Get Mystery Box with random crypto!

ውቢት በአንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ የምትኖር ውቢት የተባለች ልጅ ነበረች ። ውቢት በከተማው  በውበ | ተረት ተረት

ውቢት

በአንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ የምትኖር ውቢት የተባለች ልጅ ነበረች ።
ውቢት በከተማው  በውበቷ እንደሷ ያለ ባለመኖሩ  የማያውቃትና የማያደንቃት ሰው አልነበረም ።

የከተማው ሰው ሁሉ ውበት ከውቢት ውጪ የትም የለም እስከማለት ደረሰ።

ታዲያ ውቢት ምን ውጫዊ መልኳ ያማረ ቢሆንም ፀባይዋ አስቸጋሪ እና የማይጨበጥ ነበር።

ከሷ ወዲያ ውብ እንደሌለ በማመን በሰዎች ላይ ትኮራ እና ሰዎችን በመናቅ ታመናጭቅ ነበር ።

ምንም አይነት ጓደኛም አልነበራትም ምክንያቱም ጓደኞቿን የምትንቅና ከሷ የበታች ሆነው ትዕዛዟን እንዲፈፅሙ ስለምትፈልግ የቀረቧት ሁሉ ራቋት።

በዚህም የተነሳ ብቸኝነት እየተሰማትና ደስታን እያጣች ሄደች።

የውቢት አባት ከሀገር ሀገር የሚዞር ነጋዴ ነበር ። የውቢት ፀባይ እንዲህ መሆንም በጣም ያሳስበው ነበር።

እሱ በሚሄድባቸው ሀገራት ከውቢት የሚበልጡ ቆንጆዎችን አይቷል።
በአጋጣሚም በስራ ምክንያት ያነጋገራቸውም ነበሩ ግን ፍፁም ትሁቶች ነበሩ።

እሱ እንደገመተው እነውቢት የሚኖሩበት ከተማ ትንሽ በመሆኗ ውቢትን ብቸኛዋ ቆንጆ እንድትሆን አስተዋፅኦ አድርጓል።
የከተማው ሰው ሁሉ ከውቢት ውጭ ቆንጆ ውብ የለም በማለቱ ልጁ እንድትኩራራና ሌሎችን በመናቅ የማይሆን ፀባይ እንዲኖራት ምክንያት ሆኗል።

በዚህ የተነሳ አባቷ አስቦ አስቦ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰ።
ይኽውም ውቢትን ለንግድ በሚሄድባቸው ሀገራት ይዟት በመዞር ያልተረዳችውን እንድታይ ወሰነ ።

ውቢት አባቷ ለሽርሽር ወደሌላ ቦታ እንደሚወስዳት በነገራት ጊዜ በደስታ ተፍነከነከች።
እንደተለመደው በሌሎች ከተሞች ውበቷ ሊወደስ መሆኑን በማሰብ ደስስስ ተሰኘች።
ለነገ ጉዟቸውም አሉኝ ያለቻቸውን ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች በሻንጣዋ ያዘች።

በቀጣዩም ቀን ለጉዞ ተነሱ።

ጉዟቸው አስደሳች የነበረ ቢሆንም ለውቢት ግን ግራ የሚያጋባ ነበር ። እንደሚኖሩበት ከተማ ሰዎች ውበቷን ያደነቀ አላጋጠማትም በተዘዋወሩባቸው ቦታዎች ብዙ ቆንጆ ሰዎችን ለማየት ቻለች።
እነሱ ግን ከሰዎች ጋር ተግባቢና ሳቂታዎች ደስተኞችም ጭምር መሆናቸውን ተመለከተች።
በዚህ ጊዜ አንድ ያልገባት ነገር እንዳለ ጠረጠረች።

በቀጣይ ቀናትም አባቷ የሚያውቃቸው ደንበኞቹ ጋር ይዘት ሄደ ከሁለቱ ጋርም አስተዋወቃት ሴቶቹ እጅግ ውብና ዘመናዊ ነበሩ።  በዛውም ልክ ከማንኛውም ሰው ጋር የሚግባቡና በመከባበር የሚያወሩ ደስተኞችም ጭምር ሆነው አገኘቻቸው።

በዚህ ጊዜ ምን መልክ ቢያምር የውስጥ ውበት ከሌለ ሁሉም ነገር ከንቱ እንደሆነ ተረዳች።
ጎደኞቿ ላይ ታሳይ የነበረው ነገርን ባሰበች ጊዜ ሀፍረት ተሰማት።
የዚህ ጊዜ አባቷ አብዝቶ የሚለው ጥቅስ ትዝ አላት
"መፅሐፍን በሽፍኑ አታድንቀው"

'ለካንስ ውበት ውስጥ ነው ያለው እውቀት ፣ደግነት ፣ ትህትና፣ ፍቅር እነዚህ ናቸው ውበት ' ብላ በማሰብ ከአንባቷ ጋር በነበራት ጉዞ የህይወቷን ትልቅ ስህተት ለማረም ቻለች።

በሂደትም ያጣቻቸውን ጓደኞቿን በጥሩ ባህሪዋ ለመመለስ ቻለች።
ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ
@TeretTeretChannel