Get Mystery Box with random crypto!

ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት

የቴሌግራም ቻናል አርማ tenbihat — ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት
የቴሌግራም ቻናል አርማ tenbihat — ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት
የሰርጥ አድራሻ: @tenbihat
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.36K
የሰርጥ መግለጫ

ተንቢሀት - የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች የሚቀርቡበት ቻነል nesiha.com

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-20 08:20:42 ደረሰ
ነሲሓ የወንድ ታዳጊዎችና ወጣቶች ልዩ የክረምት ኮንፈረንስ

ወጣት የነብር ጣት! የዲኑ የጀርባ አጥንት!

ታዳጊ እና ወጣት ወንዶችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ድንቅ ኮንፈረንስ!

በዕለቱ የተለያዩ ወሳኝ ርዕሶች የሚዳሰሱ ሲሆን

ዐቂዳ እና ቁሳዊነት

የቁሳዊነት ጭለማ በእምነት ብርሃን የሚገፈፍበት። ዘመን አይሽሬ ኢስላማዊ መፍትሄ የሚሰጥበት።

በአንጋፋው ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

መዝናናት እና መደሰት በሸሪዓ ሚዛን

መዝናናት ምንድን ነው? እውን ኢስላም መዝናናትና መደሰትን ከልክሏል? እና መሰል ጥያቄዎች ከመድረኩ መልስ ያገኛሉ!

ለወጣቶች በወጣቱ ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ ፈረጃ

በተጨማሪም

በሌሎች ዳዒዎች እና ባለ ተሰጥኦ ወጣቶች ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ!

እንዲሁም:

☞ልዩ ዶክመንተሪ

☞ "የነብዩላህ ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም ድንቅ ፅናት" ልዩ በሆነ አቀራረብ ተካቷል።

ፒያሳ በሚገኘው ኸሊፋ አዳራሽ

ቀን: እሁድ ነሐሴ 15 / 2014

ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

መግቢያ በነፃ

ከእናንተ የሚጠበቀው ማስታወቂያውን ያልሰማ ወንድማችሁን ይዞ መምጣት ብቻ!

https://t.me/darulhadis18
851 views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:53:05 እንዳያመልጥሽ
ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

በተለመደው ወርሃዊ የሙሀደራ ፕሮግራማችን በአላህ ፈቃድ፦

እምነታችን

የልብ በሽታዎች እና መድሀኒታቸዉ
እንዲሁም አስተማሪ መነባንብ ይቀርባል።


ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ቅዳሜ ነሐሴ 14፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:00
ቀጠሮአችን በኢማሙ አህመድ መስጂድ ይሁን።

አድራሻ: አለም ባንክ/ አንፎ አል-ጋዚ አደባባይ

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!


https://t.me/darulhadis18
960 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 11:08:27
ነሲሓ የወጣት ወንዶች ልዩ ኮንፈረንስ


ነሲሓ ወጣቶችና ታዳጊዎችን አስመልክቶ በአይነቱ ልዩ የክረምት ኮንፈረንስ አሰናድቷል


በእለቱ የሚሰናዱ ፕሮግራሞች

☞ዐቂዳና ቁሳዊነት በኡስታዝ ሙሐመድ ሀሰን ማሜ
☞መዝናናትና መደሰት በሸሪዓ ሚዛን ዐብዱረዛቅ ፈረጃ

በሌሎች ዳዒዎችና ባለተሰጥኦ ወጣቶች ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

☞ አስተማሪ መጣጥፍ በዶክመንተሪ መልኩ

☞ "የነብዩ ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም ድንቅ ፅናት" ልዩ በሆነ አቀራረብ


ፒያሳ በሚገኘው በኸሊፋ አዳራሽ

ነሓሴ 15 2014

መግቢያ በነፃ

ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ

የፕሮግራሙ መግቢያ ላይ የተለያዩ ጠቃሚ መፅሀፍት፣ ጣፋጭ ምግቦች መጠጦች በተመጣጣኝ ዋጋ ይቀርባሉ

ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
1.3K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 21:57:53
የሺዓና የአህሉሱና የዓሹራ ውሎ

