Get Mystery Box with random crypto!

ተዋህዶ አንዲት ናት😍

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahdo01 — ተዋህዶ አንዲት ናት😍
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahdo01 — ተዋህዶ አንዲት ናት😍
የሰርጥ አድራሻ: @tewahdo01
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.09K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
#ተዋህዶ_አንዲት_ናት_ቻናል
#የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርዓትን የጠበቁ #profile የሚሆኑ ምርጥ ምርጥ ፎቶችን እና አሪፍ ትምህርቶች ለማግኘት ይጎብኙን ።
ለመቀላቀል👉👉 @tewahdo01 👈👈

👇 ለጥያቄ እና አስታያየት👇
@jobabi21

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-11 10:26:46
ሥርዓተ ማኅሌት ዘታኅሣሥ በዓታ ለማርያም "ታኅሣሥ ፫"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ ሥርዓተ ነግሥ።
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ለማርያም ዘምሩ፤ ለማርያም ዘምሩ፤ መስቀሎ ለወልድ እንዘ ትጸውሩ።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤ እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ወብሥራት ለገብርኤል፤ ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

መልክዐ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤ ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክት ሰማይ ፤ እንዘ ሀሎኪ ማርያም ወመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤ ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕት ሠርክ ኅሩይ፤ ለእመ ኅፍነማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ።

ዚቅ
አንቲ ዉእቱ ንጽሕት እምንጹሐን፤ ዘነበርኪ ዉስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦር፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፤ ስቴኬኒ ስቴ ሕይወት ዉእቱ፤ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ።

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርስኪ ፆርኪ፤ እምአንስት ቡርክት አንቲ፤ ለመሠረትኪ የኃትዎ ዕንቊ ክቡር፤ አንቲ ውእቱ መንፈሳዊት ሀገር ንጽሕት ፀምር፤ ዘኃረያ ጸባኦት አማኑኤል።

ነግሥ
መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ፤ ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ፤ በረምሃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ።

ዚቅ
ፈንዊ ለነ እግዝእትነ፤ ፋኑኤልሃ መልአክኪ ሄረ፤ በሃይለ ጸሎቱ ይዕቀበነ ወትረ።

መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
ይዌድስዋ ኲሎሙ በበነገዶሙ፤ ወበበማኅበሮሙ ለቅዱሳን፤ ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ።

ወረብ
"ይዌድስዋ ኲሎሙ"/፪/ በበነገዶሙ/፪/
ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ/፪

መልክአ ማርያም
ሰላም ለልሳንኪ ሙኀዘ ኃሊብ ወመዓር፤ ዘተነብዮ ወፍቅር፤ ማርያም ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር፤ ኅብእኒ እምዓይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር፤ እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር።

ዚቅ
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ፤ ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ፤ ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ፤ ውስተ አውግረ ስኂን።

መልክአ ማርያም
ሰላም ለእመታትኪ እለ ፀንዓ ይፍትላ፤ ሜላተ ወወርቀ በናዝሬት ወበገሊላ፤ ማርያም ድንግል ለዮዲት ጥበበ ቃላ፤ ብጽሂ በሠረገላ ንትመኃል መኃላ፤ ከመ ታኅድርኒ በብሔር ዘተድላ።

ዚቅ
ገብርኤል መልአክ መጽአ፤ ወዜነዋ ጥዩቀ፤ በዕንቊ ባሕርይ እንዘ ትፈትል ወርቀ።

ወረብ
ገብርኤል መልአክ መጽአ "ወዜነዋ"/፫/ ጥዩቀ/፪/
"በዕንቊ ባሕርይ"/፫/ እንዘ ትፈትል ወርቀ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለአብራክኪ በስብሐተ ልዑል ዘአስተብረካ፤ እምአመ ወሀቡኪ ብፅአ ውስተ ኦሪታዊት ታዕካ፤ ማርያም ድንግል መንበር ዘእብነ ፔካ፤ ጊዜ ስደቶሙ ለኃጥአን እምዓጸደ ዓባይ ፍሲካ፤ ጼውውኒ መንገሌኪ እኩንኪ ምህርካ።

