Get Mystery Box with random crypto!

Terefe Abera's View

የቴሌግራም ቻናል አርማ terefeaberaview — Terefe Abera's View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ terefeaberaview — Terefe Abera's View
የሰርጥ አድራሻ: @terefeaberaview
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 620
የሰርጥ መግለጫ

ከማውራት ያለፈ እንኑር!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-22 06:01:32 ለኢየሱስ በመክፈት ማስከፈት

ወደ ሕይወት የገባንበት በር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልባችን ደጅ ቆሞ እንዲህ ይላል "እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።" ራእይ 3:20 የልባችን በር ላይ የክብር በር ቆሞአል፡፡ እንዴት ወደ ሰማይ ያስገባንን በደጅ እናቆመዋለን??? ድምፁን ሰምተን የምንከፍትለት መቼ ነው??? ወደ ሕይወታችን መቼ ነው የምንጋብዘው???
ብዙ ነገሮች ለምን የተቆላለፉብን ይመስላችኀል?? ለምን የቁም ነገር ውሉ ጠፋብን?? የተወሳሰቡብን ጉዳዮች መፍትሔ ማን ነው?? ለኢየሱስ በሩን የከፈተ በር አይዘጋበትም፡፡ ለእርሱ ልባችንን ከከፈትን ሰማይ እንኳ አለመከፈት አይችልም!! በሐዋርያት ሥራ ላይ የተተረከው ድንቅ ነገር ትዝ ይላችኀል??? ሐዋርያው ጴጥሮስ ከእግዚአብሔር መልአክ ጋር ከእስር ቤት ሲወጣ የእስር ቤቱ በር አውቆ ተከፈተላቸው፡፡
እንዲህ ተጽፎአል፦ "የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው" የሐዋርያት ሥራ 12:10 ለኢየሱስ በሩን የከፈተ እንዲህ ይከፈትለታል፡፡ በር እንኳ አውቆ ይከፈታል፡፡ ለኢየሱስ በሩን የከፈተ ለምንድነው ደጆች ሁሉ የሚከፈቱለት??? መክፈቻ ያለውን ጌታ ስለያዘ ነው፡፡ የሰላም፥ የፍቅር፥ የደስታ፥ የስኬት እና የሕይወት ደጅ ከተዘጋብን ለኢየሱስ በመክፈት እናስከፍት፡፡እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!!!! ተረፈ አበራ
https://t.me/terefeaberaview
82 views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 08:18:26 ጠንቃቃ ኃጢአተኛ በራሱ ጉዳይ እውር ሲሆን በሰው ጉዳይ ዳኛ ይሆናል፣ ያድነን!!!
እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!!!ተረፈ አበራ
https://t.me/terefeaberaview
261 views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 05:53:00 የሚያሳድር ጥላ

ይህን መዝሙር ወደዋለሁ፥ እጸልየዋለሁ፥ ተጠቅሜበታለሁ።

"በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።" መዝሙረ ዳዊት 91:1።

ልዑል መጠጊያችን ነው፡፡ ሁሉ ስላለው ቢያስጠጋ ያምርበታል፡፡ ልዑልን መጠጊያ አድርጎ የሚኖር <ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል> ልዑል ሁሉን የሚችል አምላክ ነው፡፡ ጥላው ያሳድራል፡፡ የዛፍ ጥላ ፀሐይ ያሳልፋል፡፡ የአምላካችን ጥላ መከራ ያሳልፋል፡፡ የሰው ጥላ ሰው አያስጠልልም፡፡ የልዑል ጥላ ሕዝብ ያስጠልላል፡፡ በክንፎቹ ጥላ አድረናል፡፡ ጥላው አሳዳሪያችን ነው፡፡ ጥላው ከለላችን ነው፡፡ ጥላው የነፃነት ዓለማችን ነው፡፡ ጥላው የዕረፍት መስካችን ነው፡፡እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!!!! ተረፈ አበራ
279 views02:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 04:27:49
300 views01:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 04:27:41 ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ፥ ኢየሱስ መጣ!