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
ሙሀረም 12/ 1436 ዓ.ሒ ተፃፈ

የዓሹራ ቀን፤ የፊዓአውንን ትእቢትና አምባገነነንነት ያከተመበትና ለሌሎችም መቀጣጫ የሆነበት፣ ነብዩላህ ሙሳም የተደሰቱበት ለአህሉሱና ታላቅ ትርጉም ያለው የድል ብስራት ቀን ነው። አህሉሱና ይህንን ቀን በአል አያደርጉትም። የተለየ ድግስም ሆነ አለባበስ የላቸውም። ሆኖም መልእክተኛው ﷺ በደነገጉት መሰረት ይፆሙታል፣ መልካም ተግባራትን ይፈፅሙበታል፣ ከአላህ ልዩ ምንዳን በመከጀልም በዒባዳ ያሳልፉታል።

ሺዓዎች ግን ስለ ዓሹራ ቀን ሲያስቡ ሚታወሳቸው የታላቁ ሰሀቢይ የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ልጅ ሁሰይን የተገደሉበት ቀን መሆኑ ብቻ ነው። ሺዓዎች በዚህ ቀን ሀዘናቸውን ለመግለፅ እራሳቸውን የሚጎዱ ብዙ ነገሮችን በስፋት ይፈፅማሉ። ጭንቅላትንና ሌሎች አካሎቻቸውን በስለት መብጣትና ማድማት (ተጥቢር)፣ ፊታቸውን መደብደብ (ለጥም፣) እራስን በሰንሰለት መግረፍና ማንገላታት፣ በእንብርክክ መሄድ፣ ብዙዎችም ዘንድ ጥቁር መልበስና የለቅሶ ሙሾ ማውረድ ብሎም በራስ ላይ ኩነኔን መጥራት የተለመዱ የአሹራ ትእይንቶቻቸው ናቸው።

በእጅጉ ይገርማል፤
ለኛ ለአህሉሱና ደስታን ሲያላብሰን፣ ተስፋን አሰንቆ ድልን ሲያበስረን፤ ለወንጀላችን ማርታን ለማግኘት ሩጫ ውስጥ ሲከተን፤

ለሺአዎች ግና፤
የሀዘን የዋይታ፣ የውድቀት የሽንፈት ማስታወሻ፣ የተስፋ ማጨለሚያ ነው!!

ሁሰይን የነብዩ ﷺ የልጅ ልጅ በኢስላማዊ እውቀት ከመጠቁ ታላላቅ ሰሀቦች አንዱ ናቸው። በኢባዳ ብርቱ የተወዳጇ የመልእክተኛው ﷺ ልጅ የፋጢማ ረዲየላሁ አንሀ ልጅ ናቸው። ሆኖም...

ቀሪውን በዚህ ሊንክ ያንብቡ
http://clearfaith.blogspot.com/2015/10/blog-post.html?m=1

------
የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts
1.8K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 10:50:06
ነሲሓ የዒልም ቅፍለት ኮርስ

ከሰኞ ነሐሴ 02/2014 ዓ.ል ጀምሮ ለተከታታይ 4 ሳምንት የሚቆይ መሰረታዊ የዒልም ኮርስ

ዘወትር ከሰኞ- ሀሙስ ከጠዋት 02፡30- 6፡30

አየር ጤና በሚገኘው ዒባዱረህማን መስጂድ
የሚሰጡ ኮርሶች፡-

መንዙመቱል ሃኢያ(ዓቂዳ ) እና ተስሪፉል ዒዝይ(ሰርፍ)
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

ሙተሚመቱል አል‘ ኣጅሩሚያ (ነህው)
በሸይኽ ሙሐመድ ኢድሪስ


ነሲሓ ቲቪ...
ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም!!

