Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxtewadochannal — ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxtewadochannal — ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አገልግሎት
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxtewadochannal
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.02K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።

.
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቀ አስተምህሮ
✝መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ይቀሰቀስኛል
ለስሙ አንድዘምር🔔 የማንቂያ ደዉል🔔🔔
ክርስትና ዘር የለውም

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-10 10:58:14 ታህሳስ ፩ | ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኤልያስ

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በዚች በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ ኤልያስ የተገለጠበት ነው።

ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ ቶና ነው፤ ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ።

በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፎአል፤ ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል።

በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ ዮሐንስ ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል፤ ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ።

ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ፤ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል።

አርኬ
ሰላም ለከ ዐራጌ ሰማያት ለአዕርፎ። ሕይወተ ዓለም ምድራዊ በተናግፎ። በእንተ ምግባሩ ምንንት ለዓክአብ እንተ ትዘልፎ። እስመ ነሠትከ ምህራማተ ወቀጥቀጥከ ግልፎ። በስብሐቲከ ኤልያስ ተሰባሕከ እፎ።

ምስለ ኤልያስ ሰማየ ዘለጐመ። ከመ ኢያዝንም ዝናመ። በሠረገላ በርህ ንዒ ከመ ትባርኪ ዓለመ። ማርያም ጸጋዊት ለምእመናንኪ ሰላመ። እለ ክህላ ከናፍርኪ አፈ ነደ እሳት ስዒመ። ይረስያ ማኅሌተነ ኀቤሆን ጥዑመ። @ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal
154 viewsAbel, 07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 11:18:05 ​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ኃያል

ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

"ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:-
"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::
       <<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>>

አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

#ኅዳር_25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2. ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ)
3. ቅዱስ ሮማኖስ

ዝክረ ቅዱሳን
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
309 viewsAbel, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 10:57:10 #እኔ_በእግዚአብሔር_ፊት_የምቆመው_ገብርኤል_ነኝ (ሉቃ 1፥19)
#ይህ_ገብርኤል_ነው
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤ የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ዳንኤልን ከአነብስት ያዳነው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዘካሪያስ የተላከ የዮሐንስ ልደት ያበሰረ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ቂርቆስና ኤናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ሰብአ ሰገልነረ በኮከብ ምልክት የመራቸው
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
ድንግል ማርያሜና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
#ይህ_ገብርኤል_ነው ።
የብርሃን ወርቅ የተቀዳጀ
#ገብርኤል_ነወ ።
የአሸናፊና የኀኃይል መልአክ
#ገብርኤል_ነው ።
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
#ገብርኤል_ነው ።
#የመልአኩ_የቅዱስ_ገብርኤል_ጥበቃና_ረድኤት_አይለየን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን አሜን
      Join @ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal
413 viewsAbel, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 19:21:23 የእናታችን የኪዳነ ምህረት ታሪክ ባጭሩ
            

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

   ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት።
  አመሰግናለሁ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት
አርጓል፡፡
    'ኪዳን' የሚባለው ቃል «ቃል» ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ «ኪዳን» ቃሉ «ተካየደ» ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡
    «ምሕረት» የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ    የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡
    «ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ» ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደ ፊትም ያደርጋል፡፡ /መዝ. 88÷3/ ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡ በቅዱሳን አበውና በቅዱሳት እማት/እናቶች/ ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸዋል፤ የምሕረት ቃል ኪዳንም ይሰጣቸዋል፡፡
    የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን በቅዱሳኑ ሕይወት ዙሪያ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፡፡   ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡት አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ቃል ኪዳን የተገባላቸው ቅዱሳት መካናት ሞልተዉናል፡፡
   ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟማት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ /ዮሐ.21÷39፤ 2ኛ ጴጥ.1÷14/ ለቅዱስ ጳዉሎስ ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡ /የሐዋ.20÷25 ፣ 21÷10-13/ «ከሞቱ አስቀድሜ እገለጥለታለሁ» እንዲል፡፡ /ሰኔ ጎልጎታ/፡፡

      እግዚአብሔር ከሞታቸው አስቀድሞ በመገለጥ ለቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን የሚሰጣቸው በእነርሱ በጎ ሥራ ከእነርሱ በኋላ ያሉ የሰው ልጆችን ለመጥቀም ፈልጎ ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹ ራሳቸው ናቸው እንዳይባል ወደ ሞት አፋፍ የተጠጉ ከመሆናቸውም ባሻገር ለቃል ኪዳን የበቁት የሚጠቀሙበት በጎ ሥራ በመሥራታቸው ነው፡፡ የሰው ልጆች ያለፉ ቅዱሳንን በመዘከር የቃል ኪዳናቸው ተጠቃሚ ሲሆኑ ቅዱሳኑ ግን ከመታሰብ በቀር በሰው በኩል የሚጨመርላቸው የለም፡፡ ቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን ሲቀበሉ ለወገናቸው መትረፋቸውን እንረዳለን፡፡

