከጎረቤት ሰው ጋር ከምታቀያይመን በእሷ የመጣ ጥቅም ይቅርብን ገበያ ወስደህ ሽጣት ስትለው። እሱም በስንት መሸጥ እንዳለበት እናቱን ሲያማክር «ላሟን ብዙ ስላልደከምንባት በአላህ ጥበቃ ስር ስለኖረች ትርፉ ይቅርብን የተገዛችበት 3 ዲናር ስለሆነ በሶስት ዲናር ሽጣት» አለችው።

ገበያ እንደወሰዳት አንድ የከብት ነጋዴ የመሰለ ሰው የጊደሯ ዋጋ ስንት ነው ብሎ ሲጠይቀው «ሶስት ዲናር »ሲል« ሞኝ ነህ እንዴ እንዴት ሶስት ዲናር ትላለህ አንተ እንደምትለው በሶስት ዲናር ብገዛት ሰው አያምነኝም ያታለልኩህ ስለሚመስላቸው በስድስት ዲናር ነው የምገዛህ» ሲለው «እኔ ሞኝ አይደለሁም እናቴ ያዘዘችኝ በ3 ዲናር እንድሸጣት ነው ከፈለክ ግዛት» ሲለው «እናትህ ሽጥ ካለችህ በላይ አተረፍክ እንጂ አልከሰርክም» ሲለው «ምን ይታወቃል ለምን ባልኩህ ዋጋ አልሸጥክም ብላ ብትቆጣኝስ» ሲል ቤቱ በአቅራቢያ ስለነበር «ሂድና እናትህን በስድስት ዲናር ልሽጣት ወይ ብለህ ጠይቃት» አለው።

እቤት ደርሶ ለእናቱን «ልሽጣት ወይ» ብሎ ሲጠይቃት ሽጣት ብላ ፈቀደችለት ። እናም ወደ ሰውዬው ተመልሶ «እናቴ ሽጣት ብላኛለች እና በስድስት ዲናር ግዛት» ሲለው። ከብት ነጋዴውም «አይ አልገዛም አስራሁለት ዲናር ነው የምገዛህ» ሲል። ነጋዴው እስኪተዋት ጣልቃ ላለመግባት የሚጠብቁ ሌሎች ሰዎች ስለነበር። ልጁ በንዴት «ለምንድን ነው ለሌላ ሰው እንዳልሸጥ የጊደሯን ዋጋ የምትዘጋብኝ ካገኘው ለሌላ እሸጣታለው» ሲለው
«አሁንም ሂድና እናትህን በ12 ዲናር ልሽጣት ወይ ብለህ አማክራት እኔ ነኝ የምገዛት እንጂ ሌላ ሰው እንዲወስዳት አልፈልግም።» አለው።

ልጅ ለሁለተኛ ጊዜ ሄዶ ለእናቱ ሲያማክራት «ምንአልባት መላኢካ እንጂ ሰው እንደዚህ አይልም እናም ተመለስና ጊደሯን መሸጤ ነው ወይስ አለመሸጤ የሚያዋጣኝ ምን የምትመክረኝ ነገር አለ ብለህ » ጠይቀው አለቸው።
እናትየው ያው እንደገመተችው ሌላ ሰው እንዳይገዛ ሊመልስ የመጣ መላኢካ ነበር።ልጅ እናቱ ያለቸውን ሲነግረው «እንግዲያውስ የምመክርህ ጊደሯን መሸጥ ያለብህ ገዢው ቤትህ ድረስ ሲመጣ ነው ።ዋጋዋም ጊደሯ ታርዳ በቆዳዋ ሙሉ ወርቅ ተሰፍሮ ነው የምትሸጠው ከዚህ በላይ እንዳትሸጥ ።በቅርብ ጊዜ መጥተው ይጠይቁሀል እና ያኔ ነው የምትሸጣት ።» ምክሩን በመቀበል ጊደሯን ይዞ ወደ ቤቱ እንደተመለሰ።

በዚያው ሰሞን በአካባቢው አንድ ክስተት ተፈጠረ ።እሱም
በአካባቢው የሚኖር ባለፀጋ ሰው ነበር ።ከአንዲት ልጅ በስተቀር ሌላ ቤተሰብ አልነበረውም ።
አንድ ምንም ዱኒያ የሌለው የወንድሙ ልጅ ነበርና አጎቱ የሚቋቋምበት ገንዘብ እንዲረዳው ፈልጎ እንዲህ ሲል ጠየቀው« አጎቴ ሆይ አንተ የተረፈክ ሀብታም ነህ ።አንተ እያለህልኝ ለምንድን ነው የምቸገረው? አንተ እያለህ ማንን ነው ምጠይቀው? የተወሰነ ገምዘብ ስጠኝና እንደሰው እራሴን ችዬ እንድኖር ልታደርገኝ ይገባል። »አጎት በጣም ስስታም ስለነበር ልጁን ሊረዳው ፍቃደኛ አልሆነም።

በዚህም ተናዶ እያለ ሰዎች እንዲ ብለው መከሩት«ልጁን በሚስትነት እንዲሰጥህ ጠይቅ ምናልባት ለልጁ ሲል ሀብትና ንብረቱን ሰጥቶ ያቋቁምህ ይሆናል» ሲሉት

