Get Mystery Box with random crypto!

ሽሽታችሁ በክረምት .....እንዳይሆን ፅልዩ ማቴ 24÷20 ➯ እንደሚታወቀው በሀገራችን ክረምት | ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

ሽሽታችሁ በክረምት .....እንዳይሆን ፅልዩ
ማቴ 24÷20

➯ እንደሚታወቀው በሀገራችን ክረምት ተብሎ የሚጠራው "ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25" ያለውን ያጠቃልላል፤ በዚህ ወራት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን መግቦቱን ቸርነቱን በዝናብ አብቅሎ ማብላቱን ትሰብካለች፤ በተጨማሪም የዳግም ምፅአቱን ነገር አበክራ ትናገርበታለች፤ ምክንያቱም ጌታ ዳግም የሚመጣው የት ነበራችሁ ምን ሰራችሁ ብሎ መዝኖ ዋጋ ሊሰጠን ነውና፤ የፅድቅ ፋሬ አፋርተን ካልጠበቅን መጠጊያ መሸሻ አጥተን የምንጨነቅበት ቀን ነውና ተዘጋጁ ትለናለች፡፡

➯ ታዲያ ወርሃ ክረምት ከዚህ ጋር ምን አገናኝው ስንል እንደሚታወቀው ገበሬው በቤት ውስጥ ያለውን እኽል አውጥቶ ዘርቶ በመጀመርያው ቡቃያውን ለማየት ይጓጓል ቀጥሎም ቡቃያውንና ቅጠሉን እያየ ወደፊት ደግሞ አበባና ፍሬን ለማየት ወርኃ ጽጌን በተስፋ ይጠብቃል፤ በዚህ ግዜ ሽሽት ቢመጣ ለመንገድ የሚሆን ስንቅ የለውምና ከባድ ይሆንበታል ፡፡

➯ ሊቃውንት ቤተክርስቲያንም ይህን መሠረት አድርገው ቡቃያና ቅጠል እንጂ ፍሬ በማይገኝበት ክረምት ስደት አስቸጋሪ እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ፍሬ ሳናፈራ የጽድቅ ሥራ ሳንሰራ ጌታ ለፍርድ መጥቶ የት ነበራችሁ? ምን ሰራችሁ? ባለን ጊዜ ምክንያትና  ምላሽ እንዳናጣ በሃይማኖት ቁመን ትሩፋት እንድንሰራና መጨረሻየን አሳምርልኝ ፍሬ ሳላፈራ ቀኑ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ እያልን በጸሎት እንድንተጋም ያስተምረናል።

ምንጭ
ብጽእ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
ስምዐ ጽድቅ