@nesihatv
993 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 23:55:10 ወንድምህ ማለት …
ካለህ ላይ ትሰጠዋለህ እሱም ይሰጥሀል ለችግርህ ጊዜ ከጎንህ ይቆማል፣ አንተ ከሱ ኪስ ትወስዳለህ እሱም ካንተ ኪስ ይወስዳል ፣ ሁሌ መስማማት ላይኖር ይችላል፣ አዎ በአንዳንድ ጉዳዮች ላትስማማ ትችላለህ በአንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ ትስማማለህ አንተ ትወቅሰዋለህ እሱም ይወቅስሀል መጨረሻ ላይ ግን እርስ በርሳችሁ ትታረቃላችሁ ልባችሁ ላይ ቂምን አትቋጥሩም የቀኑ መጨረሻም ሌሊት ላይ አብራችሁ በሳቅ በጨዋታ ታሳልፋላችሁ።ይህ ነው ትክክለኛ ወንድማማችነት።አንተ ስትደሰት ይደሰታል፣ አንተ ተከፍተህ ማየት አይወድም አንተ ስትከፋ እሱም ይከፋዋል ፣ አንተ በሌለህበት ስትታማ ካንተ ይከላከልልሀል ፣ ነውርህን ይሸፍንልሃል ፣ ወደ መልካም ነገር እጅህን ስትዘረጋ እሱም ይዘረጋል፣ ክፍተትም ካለብህ ይሸፍንልሃል፣ እንጂ እንደሌላው ዳር ይዞ አንተን አያማም ፣ የሆነ ችግር ወይም አደጋ ቢደርስብህ ቀድሞ የሚደርስልህ ወንድምህ ነው!
የሆነን ነገር ከጠየቅከው ይሰጥሀል ፣ አኩርፈኸው ዝም ብትለው እሱ በሰላምታ ይጀምርሃል ያናግርሃል ፣ መልካም በሆኑ ነገራቶች ከራሱ አንተን ያስቀድማል ፣ ለችግርህ ቀድሞ ይደርሳል ፣ ከአይኑ ስትሰወር ይናፍቅሀል ይፈልግሀል፣ ስትዘነጋም ያነቃሃል።ጌታውን ሲለምን ዱዓዕ ሲያረግ አይረሳህም ፣ በዱዓው ያስታውስሃል።
ወንድም ማለት ራስ ላይ የሚደፋ አክሊል ፣ አንገት ላይ የሚደረግ ጌጥ ነው ፣ እርሱ ማለት ላንተ ውበት ነው። ወንድም በሆነ ችግር ወድቆ ብታገኘው ልታነሳው ይገባል ፣ ችግር ላይ ቢወድቅ እርዳው ደግፈው ፣ ቢደክም ቢልፈሰፈስ አንሳው አበርታው ።
ወንድም ማለት በችግር ጊዜ ደራሽ ነው ፣ አጋዥ ነው ፣ በችግር ጊዜ እንደ ጥላ ያገለግልሀል ፣ ልትወድቅ ስትል እንደ ምርኩዝ ያገለግልሃል።
ስለ ወንድምነት ካደረገው የጁምዓ ኹጥባ የተወሰደ
https://t.me/sultan_54
1.3K views20:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 20:22:47
ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

"ሲሕር (መንፈሳዊ ሕመሞች) መንስኤና መፍትሄ"
በሸይኽ አህመድ ሸይኽ ኣደም

እሁድ ጧት ከ3:00 ጀምሮ(1/12/2014)

፨ከተለያዩ ፕሮግራሞች ጋ!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
=====================

አድራሻ፦ ከአየር ጤና ቻይና ካምፕ ወደ ጀሞ3 በሚወስደው አቋራጭ አዋሽ ዳቦ ጋ!

{ራህማ መስጂድ}
1.6K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 12:41:32 ልዩ የዳዕዋ መድረክ ለእህቶች ብቻ!

በወርሀ ዙልሒጃ አንድ ብሎ የጀመረው ልዩ የዳዕዋ መድረካችን እንዳማረበት ሊቀጥል በቀጠሯቸን መሰረት እነሆ ቁጥር ሁለት ደረሰ።

ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ተሰናድተው እናንተን እየጠበቁ ነው።

በእለቱ የሚዳሰሱ ርዕሶች

ዐሹራ
እምነታችን
ሴቶችና ኢስላም

በተጨማሪም

መነባንቦች ይቀርባሉ

እሁድ ነሀሴ 1፣ 2014
ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

አድራሻ: ፒያሳ የሚገኘው ኸሊፋ ህንጻ አዳራሽ

በራስ ድግስ አይቀርም! አይረፈድም!

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

@darulhadis18
1.9K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 21:07:13
ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም

ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

ርዕስ፦ «ነባሩ እስልምና »

በሸይኽ አብዱስ'ሰላም አንዋር (ሐፊዘሁላህ)

የፊታችን እሁድ ሐምሌ-24-2014 አስር ሰላት እንደተጠናቀቀ

አድራሻ፦ ሎሚ ሜዳ ኹበይብ መስጂድ

ለበለጠ መረጃ፦ 0932982730/ 0923623124
t.me/khubeybmesjid
2.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:47:18 በሒጃብ ለምጽናት የሚረዱ መንገዶች!

ኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ

እህቶች ሊያደምጡት የሚገባ ወሳኝ ትምህርት!

@ustazsuleyman
1.9K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