አጎቴ ሴት ልጁን በሚስትነት ይስጠኝ በማለት የላካቸው ሽማግሌዎች አጎቱን ሲጠይቁለት አጎት እንዴት ደፈረኝ በማለት የላካቸውን ሽማግሌዎች ገልምጦና ሰድቦ ሲመልስበት ። ልጁ በአጎቱ ንቀት በመበሳጨት «እንዴት ገንዘብ ባይኖረኝ በስድብ ያዋርደኛል ለምን ይሄን ሰው ገድዬ ልጁቷን አላገባትም ሀብቱንም እወርሳለው በማለት ከሰይጣኑ ጋር ተማክሮ አጎቱን ለመግደል ይወስናል ።

ከዛም ወደ አጎቱ ይሄድና «ያለ አቅሜ ነው ልጅቷን የጠየቅኩህ ሰዎች ሽማግሌ ላክ ብለዉኝ ነው ይቅርታ አድርግልኝ»በማለት ይጠይቀዋል። አስከትሎም«አጎቴ እባክህ አንድ ነገር ላማክርህ እፈልጋለው አንተ ባትረዳኝ እንኳን ቢያንስ ዋስ ከሆንከኝ እንዳቋቋምከኝ ነው። አንዳንድ ሀብታሞች ከሩቅ ሀገር ሸቀጥ እያመጡ በአካባቢው ላሉ አነስተኛ ነጋዴዎች በዱቤ የሚሰጡ ስላሉ ከነሱ ጋር የዱቤ እቃ ወስጄ ልሰራ አስቢያለው እና እባክህ ተባበረኝ ። አንተ እያለህ ማንስ ዋስ ይሆነኛል» ሲለው አጎቱ እሺታውን ገለፀ።

በዚህ ሰአት ነጋዴዎችን አብረው ሄደው ለማነጋገር በምሽት ወደ ነገዴዎች መንደር እየሄዱ እያሉ ሰው በማይደርስበት ሰዋራ ስፍራ ሲደርሱ አጎቱን በስለት በመውጋት ገድሎ አስክሬኑን ጥሎ ወደ ቤቱ ይመለሳል ።የሰራውን ሰርቶ ካበቃ ቡሀላ «አጎቴ በምሽት ወጥቶ ቀረ ምን አጋጠመው ይሆን»በማለት ያስወራል በማግስቱ «ኡኡ ያገር ያለህ አጎቴ ጠፋብኝ አፋልጉኝ» ሲል ኡኡታውን የሰማው ሁሉ ሲያፈላልጉ በሰዋራ ስፍራ ተገድሎ ያገኙታል።

ገዳይ አቧራ ላይ እየተንከባለለ አጎቴን አጣሁኝ እያለ ሲያለቅስ የአካባቢው ሰዎች ባላዩት በሰፈራቸው ነው ሞቶ የተገኘው ወንጀለኛውን አምጡ ተብለው ይያዛሉ ።
«እኛ አላየንም» ቢሉም የሚሰማቸው ያጣሉ። «ከሆነም ካሳ እንክፈል እንጂ ገዳዩን ማግኘት አልቻልንም» ሲሉ ልጁ አልፈልግም የአጎቴን ገዳይ ነው የምፈልገው ካሳ አልቀበልም በማለት አስቸገረ።

በኑ እስራኤሎች ግራ ሲገባቸው ወደ ነብዩላህ ሙሳ አለሂ ሰላም ዘንድ በመሄድ«በማናቀው ነገር ተቸግረናልና መፍትሄውን ከአላህ ዘንድ ይጠይቁልን»አሏቸው።ነብዩላህ ሙሳ መልስ ያገኙላቸው ምላሽ በቁርአን ውስጥ በምዕራፍ 2 አንቀፅ 67 እስከ 73 ድረስ በቁርአን ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን ። እሱም አንዲት ላም ገዝታችሁ ጊደሯን አርዳችሁ በከፊል ስጋዋ የተገደለውን ሰው በድን ምቱት ከሞተበት ተነስቶ ማን እንደገደለው ይናገራል የሚል ነበር።

የተባለችዋን ጊደር ፈልገው እና አፈላልገው አገኟት ።ጊደሯ ከላይ የተጠቀሰው ልጅ ጊደር ነበረች።እናም በኒ እስራኤሎች እንግዛህ ብለው ሲጠይቁት አውቆ አልሸጥም ይላቸዋል። ለምን መግዛት ያለብን ያንተን ጊደር ስለሆነ ነው? ሲሉ ዋጋዋን የምትችሉት አይመስለኝም አላቸው። ስንት ነው የምትሸጣት አሉ«ዋጋዋ ጊደሯ ታርዳ ቆዳዋ እንደ ማዳበሪያ ተሰፍቶ በሙሉ ወርቅ ተሰፍሮ ነው»አላቸው «ሞኝ ነህ እንዴ በዚህ ዋጋ ማን ነው የሚገዛህ?ማንስ ሲሸጥ አይተሀል»ቢሉት «እኔ መች ግዙኝ ብዬ ለመንኳቹ ከፈለጋቹ ግዙኝ ካልፈለጋቹ ተውት »ብሎ ኮራባቸው ። እንዳይተዋትም ተቸገሩ እንዳይገዙትም ዋጋዋ ከበዳቸው ሁኔታውን ለነብዩላህ ሙሳ አለሂ ሰላም ነገሯቸው ....

ይቀጥላል....

https://t.me/tewihd/