Get Mystery Box with random crypto!

#Update የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን የፈ | ትምህርት በቤቴ🔝

#Update

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

ይኸው የፈተና መርሀ ግብር ዛሬ ከሰዓት በኃላም ይቀጥላል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና መርሀግብር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ነገ ጥቅምት 2 / 2015 የሚጠናቀቅ ሲሆን ተማሪዎች ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 4 ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

በሌላ በኩል ፤ ትላንት የድልድይ መደርመስ አደጋ ደርሶ የአንድ ተማሪ ህይወት በጠፋበት እና በርካታ ተማሪዎች በተጎዱበት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

የደቡብ ክልል ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሀዋሳ ዋናው ግቢ ብሄራዊ ፈተና እየተሰጠ መሆኑን ገልጾ ሁሉም በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ ነው ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የፈተናውን ሂደት እየተመለከቱ መሆኑ ተነግሯል።

ትላንት ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችና ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ሌላ ዕድል ከት/ት ሚኒስቴርና የፈተናዎች ድርጅት ጋር በመነጋገር እንደሚመቻችላቸው የሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ማሳወቁ አይዘነጋም።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete