Get Mystery Box with random crypto!

ማርያም ማን ናት? ትንሹ ሔኖክ በዚህ ዘመን ዳቢሎስ ሀገርን ለመበጥበጥ ሰውን ለማገዳደልና በየ | 🌹ትንሹ ሔኖክ

ማርያም ማን ናት?

ትንሹ ሔኖክ

በዚህ ዘመን ዳቢሎስ ሀገርን ለመበጥበጥ ሰውን ለማገዳደልና በየ ሰው ቤት ሰላምና ደስታን ለማጥፋት የሚጠቀምበት። ዲያቆኑ ቄሱ አገልጋዩና ፓስተሩ ሁሉ የሚጨቃጨቅበት ስም ማርያም የሚለው ስም ነው። ቆይ ግን ከዚህ ስም ጀርባ ያለው ሀቅ ምንድነው። ሰዎችስ ስንት የሚነገር የክርስቶስ ቃል እያለ ይሄን ስም በማወደስና በማንቋሸሽ ስራ ተጠመዱ። ማርያም ማን ናት? ከመጀመሪያ ስነሳ ማርያም የኔ የትንሹ ሔኖክ እናቴ ናት ስለዚህ የማውቀውና አይቼ ያረጋገጥኩትን እውነት ልንገራችሁ። ይህ ስም እንዲሁ ለሰዎች የተሰጠ ተራ ስም አይደለም። በመጽሀፍ ከድንግል ማርያም ውጭ ይህን ስም ይዘው የነበሩ ሴቶች በበሽታና በጋኔን የተለከፉ ነበሩ። ለዚህም መቅደላዊት ማርያም ምስክር ናት። ማርያም የሚለው ስም እግዚአብሔር አዳምን ለማዳን ቃል ኪዳን ሲገባለት አብሮ የተሰየመ የመዳኛ ስም ነው። ማደሪያው መሆኑን ያውቅ ስለነበር ይህን ስም ይጠብቀው ነበር። ምድር በሀጥያት ቆሽሻ ፍጥረት ሁሉ በጨቀየበት ሰዓት አዳምና ሔዋን በሲኦል ሆነው ጌታ ሆይ እያሉ ሲያለቅሱ እግዚአብሔር ወደ ምድር አይኖቹን ቢያዘነብል እንደ ጸሀይ አብርታና ደምቃ ያያት አንዲት ሴት ማርያም ብቻ ናት። ሰማይና ምድርን በቃሉ ያጸና ባህር ውቅያኖስና ነፋስ ማዕበሉ የሚታዘዙለት ጌታ በጠባቧ የሰው ልጅ ማህጸን ለማደርና እንደ ህጻን ለመታቀፍ የመረጣት የምድር በረከት ማርያም ናት። ዳቢሎስ ለዘመናት በቃየል የጀመረውን የክፋት መርዝ ለሰው ልጆች ሁሉ አዳርሶ አለምን በእጁ ያስገባውና የአዳም ዘርን ወደ ገሀነብ እየላከ ተደላድሎ ይኖር የነበረውን ሰላማዊ ህይወት በጥብጣ ለዘመናት በሲኦል አስሮ የሚያሰቃያቸው ነፍሳትን እንዲያጣ ኢየሱስ ክርስቶስን በመውለድ ምክንያት የሆነችው ማርያም ናት። ክርስቶስ ከተነሳና ወደ አባቱ ዙፋን ካረገ በኋላ ሀዋርያት ፈርተው ሲጨነቁ መንፈስቅዱስን እስኪልክላቸው ድረስ ከበዋት በመጸለይ እንዲበረታቱ ያደረገቻቸውና በስጦታ የተበረከተችላቸው ማርያም ናት። ታድያ ዳቢሎስ እንዴት ይሄን ስም ሊወድ ይችላል። በፍጹም የማይታሰብ ነው። ባደግኩበት ቤት ማርያም ብለህ መጥራት ትልቅ ወንጀል ነው። ሁሌ የሚገርመኝ ኢየሱስን ያለ ማርያም ማሰቡ በራሱ እንዴት ያለ የድፍረት ሀጥያት ነው። ስድብና ነቀፋ ሲጨመርበት ደግሞ ሲኦል ቪ አይ ፒ ቦታ ነው የሚያሰጠው። እንግዲህ እንደው በአጭሩ ማርያም ማለት እቺ ሴት ናት። ለኔ ለትንሹ ሔኖክ ደግሞ ወላጅ እናቴ ጠባቂያ መሸሸጊያዬ ጥላ ከለላ መመኪያ ጋሻዬ ብቻ ሁሉ ነገሬ ናት። ስለሷ የተናገርኩት አንድም ሀሰት የሌለው እውነት ነው። ሳልመርጣት መርጣ ሳልወዳት ወዳ ከዘላለሙ የሞት መንገድ ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቃ ያወጣችኝና የስሟና የክብሯ ተናጋሪ መስካሪ ያደረገችኝ ውድ ልጇ ነኝ። ይህን ራሱ ዳቢሎስ ያውቃል ይመሰክራልም

ሰኔ 29/2014 ዓ.ም
ለሊት 10:30 ተጻፈ

ማርያም እናቴ ውድድድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