Get Mystery Box with random crypto!

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedomediacenter — ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedomediacenter — ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል - Tewahedo Media Center - TMC
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedomediacenter
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.93K
የሰርጥ መግለጫ

እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ !
የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልን የቴሌግራም ቻናል
ድረ ገፃችንን - www.tewahedomediacenter.org ይጎብኙ
የዩቲዩብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:57:06
276 views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:56:53 ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በምልዓተ ሕዝብ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተገለፀ !!!


ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሀገረ አሜሪካ ሲደረግላቸው የቆየውን የሕክምና ክትትል አጠናቅቀው ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ የቅዱስነታቸው ልዩ ጽ/ቤት ከትናንት በስቲያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

የቅዱስነታቸውን ወደ ሀገር ቤት መመለስ አስመልክቶ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኗዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ልዩ ክትትል የሚደረግለት የአቀባበል ዐቢይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ነው የተገለፀው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸውን ለመቀበል በወጣው ዝርዝር መርሐግብር መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ በካህናት እና በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ደማቅ አቀባበል የሚደረግላቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዕለቱ በርካታ ካህናትና ምዕመናን በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከፍተኛ ሕዝባዊ አቀባበል የሚደረግላቸው መሆኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል።

በተያያዘ መላው ኦርቶዶክሳውያን ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት ቅዱስነታቸው እንዲቀበሉ ጥሪ ቀርቧል።

የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን

#Ethiopia 
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media
283 views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:53:12
499 views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:52:55 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐሥራ አንደኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ እየተሳተፈች ትገኛለች።

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++


ዐሥራ አንደኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ በጀመርን ሀገር ካርልስሩሄ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ስብሰባውያን ያዘጋጁት እና ጥሪውን ያስተላለፉት በአውሮፓ የሚገኙ የጀርመን ቤተ ክርስቲያን፣ ቢደን የፕሮቲስታንት ቤተ ክርስቲያን፣ የጀርመን አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ጉባኤ፣ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት እና የስዊዘርላንድ ቤተ ክርስቲያን በጋር በመሆን ነው፡፡

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ የምክር ቤቱ ከፍተኛው የውሳኔ አካል ሲሆን በየስምንት ዓመቱ ይካሄዳል፡፡ በዚህ ስብሰባ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አባል ከሆኑ ከ352 (ሦስት መቶ ሃምሳ ሁለት) አባል አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሁለት መቶ ዘጠና አምስት አባል አብያተ ክርስቲያናት በተዋካዮቻቸው የተገኙ ሲሆን፣ 800 የሚሆኑ የምክር ቤቱ የባለፈው ማእከላዊና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውች አባላት፣ ከ1484 በላይ የምክር ቤቱ ድጋፍ ሰጭና አጋር ተቋማት ተወካዮች፣ 974 የሚሆኑ የምክር ቤቱ ቢሮ ሠራተኞች፣ የአዘጋጁ ሀገር የአስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ ከ137 በላይ የሚሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላላ ጉባኤ እየተሳተፉ ያሉ ከመላው ዓለም የመጡ የቦሴ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ልዩ ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ታዛቢዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ስብሰባው በዛሬው እለት ጠዋት የዓለም አብያተ ክርስቲያት ምክር ቤት ዋና ሊቀመንበር (ሞረዴተር) ዶክተር አግናስ አቡም እንኳን ደህና መጣቸችሁ በማለት የከፈቱት ሲሆን ከርሳቸው በመቀጠል የዓለም አብያተ ክርስያናት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ንግግር አደርገዋል፡፡

በዚህ ስብሰባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ በብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ጉዳይ መመሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ አማካኝነት የማእከላዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሁናለች፤ በስብሰባው ላይ የተገኝው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ በብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ወደ ስብሰባው ያቀና ሲሆን ከኦሬንታል ኦርቶዶክስ፣ ከምሥራቅ ኦርቶዶክስና ከሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የተወከሉ ልዑካን በጉባኤው እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia 
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media
477 views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:26:59
382 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:26:00 የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም የጽንሰት በዓል ሻሸመኔ ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል ወአቡነ ሀብተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በፎቶ

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ፎቶ ፦ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media
384 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:55:16
400 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:47:34 የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም የጽንሰት በዓል በቃሉ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተ ማርያምና ቅድስት አርሴማ ገዳም በፎቶ

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ፎቶ ፦ አዲስአበባ ሀገረ ስብከት

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media
461 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 06:54:12
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ ስድስት በዚህች ዕለት ጻድቅ የሚሆኑ የአባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የጽንሰታቸው መታሰቢያ በዓል ነው !

በረከታቸው ከሁላችን ጋር ትሁን

አሜን
593 views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:28:40
703 views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