የተዘጉ ልቦች እንጂ የተዘጉ ደጆች ከመግባት አይከለክሉትም
እርሱ የከፈተውን የሚዘጋ፤የዘጋውንም የሚከፍት ማንም የለም
"ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። ይህንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።" የዮሐንስ ወንጌል 20:19-20

ዛሬም ቀን በመሸ ጊዜ፥ የማይጠልቀው ፀሐይ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ሌሊት በረዘመ ጊዜ፥ የአጥቢያው ኮከብ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ወዳጅ በሸሸ ጊዜ የማያረጀው ወዳጅ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ስልጣን በመሸበት ጊዜ የማይሻረው ንጉሥ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ሀብት በመሸበት ጊዜ የማያጎድልበት ባለጸጋ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ውበት በመሸበት ጊዜ የማይጠወልገው ውበት ኢየሱስ ይመጣል፡፡ እውቀት በመሸበት ጊዜ የማያልቀው የጥበብ መዝገብ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ስለሆነም ትኩረታችንን እርሱ ላይ እናድርግ፡፡

ደቀመዛሙርቱ ተሰብስበው እንኳ ይፈሩ ነበረ፡፡ ተሰብስቦም ፍርሐት፥ አብሮም ሆኖ ፍርሐት፥ ደጅም ዘግቶ ፍርሀት የከፋ ጉስቁልና ነው፡፡ ተሰብስበን እንኳ የሚያስፈሩ ይኖራሉ፤ አብረን ሆነን እንኳ ያለሸነፍነው ፍርሀት አለ፡፡ በሰው ልብ ኢየሱስ ሕያው ካልሆነ እንዲህ ያለ ፍርሀት ያሰቃየዋል፡፡ ፍርሀት አደገኛ በሽታ ነው፡፡ ፍርሀት ብዙዎችን ከታሰበላቸው እንዳይደርሱ ከልክሏል፡፡ ፍርሀት እውነትን ቀብረን የውሸት እንድንኖር ያደርጋል፡፡ ይህ ፍርሀት በኢየሱስ ስም ይነቀል፡፡ የሚያስፈሩንን ሊያስፈራ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ያስጨነቀንን ሊያስጨንቅ ኢየሱስ ይመጣል፡፡ በፈራነው ነገር ላይ ባለ ድል ሊያደርገን ኢየሱስ ይመጣል፡፡

ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ ነበረ ኢየሱስ የመጣው፤ የተዘጉ ልቦች እንጂ የተዘጉ ደጆች ከመግባት አይከለክሉትም፡፡ ዛሬም በተዘጉብን ነገሮች ላይ መክፈቻ ያለው ኢየሱስ ይመጣል፡፡ ዛሬም በጨለመብን ነገር ላይ ብርሀናችን የእግዚአብሔር ልጅ ይመጣል፡፡ እርሱ የችግሮቻችን ሁሉ መፍቻ ነው፡፡ በተዘጉብን ሁሉ የእርሱን ስም እናውጅ፥ ይከፈታል፥ የከፋቹን ስም እንጥራ፡፡ ኪሳራ ፈርተን በዘጋናቸው ስራዎች ላይ፥ ወጭ ፈርተን ባቆምነው ነገር ላይ፥ ፀብ ፈርተን በዘጋነው ወዳጅነት ላይ ኢየሱስን እንጋብዘው፡፡እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን! ! ተረፈ አበራ

https://t.me/terefeaberaview
320 views01:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 06:15:04 የትልቅነቱን ያህል ቅርብ እንደ እግዚአብሔር ማን አለ?
“እግዚአብሔር ትልቅ ነው”
መዝሙር 48፥1

ከምደነቅባቸው ህያው ቃሉ መካከል አንዱ፤
"ጌታ ቅርብ ነው "ፊል4:6 የሚለው ነው።
ኃያሉ ልዑል፣ሁሉን ቻዩ ኤልሻዳይ፣የሁሉ ፈጣሪና አስገኝ አዶናይ፣የነበረ ያለ የሚኖር አልፋ ዖሜጋ የሆነው ቅርባችን ነው።

አስባችሁታል ?
ትልቆች የሚገኙት በእነርሱ ሁኔታ እንጂ በእኛ ሁኔታ አይደለም።
ትልቁ እግዚአብሔር በምንም ሁኔታ ብንሆን ቅርባችን ነው።

