Get Mystery Box with random crypto!

#ትምህርተ_ንስሐ_በአቡነ ሺኖዳ) @tewahido_ortho ክፍል ንስሐ ምንድነው | ✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣

#ትምህርተ_ንስሐ_በአቡነ ሺኖዳ)
@tewahido_ortho

ክፍል

ንስሐ ምንድነው

➾ ንስሐ ነስሐ ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ነው። የቃሉ ፍቺ ሐዘን ፣ ፀፀት ፣ ቁጭት ፣ ማለት ነው ። አንድ ሰው ንስሐ ገባ ሲባልም አዘነ ፣ ተፀፀተ ፣ ክፉ አመሉን ተወ ማለት ነው ። ➾ንስሐ ማለት ደግሞ አንድ ሰው በሰራው ጥፋት ባደረገው ስህተት ፣በፈፀመው ኀጢአት ማዘኑና መቆርቆሩ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኀጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው ። በአጠቃላይ ንስሐ ከፍ ብሎ የተገለጠውን ትርጉም ሲኖረው በሰዎች ህይወት ውስጥ ደግሞ የሚከተሉትን ፍችዎች ይዞ እናገኘዋለን።
➥ሀ➝ ንስሀ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ➠ኀጢአት ከእግዚአብሔር መለየት ነውና። እግዚአብሔር አምላክም በነብያት አድሮ ህዝቡ እንዲመለሱ አዟል። "ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል። እርሷንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለው። " (ሚል 3:6) በማለት ጥሪውን አስተላልፏል። በመፅሐፈ ምሳሌም "ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም ፣ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል" በማለት ተፅፏል። (ምሳ 28:13) በሉቃስ ወንጌል የምናገኘው አባካኙ ልጅ ኃጢአቱ በመረረውና በተፀፀተ ጊዜ ወደ ልቡ ሲመለስ ወደአባቱ ለመምጣት ወሰነ አባቱም በሐሴት ተቀበለው ። (ሉቃ 15:18-20) እውነተኛ ንስሀም ሰዎች በበደልና ኃጢአት ምክንያት ወደ አጡት ሥፍራ ለመመለስ የሚኖራቸው ናፍቆትና ውሳኔ ነው።
➥ለ➝ ንስሀ ከኀጢአት እንቅልፍ መንቃት ነው። ኃጢአት በመንፈሳዊ ሕይወት ማንቀላፋት ነውና ። ኀጢአተኛ ያለበትን ስፍራ የወደቀበትን ጉድጓድ አያውቀውምና በንስሐ መቀስቀስ ያስፈልገዋል ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ " በማለት የተናገረው ።
➥ሐ➝ ንስሐ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው ። ኃጢአት የነፍስ ሞት ነውና ። ቅዱስ ጳውሎስ "በኃጢአታችን ሞተን ሳለን በክርስቶስ አዳነን " ብሏል ። (ኤፌ2:5) ዳግመኛም "አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሀል " ሲል ተናግሯል ። (ኤፌ 5:10) ቅዱስ ዮሐንስም "እኛ ...ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገርን እናውቃለን " ብሏል ። (1ኛ ዮሐ 3:14) ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ "ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኀጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ" በማለት ኃጢአት የነፍስ ሞት ንስሐ ደግሞ ሕይወት መሆኑን አስተምሯል (ያዕ5:20)

➝ #ይቀጥላል

https://telegram.me/tewahido_ortho