Get Mystery Box with random crypto!

በዕፀ መስቀሉ በዕፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ የኢየሱስ ፍቅር ምንኛ ማረከኝ ከፍቅርም በላይ ሆነና | ✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣

በዕፀ መስቀሉ

በዕፀ መስቀሉ የተከፈለልኝ
የኢየሱስ ፍቅር ምንኛ ማረከኝ
ከፍቅርም በላይ ሆነና መሠጠኝ
ከመስቀል ሥር ሁኜ ፊቱን እያየሁኝ

ዓለምን በፍቅሩ ያሸነፈ ጌታ
የጸብን ማዕበል በፍቅሩ የገታ
ሕይወቴን ጸጥ አድርጎ ይምራት በምልሐቱ
እኔ ምን አለፍኝ አልደክምም በከንቱ
#አዝ
ደሙ ከወዙ ጋር ተዋሕዶ ሲወርድ
በእኔ በደል ጌታዬ ቀረብልኝ ለፍርድ
ሀጥያቴን በጫንቃዉ ተሸክሞልኛል
በደሌን ደምሥሶ ንፁሕ አድርጎኛል
#አዝ
የቀራንዮ ግፍ በአንተ ላይ የሆነዉ
ሰይጣንን ጠርቆ ከመንገድ አወጣዉ
እሾሕ አሜኬላዉ ተደምስሶልናል
የንጹሕ በግ ደም አዳምን ታድጓል
#አዝ
ይኽንን ሥጋዬን ብሉ ይላችሁዋል
ይኽንን ደሜንም ጠጡ ይላችሁዋል
ከመስቀል ሥር ሆነን ደሙን እንቀበል
ሥጋዉን እንብላ ሠዉ ሆይ ችላ አንበል

ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሀይሉ


ለወዳጅ ያጋሩ

መምህር ምህረተአብ በጅ
ይቀላቀሉ

@tewahido_ortho