ዚቅ
እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር፤ አስተርዓያ መልአክ፤ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ፤ ግሩም ርእየቱ፤ ኢያውአያ እሳተ መለኮት።

ወረብ
እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር/፪/
አስተርአያ መልአክ ዘኢኮነ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ ኢኮነ/፪/

መልክአ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ።

ዚቅ
ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለወለተ ሀና፤ ህብስተ ህይወት ተጸውረ በማኅጸና፤ ጽዋዐ መድኃኒት፤ ዘአልቦ ነውር ወኢሙስና፤ እፎ አግመረቶ ንስቲት ደመና፤ ኢያውአያ በነበልባሉ፤ ወኢያደንገጻ በቃሉ፤ አላ ባሕቱ ትብራህ፤ ረሰያ ዘበጸዳሉ ፤ይዜኑ ብሥራተ፤ መልአኮ ፈነወ፤ ዮም ተሠርገወ በከመ ተዜነወ።

ማኅሌተ ጽጌ
የኃዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦዕኪ እንዘ ትጠብዊ ኃሊበ ሀና፤ ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልኅቀትኪ በቅድስና፤ ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና፤ ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና።

ዚቅ
ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና፤ ከመ ታቦተ ዶር ዘሲና፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በቅድስና፤ ሲሳያ ህብስተ መና፤ ወስቴሃኒ ስቴ ጽሙና።

ምልጣን
ጽርሕ ንጽሕት ማርያም፤ ተፈሥሂ ሀገረ እግዚአብሔር፤ ቃል ቅዱስ ይወጽእ እምኔኪ፤ አእላፍ መላእክት ይትለአኩኪ።

እስመ ለዓለም
በጽሐ ሠናይ ወአልጸቀ ዘመን፤ ወበዓላ ለቅድስት ማርያም፤ እንተ በላዕሌሀ ተመርዓወ ቃል፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ተፈሥሂ ፍሥሕት ቡርክት አንቲ እምአንስት፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ይመጽእ ላዕሌኪ መንፈስ ቅዱስ፤ ወሃይለ ልዑል ይጼልለኪ፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ውእቱ፤ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ኢሳይያስኒ ይቤላ ቅንት ሐቌኪ፤ ወልበሲ ትርሢተ መንግሥትኪ፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ዳዊትኒ ይቤላ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ይሰግዱ ለኪ ኲሎሙ ነገሥታተ ምድር፤ ወይልሕሱ ጸበለ እግርኪ፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ወተወልደ እምኔሃ፤ ወይቤላ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ንባብኪ አዳም።

ወረብ
በጽሐ ሠናይ ወአልጸቀ ዘመን/፪/ ወበዓላ ለቅድስት ማርያም/፪/
እንተ በላዕሌሃ ተመርዓወ ቃል አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ/፪/

ቅንዋት፦
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ ማ፦ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል

ሰላም፦
ማህደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሠማእት ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኩልነ ኃበ ማርያም እምነ።
ዘተዋህዶ
@tewahdo01
@tewahdo01
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩመ
783 views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-11 09:27:47
ዉድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንደነዚ አይነቶችን ማሰራት የምትፈልጉ በ @jobabi21 ያናግሩን
525 viewsedited  06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 15:25:00 በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው ከምን ከምንድን ነው?

ክፍል ሁለት


➋ . #ከመጠመቅ


ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “#ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡

ለእግዚአብሔር በጎ ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1ኛ ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡

ስለዚህ ጥምቀት ስጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ ከመጠመቅ በፊት #ተጣጥበው ከጠሩ በሗላ መጠመቅ ይገባል እንጂ ከእድፍ ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡

ሌላው በዚህ በወር አበባ ወቅት ጸበሉን መጠጣት ይቻላል፤ እድፍን ማጥራት እንዳይሆን በሚል መጠመቅ ተከለከለ እንጂ መጠጣት አልተከለከለም፡፡