ሌላው የሚያስደንቀው ቅርብነቱ ለፈለጉት ሁሉ ነው።

ወገኖቼ ትልቅ ሰው፣ሀገር አለ ለሁሉ ግን ቅርብ አይሆንም አይደለምም ።
ለዚህ ነው የምንፈልገውና የምንወደውን ሰው፣ለመርገጥ የምንመኘውን ምድር፣በሕይወታችን አንዴ እንኳ ማግኘት የማንችለው ።

አዎ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ለልጆቹ ቅርብ ነው።
ቅርባችን ሁሉን ቻይ ነው ።
ከቅርባችን ጋር ውለን እንደር።
በፊቱ ከምስጋና ጋር በፀሎትና በምልጃ አብረነው ወጥተን እንግባ።

የግልና የቤተሰብ፣የሀገርና የቤተክርስትያን ሐሳባችንን ፣ሸክማችንን ፣የሚያስጨንቀንን ሁሉ ለቅርባችን እንተወውና እንረፍ።

እግዚአብሔር ከእኔና ከአንተ ከአንቺ ጋር ነው!!
ሰው ሁሉ ከማያገኘው የሀገር መሪ ጋር ብንውል ዛሬ ከእገሌ ጋር እያልን ስናወራ ነው የምንውለው ነገም ትላንትና የዋልኩት እያልን መገኘት ሰውኛ ነው።

ካገኘናቸውና ከምናገኛቸው ሁሉ ትልቅ ግን አብረነው ውለን በማደራችን ተደንቀን ያላወራነው አለና ዞር እንበል።
በሉ እስኪ እንዲህ በማለት ዛሬ ስናሰላስል እንዋል እናውራ ።
አንተ የእኔ አባት ከምንልህ ይልቅ ታላቅ ነህ።የገባንን ያህል ነው ትልቅ ነህ የምንልህ አንተ ግን ከዚያም በላይ ነህ።ነገር ግን ከእኔ ከልጅህ ጋር ትገባለህ ትወጣለህ ፤ትሰማኛለህ ትመልስልኛለህ፣አብረኸኝ ስለለህ እጅግ ደስ ይለኛል ተመስገን
እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን !!! ተረፈ አበራ

https://t.me/terefeaberaview
297 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 06:34:38 ጠዋትህን የጀመርክበት መንገድ ቀንህን እንደሚወርሰው ታውቃለህ?
በዚህ ማለዳ ስለተኛነው ጣፋጭ እንቅልፍ፣ ደግፎን ስለመንቃታች በምህረቱ የመደነቅ ምስጋና ጠግበን እንውጣ።በቀኑ ውስጥ ምንም ይግጠመን ።ስሜታችንና ልባችን በገጠመን ነገር ሳይሆን በወጣንበት የምስጋና ኃይል እየተዳኘ ይውላል።ስለዚህም ሲመሽ እናመሰግናል።ይህ ከሆነ በብርሃን ፣በጨለማ በምስጋና የመኖር ሕይወት ባለቤት ሆንን ማለት ነው ።
እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ተረፈ አበራ
“እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ።”
መዝሙር 3፥5“በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን ”
መዝሙር 90፥14https://t.me/terefeaberaview
275 views03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 01:29:12 ራስን ማጥፋት

