Get Mystery Box with random crypto!

❖ ቻይ እና ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ይጸልያል ስለሚሰጠውም የእግዚአብሔር መልስ አይጨነቅም፤ እግዚአብ | ✞ ተዋሕዶ ✞ 🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴

❖ ቻይ እና ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ይጸልያል ስለሚሰጠውም የእግዚአብሔር መልስ አይጨነቅም፤ እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚሰማው እርግጠኛ ነው፤ ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ እንደሚሆን በተገቢው ጊዜና መንገድ መልስ እንደሚሰጠው በማመን ለእግዚአብሔር ፍቅር ይተዋል፤ አንዳንድ ሰዎች ይህ መሰል ትዕግሥት የላቸውም፤ እግዚአብሔርን መውቀስ እና ከእርሱ ስሕተት መፈለግ እንጂ መጠባበቅ አይችሉም፤ እርሱን ይወነጅሉታል እርሱ ግን እጅግ ይታገሳቸዋል ወቀሳቸውንም ይሸከማል፤ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደሚሰራ ማመን አለባቸው።

ምንጭ
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