በነገራችን ላይ መጠመቅ ሲባል ለመጀመሪያ ጊዜ የሥላሴ ልጅነት ለሜገኝ ነው

ለእኛ ደሞ መፀበል ነው የሚባለው

ይቀጥላል

@tewahdo01
@tewahdo01
@tewahdo01
638 views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 11:18:37 በድጋሚ ወጣት ሆይ ንቃ ተበለተናል

ግብረ ሰዶማውያን በእጅ አዘውር ገብተውልሀልና ንቃ ወጣት መጀዘብ ይብቃ ፋሽንን መከተል ይብቃ መፈንደቅ መፈነዳደቅ ይብቃ ሰምተሀል ሰምተሻል ዝሙትና የዝሙት ፓርኖ ፊልም ይብቃ የግብረ ሰዶም ሀሳብና ተግባር ይብቃ አዎ ይብቃ ለዚህ እኮ ነው ሀገራችን ዙሪያዋን በጠላት ተከባ ያለችው ለዚህ እኮ ነው የሰይጣን ተልእኮ አስፈፃሚዎችን እየተከተልን ጠላት ዲያቢሎስ የሰለጠነብን
ኧረ ስንቱን ላውራው እባካችሁ እንንቃ ተኝተናል በተለይ በተለይ አዲስ አበባ ያላችሁ ተማሪዎች ንቁ ንቁ ንቁ አዎ ንቁ

''አለም በዝሙቷ የተነሳ ትጠፋለችን እናንተ ግን ተጠንቀቁ '' እንደሚል ቃሉ ልንጠነቀቅ ይገባል ፨

ስለሌሎች share በማድረግ ያልነቁት እናንቃ share ኮተት ነገር ሼር ለማድረግ ደቂቃ አይፈጅብንም መቼም ለዚህ ጉዳይስ በነፍሳችን ላይ በመጣ አስነዋሪ ነገርስ ቸል ማለት ይገባን ይሆን

@tewahdo01
@tewahdo01
@tewahdo01
@tewahdo01
@tewahdo01
547 views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 17:09:37 በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው ከምን ከምንድን ነው?

#ሴቶች ደመ ፅጌን በሚያዩበት ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አራት ዋና ዋና ነገሮች እንዳይፈጸሙ በመንፈሳዊ ሕግ ተከልክለዋል፡፡

#እነሱም


1). ከሩካቤ

2). ከመጠመቅ

3). ከመቁረብና

4). ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለከላሉ

➊ . ከሩካቤ

የወር አበባን የምታይ ሴት ባለ ትዳር ከሆነች በደሟ ወቅት ምንም እንኳን ባሏ ቢሆንም ሩካቤ መፈጸም በመንፈሳዊ ሕግ አይፈቀድላትም፡፡

የሕክምና ባለሙያዎችም ቢሆኑ በደም ወራት የሚደረግ ሩካቤ በአብዛኛው ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ በሽታዎችና እንድሁም ለልክፋት (ለኢንፌክሽን) በቀላሉ ለመጋለጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ይናገራሉ፡፡

በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር ክቡር ነው፡፡ #ስለዚህ ሴት ልጅ በትክት (በወር አበባ) ላይ እያለች ሩካቤን መፈጸም ክቡር ዘርን እዳሪ ከሆነ ደም ጋር ማዋሐድ ነውና ከባድ ኃጢያት ሆኖ ይቆጠራል፡፡


➋ . #ከመጠመቅ

ይቀጥላል

@tewahdo01
636 views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 21:42:41 ''ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመለከቶ የሚጸናበት፣ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው በሥራው የተባረከ ይሆናል''


(ያዕ.1÷25)
552 views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 21:31:29 ሰላም የተዋህዶ ልጆች እንደ አዲስ ልንጀምር አስበናል ምን ትላላቹ?
533 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-08 06:35:12 ይህ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን
ይጠብቃቸዋል (ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ. 90÷11-13 )
ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1÷12)
በፈሪኃ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን ድናቸዋል (ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37)

« እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የይቅርታ መላእክትን ያመጣል» (ሮሜ.9÷22)


ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀመናብርትን ድንቅ ገቢር ተአምራቱን ያዩ ምዕመናን

የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ
ስለተሾመ ከጌታ
አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም
ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም
በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ የባላገር ሴቶች ሁሉ
የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ
ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ ……


↳ እያሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡
ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት በቅዱሳን ላይ ድንቅ የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት ምንጭ በሆነ ድርሳኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡

በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል ጥቂቶቹን እነሆ

~> በሥነ-ሥዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ ቴዎዶስዮስንና ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና ክብር አብቅቷቸዋል፡፡

~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጸድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው ህግ እየተመራ የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡

~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ ክብር በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ ሳለች ጠላትዲያቢሎስ አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጸ ከጥፋት ታድጓቸዋል፡፡

በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው

~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን ጋንኤን ሲታደጋት የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት (መጽሐፍ ጦቢት)
ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡


ማጠቃለያ

እንግዲህ የእግዚአብሔርን ሃይል በቅዱሳኑ መላእክት አድሮ የሚፈጽመውን ሥራ የሚክዱ የአምልኮ መልክ ያላቸው ይህን ቅዱስ መጽሐፍ በምስክርነት የገለጠውን በምልዐት የሰበከውን የቅዱሳን መላእክት አገልግሎትና ክብር ማስተዋል የተሳናቸው የገዛ መንገዳቸውን ስለሚከተሉና ቅዱሱንም ቃል ስለማያደምጡ፣ ለራሳቸው ደስታ ቅድሚያ ስለሚሰጡ ነው፡፡ « ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ የአምልኮት መልክ አላቸው ሃይሉን ግን ክደዋል» (2ኛ ጢሞ.3÷5)

በታላቁ ንጉሥ በእግዚአብሔር ፊት ለምሕረት ለምልጃ የሚቆሙ መላእክቱን መመልከት የሚቻለው እንደሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ መከራን ሁሉ ታግሶ በመጽናት መስቀሉ ስር በመገኘት የሥጋን ፈቃድ አስገዝቶ የነፍስን መንፈሳዊ ኃላል በማጎልበት፣ በቅዱሳን መላእክቱ ረዳትነት እግዚአብሔርን ምህረት በመሻት ነው፡፡
በሃይማኖት ያለን ጽናት ለተጋድሎ ያለን ትጋት፣ ለቤተክርስቲያን ያለን ፍቅር ለአባቶች ያን ክብር ሳቀንስ ሰማያዊውን ሃይል በታቦት በመስቀሉ መንፈሳዊውን በረከት በእምነት በጠብሉ ተቀብለን መንግስቱን አምላካችን እንዲያወርሰን የሊቀመናብርት ቅዱስ ሩፋኤል ምልጃ በህይወታችን ሁሉ አይለየን፡፡ አሜን

✧የቃልህ ፍቺ ያበራል✧ መዝ118 ÷130

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

(ከቴዎድሮስ በለጠ ከታህሳስ ፲፫ ፳፻፭ በድጋሜ ለጳጉሜን ፫ የተለጠፈ)
903 views03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-05 22:47:03 ጳጉሜን እኔና ጓደኞቼ
     *~★★~*

… ዘንድሮም እንደተለመደው ፌስቡክ ጳጉሜን መድረሷን ጠብቆ ከገጹ ቢያግደኝም። እኔ በቴሌግራም ቻናሌ እናንተ ደግሞ በፌስቡክ ገጻችሁ ማጥለቅለቃችንን እንቀጥላለን።

•••
እኔ ዘመዴ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ጓደኞቼ በሙሉ አንድ ላይ ሁነን መጪውን የወርሀ ጳጉሜን ፭ቱን ቀናት ልክ እንደ አምናው ካቻምናው ሁሉ ዘንድሮም ዘመነ ማቴዎስን አሳልፈን ዘመነ ማርቆስን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ዘንድሮ እንዲያውም በቋሚ ሲኖዶሳችን ጭምር ወርሀ ጳጉሜን በጾም፣ በጸሎትና በምህላ እንድናሳልፍ ሁሉ ዐዋጅ ታውጇል። አዲሱን ዓመትም በዚህ መልኩ እንቀበላለን ማለት ነው። እናም እኛም ከጾም ጸሎት ምህላው ጎን ለጎን አምስቷን ቀናት እንደልማዳችን በዚህ መልኩ እናሳልፍ ዘንድ አስበናል። ወስነንም ተዘጋጅተናል።
                     
