Get Mystery Box with random crypto!

' ዘንድሮ በመደበኛው 667 ሺህ 483 ፤ በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈ | Medical Information- ጤና መረጃ®️🇪🇹

" ዘንድሮ በመደበኛው 667 ሺህ 483 ፤ በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ከ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት የተስተዋሉ የተለያዩ እንከኖች በዚህኛው ዓመት መስተካከላቸውን የትምሕርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ምዝገባው በማንዋል በመሆኑ ተፈጥሮ የነበረውን የተፈታኞች መረጃ አያያዝ ጥራት ጉድለት ለማረም ዘንድሮ ምዝገባው በበይነ መረብ መካሄዱን አገልግሎቱ ገልጿል።

በተጨማሪም ከዩኒቨርሲቲ ድልድል፣ ዝግጅት እና አቀባበል ጋር በተያያዘ እክሎች የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ችግሩ መቀረፉን አረጋግጧል።

አምና ካጋጠመው ጉድለት በመማር የፈተና ማስፈጸሚያ ማንዋል እና መመሪያውን በማዘጋጀት እና በመከለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል።

ባለፈው ፈተና ወቅት ተፈታኞችን ማዘጋጀት አለመቻሉ ዋና ችግር እንደነበር የጠቀሰው አገልግሎቱ በዚህ ዓመት በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ ገልጿል።

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 869 ሺህ 802 ትክክለኛውን የምዝገባ ሂደት ያላሟሉ 1 ሺህ 213 ተፈታኞች ምዝገባ መሠረዙንም ተገልጿል።

ዘንድሮ ፦

- በመደበኛ 667 ሺህ 483
- በግል፣ በማታ እና በርቀት 200 ሺህ 691 ተፈታኞች ፈተና ይወስዳሉ።

ፈተናው በሁለት ዙር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሳጣል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን፤ ሁለተኛው ዙር ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 25 እስከ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ አገልግሎቱ አረጋግጧል።

የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 16 እስከ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እ
የሚገቡ ሲሆን ሐምሌ 18 ገለጻ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች ደግሞ ከሐምሌ 22 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ገብተው ሐምሌ 24 ቀን ገለጻ ይሰጣቸዋል።

ተፈታኞች ፈተናውን በራሳቸው ጥረት እንዲሠሩ አሳስበው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባለፈው ዓመት የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 17 ሺህ ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን አስታውሷል።

Credit : #ኤፍቢሲ

ፌስቡክ ገጻችን፡ facebook.com/tenamereja
Group፡ @medical_Ethiopia

ለመልዕክት፣ ጥያቄ፣ ማስታወቂያ፣ ጥቆማ፣ መረጃ፦ @medicaladds

@medicaladds
@medicaladds