     የምሕረት ቃል ኪዳን ለምን ያስፈልጋል ቢባል ሕግ መተላለፍ ካለ ሁልጊዜ ተጠያቂነት ወይም ቅጣት ይኖራል፡፡ ይህም በአዳም ይታወቃል፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ አኗኗር ይዘው አይገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅጣት እንዳያገኛቸው የሚድኑበትን በርካታ መንገዶች እግዚአብሔር አዘጋጀ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

    የምሕረት ቃል ኪዳን ሁሉ በጎ እንድንሠራ የሚያበረታታ ነው፡፡ ይህም ዘወትር ከቃል ኪዳኑ ጋር ተያይዘው በሚቀመጡ ግዴታዎች ይታወቃል፡፡ ለበጎ ሥራ ምክንያት የማይሆን ባዶ የምሕረት ቃል  ኪዳን የለም፡፡ «ስምሸን /ስምህን/ የጠራውን፣ ዝክር ያዘከረውን፣ የተራበ ያበላውን፣ የተጠማ ያጠጣውን፣ የታረዘ ያለበሰውን፣ እንግዳ በስምህ /በስምሽ/ የተቀበለውን፣ ገድልህን ያነበበውን፣ የሰማውን፣ የተረጎመውን ወዘተ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ፣ እምረዋለሁ» የሚሉ ቃል ኪዳናት በሙሉ ከባዱን መልካም ሥራ መፈጸም ባይቻለን እንኳን ቀላሉን መሥራት እንዳለብን ግዴታ የሚጥሉ ናቸው እንጂ አንዳንዶች እንደሚያስቡት መልካም እንዳንሠራ የሚያሳንፉ አይደሉም፡፡

   ከዚህ ይልቅ ለበጎ ሥራ የሚያነሣሡና የታዘዙትን መሥራት ያልተቻላቸውን ሰዎች ተስፋ ሳይቆርጡ እስከ መጨረሻው ሰዓት የሚድኑበት መንገድ እንዳለ አውቀው የተቻላቸውን እንዲያደርጉ የሚጠቁሙ ናቸው፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት ከአእምሮ በላይ ነው፡፡ ይህም ሰዎች በእግዚአብሔር ቸርነት ላይ በሚያነሡት ጥያቄ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ በየዜና ገድላቸው እንደምናነበው እግዚአብሔር ለብዙ ቅዱሳን «እስከ አሥር፣ ሠላሳ፣ ሃምሳ አምስት ወዘተ ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ» እያለ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በማንበብ እምነት የጎደላቸው አንዳንዶች «ይህ እንዴት ይሆናል ?» እያሉ ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ብቻ በራሱ የፈጣሪ ቸርነት ከሕሊና በላይ መሆኑን አያስረዳምን ?

    ፈጣሪ ስለ ፈራጅነቱና ስለ መሐሪነቱ ሲናገር «በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወዱኝ ትእዛዜን ለሚጠብቁ እስከ ሺሕ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፡፡» ይላል፡፡ /ዘጸ.20÷2-6/ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ የሚደርስ የእግዚአብሔርን ምሕረት መናገሩ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ ያለው የሠላሳና የሃምሳ ትውልድን ምሕረት የሚያወሳው ኃይለ ቃል ሊስተባበል አለመቻሉን ያሳያል፡፡ ያን   ማክፋፋት ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደመቃወም ይቆጠራል፡፡

   ዓለም ከተፈጠረች ሰባት ሺሕ አምስት መቶ ዓመት ገደማ ሊሆናት ነው፡፡ የሰው ልጅን አማካይ እድሜ እጅግ አሳንሰን በመቁጠር የአንድ ትውልድ ዘመን ሠላሳ ዓመት ነው ብንል እንኳን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያለው ትውልድ ከሁለት መቶ ሃምሳ አይበልጥም፡፡ ነገር ግን ፈጣሪ የሚወደውና ትእዛዙን የሚጠብቅ እውነተኛ ሰው ከተገኘ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያን ያህል ትውልድ እስከዓለም ፍፃሜ የሚኖር ከሆነም «እስከ ሺሕ ትውልድ» ድረስ እንኳን ይቅር ሊል ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔርን የቸርነት ስፋት ነው፡፡ ሺሕ ትውልድ ባይኖር እንኳን ሺሕ ትውልድ ስለሌለ እግዚአብሔር ሺሕ ትውልድ ሊምር አይችልም አይባልም፡፡ ስለዚህ የፈጣሪን ቃል ኪዳን ከመሐሪነቱ አንጻር እንጂ ከዓመታቱ መብዛት አንጻር ሊመለከቱት አይገባም፡፡
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
513 viewsAbel, edited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 06:11:33 ​​​​ #የቀጠለ

የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡

ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡

እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35)

እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡

እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡

#ምንጭ፦ የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መልአከ ሠላም ሰንበት ትምህርት ቤት ገጽ

@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
535 views03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 06:08:52 ​​#ሕዳር_ሚካኤል !

#እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን !

በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12)
(አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE_SHARE_SHARE
ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡)

ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡

በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት
አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡

ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም
የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡

ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡

#ይቀጥላል .......
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
425 views03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 11:19:50
`
                  ◦◊◦   ◦◊◦   ◦◊◦       
         በዓለ ደብረ ቁስቋም
                  ◦◊◦   ◦◊◦   ◦◊◦       

| ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ኹሉ እጅግ የደስታ ቀን ናትና ሐሤትን እናድርግ። የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና። ስደቷን አስበን ካዘንን፥ መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና። |

●◦●◦●
ይኽን በዓል ለኢትዮያውያን ልዩ የሚያደርገው፦

፩. በስደቷ መላው የኢትዮጵያ ምድር ስለተባረከች [ግማሹን በእግሯ እየሄደች፣ ግማሹን በደመና ተጭና እየበረረች ባርካታለችና]፤

፪. አሥራት ተደርጋ ከጌታችን ዘንድ ተሰጥታታለችና ፤

፫. ትውፊት እንደሚያስረዳን፥ የእመቤታችን እና የጌታ መድኃኔዓለም ስደት ማብቃቱን፣ ሔሮድስ መሞቱን የነገራት መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ኾነው ነውና።

● እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል፤ ሐሴትንም አድርገዋል።

◍◦◍◦◍
እመቤታችን ስደት ማብቃቱን በቅዱስ ገብርኤል ምሥራች የሰማችባትን የአሥራት ሀገሯ ኢትዮጵያን፦ "ለቅሶሽ፣ መከራሽ፣ ስደትሽ ይብቃ" ትበላት።

ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግሥተ ሰማያት ስደት ይሰውረን። ከስደቱ በረከትም ያድለን።
◍◦◍◦◍
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
501 viewsedited  08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 16:38:24 ❖ የመጨረሻው ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ  ❖

እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን የዓመት ሰው ትበለን!!!

የ ፳፻፲፭ ዓ.ም የአምስተኛው ዓመት የኅዳር ፬ የስድስተኛውና የመጨረሻው ሰንበት የጽጌ ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

፩. ነግሥ

ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤
ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤
መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤
ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤
እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።

ዚቅ፦

ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም ፨ በዝ መካን መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ፨ ከመ ጽጌ ደንጐላት ዘቊላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት ፨ (ለአዘአክብሮ ለቂርቆስ) ለዘቀደሳ ለሰንበት  ኪያሁ ፍርህዎ ወሰብሕዎ ወተማኅፀኑ ኀቤሁ።

፪. ኢየኃፍር ቀዊመ / ማኅሌተ ጽጌ /

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤
ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤
ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤
ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፡
ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡

ወረብ ፦

ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ፤
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ።

ዚቅ፦

እለትነብሩ ተንሥኡ ፨ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ ፨ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ ፨ ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ ፨ ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፨ መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡

፫. እንዘ ተሐቅፊዮ /ማኅሌተ ጽጌ/

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡፡

ወረብ ፦

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል።

ዚቅ፦

ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ፨ እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ ፨ መላእክት ይትለአኩኪ ፨ ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት።

፬. ሶበ ዴገነኪ አርዌ / ማኅሌተ ጽጌ /

ሶበ ዴገነኪ አርዌ በሊዓ ሕፃንኪ ዘኀለየ፤
በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጐይየ፤
አመ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤
ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤
ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ፡፡

ወረብ፦

ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤
ተአምረኪ ፀሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ ዘርእየ ተአምረኪ።

ዚቅ፦
በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ ፨ ዘምስለ ዮሴፍ አረጋይ ፨ ነገደት ቍስቋመ ናዛዚተ ኃዘን ወብካይ፡፡

፭. ክበበ ጌራ ወርቅ / ማኅሌተ ጽጌ /

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ፦

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየሐቱ እምዕንቈ ባሕርይ /፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ /፪/

ዚቅ፦

ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ፨ ወስብሕት በሐዋርያት ፨ አክሊለ በረከቱ ለጊዮርጊስ ፨ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል ።

፮. ኅብረ ሐመልሚል / ማኅሌተ ጽጌ /

ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ፤
አርአያ ኮሰኮስ ዘብሩር፤
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር ።

ወረብ ፦

ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ፤
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት።

ዚቅ፦

ሃሌ ሃሌ ሉያ ፨ ሃሌ ሉያ፨ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ፨ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ወርቅ፡፡

፯. ተመየጢ / ሰቆቃወ ድንግል /

ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤
ወኢትጎንድዪ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤
በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤
ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤
በከመ ፤ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ።

ወረብ፦

ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ፤
ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ።

ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ፨ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ፨ ወንርዓይ ብኪ ሰላመ ፨ ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ
ሰጣዊት ፨ እንተ ትሔውፅ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር ፨ ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ።

°༺༒༻° መዝሙር ዘሰንበት °༺༒༻°

ሃሌ በ፮ ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ ክርስቶስ ሰንበተ ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ ፨ አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረዩ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ አሐዱ እምእሉ።

°༺༒༻°   አመላለስ ዘመዝሙር °༺༒༻°

ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤
  ከመ አሐዱ እምእሉ።

°༺༒༻° የ ፳፻፲፭ ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ  °༺༒༻°

                ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                  ወለወላዲቱ ድንግል
                  ወለመስቀሉ ክቡር !!!
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal @ortodoxtewadochannal
508 views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 15:30:09 ​​እንኳን #አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!

አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል።

አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ።

አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ

ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው።

በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር።

በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል።

ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል።

ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል።

ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል።

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ።

#ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14 
ለወዳጅዎ ያጋሩ
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
747 viewsedited  12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 14:39:18 «ግሸን ደብረ ከርቤ»

ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊት ጎልጎታ ከደሴ ከተማ 82 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ ውስጥ በሃይቅ እና በመቅደላ በደላንታና በየጁ መካከል በበሽሎ ወንዝ አዋሳኝ ከፍተኛ በሆነ ተራራ ላይ የምትገኝ ገዳም ናት፡፡ የበሸሎን ወንዝ ተሻግረን ሰማይ ጥግ የደረሱ የሚመስሉትን ተራሮች ወጥተን በስተመጨረሻ መግቢያ አንድ በር የሆነ እና ከተራራው አናት ላይ በሚገኝ ስፋራ ላይ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸ እና ግማደ መስቀሉ የሚገኝበት የእግዚአብሔር አብ አብያተ ክርስቲያናት እና ፈዋሽ ጸበል ይገኛሉ፡፡ በ1942 ዓ.ም አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር ከዚህም ጋር ''መንፈሳዊ መናኝ'' በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ያሰሩት ቤተ ክርስቲያንም ይገኛል፡፡

ግሸን ይህን የአሁኑን መጠሪያ ስም ከማግኘትዋ በፊት በተለያየ መጠሪያ ስሞች ትታወቅ ነበር:: በመጀመሪያ በአጼ ድልነአድ ዘመነ መንግስት በ896 ዓ.ም ሃይቅ ደብረ እስጢፋኖስ ሲመሰረት ''ሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ'' ተብሎ ሲሰየም ግሸንም በሃይቅ ግዛት ውስጥ ስለሆነች ስምዋ ''ደበረ - ነጎድጓድ'' ተባለች፡፡ ይህን መጠሪያ ስም እንደያዘች እስከ 11ኛው ክ/ዘመን ድረስ ቆየች፡፡ በ11ኛው ክ/ዘ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ጻድቁ ንጉስ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍሎ የሰራው ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር አብ ስም ይጠራ ስለነበር ግሸንም ''ደብረ እግዚአብሔር'' ተብላ መጠራት ጀመረች፡፡ ነገር ግን በዚህ ስም በመጠራት ብዙም ሳይቆይ ስሟ ተለውጦ ''ደብረ ነገሥት'' ተባለች፡፡ ደብረ ነገስት የተባለችውም ነገስታቱ ይማጸኑባት የክብርና የማእረግ እቃዎች የሚያሰቀምጡባትና የነገስታቱ የመሳፍንቱ ልጆችም የቤተ መንግስት አስተዳደር የሚማሩባት ስፍራ ስለነበረች ነው፡፡ እንደገና ደግሞ በ1446 ዓ.ም ኢትዪጵያዊው ፈላስፋ እየተባሉ በሚጠሩት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ግማደ መስቀሉ መጥቶ በዚህ ቅዱስ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ- ነገሥት መባልዋ ቀርቶ ''ደብረ- ከርቤ'' ተባለች፡፡
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
742 views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