፩፥ ጳጉሜ ፩  የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜ ፪  የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜ ፫  የፊደል ገበታ ቀን።
፬፦ ጳጉሜ ፬ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።
፭፦ ጳጉሜ ፭  ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያና ለአቅመ ደካሞች የሥጦታ ቀን።

•••
ጳጉሜ ፩ ፥ የማዕተብ ቀን ነው።

… የተዋሕዶ ልጆች አንገት በሙሉ በአንገት ማዕተብ ክር ያሸበርቃል። የመስቀል ዓይነት የፌስቡክና የቴሌግራም ቻናሎቻችንንም ያጥለቀልቃል። በዕለቱ ፌስቡክ ሌላ ወሬም የለም፣ ሌላ ፎቶም አይለጠፍበትም። ተዘጋጁ፣ ጳጉሜ ፩ እየጾምን፣ እየጸለይንም፣ ማዕተባችንንም አጥብቀን እናስራለን። የአንገት ማዕተብ የሌላችሁ ከወዲሁ ግዙ፣ አስባርካችሁም እሰሩም። አንገታችሁ ባዶ አይሁን።

•••
ጳጉሜ ፪ ፥ የክብረ ክህነት ቀን ነው።

… ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለካህናት አባቶቻችን፣ ፍቅራችንን፣ አክብሮታችንን የምንገልጽበት ዕለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ የምንልበት፣ ቡራኬ የምንቀበልበት፣ ለበዓሉም ለአባቶቻችን ስጦታ የምንሰጥበት፣ ዕለትም ነው። እኔም አደርገዋለሁ። እናንተም አድርጉት። ተዘጋጁ።

•••
ጳጉሜ ፫፥ የፊደል ገበታ ቀን።

… አከተመ የዚያለት ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፊደላት ሲያሸበርቅ ይውላል። የዚያን ዕለት ልብሱ ሁሉ የፊደል ገበታ ነው የሚሆነው። በዓለሙ ሁሉ ስንነበብ እንውላለን። ፊደላችን የፌስቡክን ግድግዳ  አጥለቅልቆት ይውላል።

•••
ጳጉሜን ፬ ፥ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን።

… ይሄ ምንም ማብራሪያም ዝርዝርም አያስፈልገውም። በዚህ ዕለት ፌስቡክ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ የነፃነት ሰንደቅ ዓላማና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፎቶ አሸብርቆ የሚውልበት ቀን ነው ማለት ነው።

•••
ጳጉሜ ፭ ፥ ከሱሶች ሁሉ የመላቀቂያና፣ የመገላገያ ለአቅመ ደካሞችም የሥጦታ መስጫ ቀን እናደርገዋለን። እነ ሲጋራ በአደባባይ ይረገጣሉ። አልኮል፣ ጫት፣ ሺሻና ሀሺሽም ይወገዳሉ፣ ይረገማሉ። ከዝሙት እንሸሻለን። በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዘመን ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ሰማዕታትን፣ እንቀበለዋለን፣ እንቀላቀለዋለንም። ታዲያ እኛ ደስስ ሲለን ሌላ የሚከፋው እንዳይኖር ጉረቤቶቻችንን በዓሉን አዲሱንም ዓመት በደስታ ይቀበሉ ዘንድ ያለንን የምናካፍልበት ዕለትም ነው። ቢያንስ ቅቤ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ዶሮና እንቁላል እናበረክትላቸዋለን።

•••
ሰምታችኋል ጓደኞቼ ተዘጋጁ። ደግሞም እናደርገዋለን። አባቴ ይሙት እናደርገዋለን። ይሄን መልእክት የጻፍኩት ለጓደኞቼ መሆኑ ይሰመርበት። መንገደኞችን አይመለከትም። አከተመ።
694 views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-06 23:00:51 ​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው?

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@tewahdo01
@tewahdo01
@tewahdo01
978 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