Get Mystery Box with random crypto!

#HawassaUniversity ዛሬ ጠዋት መስከረም 30/2015 ዓም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ | ትምህርት በቤቴ🔝

#HawassaUniversity

ዛሬ ጠዋት መስከረም 30/2015 ዓም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ሁለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿጻ።

" ሁኔታቸዉን መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረሀይል በቅርበት እየተከታተለ " ነው ያለው ትምህርት ሚኒስቴር " ወላጆች እንዳይደናገጡ እንጠይቃለን " ብሏል።

ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ አሳስቧል።

ሁኔታዉን በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅም ገልጿል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete