Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ ሰላም ዶክተር በኦፕሬሽን 3 ጊዜ ወልጃለሁ አራተኛ አርግዣለሁ አራተኛ ኦፕሬሽን ስሰራ ለ | TenaSeb - ጤና ሠብ

ጥያቄ
ሰላም ዶክተር በኦፕሬሽን 3 ጊዜ ወልጃለሁ አራተኛ አርግዣለሁ አራተኛ ኦፕሬሽን ስሰራ ለጤናየ ምን ጉዳት ያመጣል በቀዶ ጥገናስ ስንቴ መውለድ ይቻላል ከጤና ጋር ያለውን አደጋ ቢያማክሩኝ ።

መልስ
ይህ ነው የሚባል የተወሰነ የቀዶ ጥገና (c/s) ጠረፍ የለውም። ችግሩ የቀዶ ጥገና(CS) እየጨመረ ሲሄድ ማህፀንና አካባቢው እና ኦፕሬሽን ቦታው መጠባበቅ መኖር ይመጣል። ይህም ኦፕሬሽኑን ከባድ እና ደም መፍሰስ ሊከሰት ይችላል።

ጥያቄ
አንዲት በኦፕሬሽን የወለደች እናት ከስንት አመትበኋላ ነዉ ማርገዝ ያለባት?ከዛስ በምጥ መዉለድ ትችላለች?

መልስ
በትንሹ 1 አመት ከ 6 ወር መቆየት ይኖርባታል።
እናቲቱ በማህፀን ለመውለድ ማሟላት ያለባት ነገሮች አሉ።

- በፊት አንድ አኦፕሬሽን ብቻ ካላት
- ኪሎ ከ 4 በታች ከሆነ
- የበፊቱ አኦፕሬሽን የተሰራላት ምክንያት አሁንም ምክንያት ካልሆነ
- በፊት የተሰራው በማህፀን ጥበት ወይም ማህፀን መቀደድ ምክንያት ላልሆነ
- በፊት የተሰራው አኦፕሬሽን አይነት

የመሳሰሉት ታይተው በማህፀን መውለድ መቻል አለመቻል ይወሰናል።

ዶ/ር ዳዊት (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)- https://t.me/DrDawitMOBGYN
***

TenaSeb - ጤና ሠብ
Youtube -http://shorturl.at/kDEP5
Telegram- https://t.me/tenaseb
TikTok - www.tiktok.com/@tenaseb
Telegram group - https://t.me/tenasebeth