የአንድ ወዳጄ ወንድሙ እንዳረፈ ሰምቼ ለቅሶ ደረስኩና በተለመደው ባህል ታሞ ነበር ? ብዬ ጠየኩት ረሱን አጥፍቶ ነው አለኝ ልብ ይሰብራል የ16 ዓመት ልጅ ፣ይህ ጉዳይ ወዴት እየሄደ ነው ? ባለፈው አርብ ጣይቱ ሆቴል ጊቢ በሚገኝ አንድ የግል ባንክ ሠራተኛ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ራሱን ገድሎ ተገኘ ተብሎ በሬድዮ ተነገረ፡፡ምክንያቱ ምን እንደሆነ ባይታወቅም ሰዎቹ ሞትን መርጠዋል፡፡ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሕይወት ይበልጣል!!የሰው ሕይወት ምን ያህል ክቡር እንደሆነ አስበው ያውቃሉ?በዚህ ዘመን ለሕይወት የምንሰጠው ትርጉም እና የተመነው ዋጋ በጣም ዝቅተኛ ሆኗል፡፡በዚህም ምክንያት ብዙዎች መራመድ ሲከብዳቸው ራሳቸውን እያጠፉ ነው፡፡ካለብን ጫና እና ካለንበት ሁኔታ አንፃር ሕይወትን መመዘን ያስቸግራል፡፡ራስን ማጥፋት በሌሎቹ ዓለማት መጠኑ በጣም ከፍተኛ ነው፥ ብዙ ነፃነት ብዙ ስኬት ብዙ ምቾት ባለበት ዓለም በደስታ መኖር ምርጫቸው አልሆነም፡፡በአንፃሩ በአፍሪካ ኑሮ ቢከብድም ችግሮችን ተቋቁሞ መኖር ምርጫ ነበረ፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ኢትዮጵያም ውስጥ መጠኑ በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ሕይወት እንደሚበልጥ ማመን አለብን፡፡እኛ የእግዚአብሔር ነን፥ በራሳችን ላይ ስልጣን የለንም ስለዚህ ራሳችንን መግደልም ሆነ ማኖር አንችልም፡፡ራስን ማጥፋት የሚያጋጥመው በሚከተሉት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፦
☞ኑሮን በፉክክር መምራት ስንጀምር፦ያለን እንደሚበቃን አምነን የራሳችንን ኑሮ በደስታ መኖር መጀመር መፍትሔ ይሆናል፡፡ልከኛ አኗኗርን መምረጥ አለብን፡፡
☞ሽንፈት፦ ሰው አልሸነፍ ባይ እልኸኛ ነው፡፡ነገር ግን በሕይወት ውስጥ ሁልጊዜ ድል መጎናጸፍ የለም፡፡ስለዚህ ሽንፈትን በጸጋ ተቀብሎ ከውድቀት መማርና ለቀጣዩ ድል ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡የቱም ነገር ይፈጠር ሕይወት ይቀጥላል፡፡
☞ችግሮችን የመቋቋም አቅም ዝቅተኛነት:- ትውልዱ መንፈሰ ጠንካራ አይመስልም፡፡በቀላሉ ይደሰታል በቀላሉ ይከፋል በቀላሉ ይወድቃል፡፡ልፍስፍስ መሆን የለብንም መንፈሰ ጠንካራ መሆን አለበን። እግዚአብሔር ብዙ ነገር የሚችልና የሚቋቋም አድርጎ ነው የፈጠረን።
☞የእግዚአብሔርን ጸጋና ምሕረት መግፋት፦ ሰው ስለሆንን ልንበድል እንችላለን እግዚአብሔር ደግሞ የንስሐ መንገድ አዘጋጅቶልናል ስለዚህ እንደ ይሁዳ የእግዚአብሔርን እውነት፥ ይቅርታ፥ ምሕረት እና ሰላም ከመግፋት እንደ ዘኬዎስ ንስሐ መግባት የበደልነውን መካስ የቀማነውን መመለስ ያስፈልጋል፡፡
☞በእግዚአብሔር አለመደገፍ፦ የትውልድ ተስፋ እግዚአብሔር ነው።"ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤በእውነት ፍጻሜ አለህና፥ ተስፋህም አይጠፋምና። " ምሳሌ 23:18 በእግዚአብሔር ከተደገፍን ፍጻሜያችን ያምራል፤ ተስፋችን አይጠፋም፡፡ከየቱም ነገር በላይ ሕይወት እንደሚበልጥ እንመን፥ ስለዚህ ደርሰን ሞት አንደግስ!! እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን !!

ተረፈ አበራhttps://t.me/terefeaberaview
327 views22:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 01:26:25 መርጋትና መርካት ከወዴት? ?
ብዙ ነገር ይዘንና ሰብስበን(ሥልጣን፣ገንዘብ፣ክብር ወዘተ)ለምን መርጋትና መርካት አቃተን?
መርጋትና መርካት ያለውና የሚሰጠው የነፍሳችን እረኛ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው።
1ጴጥ 2:25
https://t.me/terefeaberaview
265 viewsedited  22:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 01:25:36 ይድረስ ያገቡ ልጆች ላላችሁ ወላጆች
ውድ ወላጆች ልጆቻችሁን ከወደዳችኋቸው ከትዳራቸው በመውጣት ውለታ ዋሉላቸው ።አግዟቸው እሱንም ከፈለጉና ከፈቀዱ ብቻ።

“ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።”
ዘፍጥረት 2፥24
https://t.me/terefeaberaview
269 views22:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