Get Mystery Box with random crypto!

ለፈተና ሄደው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለወለዱ ተፈታኞች በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣ | ትምህርት በቤቴ🔝

ለፈተና ሄደው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለወለዱ ተፈታኞች በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣቸዋል ተባለ

በእርግዝና ላይ ላሉ እና ወልደው ህጻንን ጡት እየመገቡ ላሉ ለተመዘገቡ ሴት የ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች የእነርሱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የመፈተኛ ስርዓት በቀጣይ ተዘጋጅቷል ሲል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል፡፡

በዚህም መሰረት አገልግሎቱ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሚሰጠው ፈተና ተፈጣኝ ወላዶች መፈተን አያስፈልጋቸውም ማለቱን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም ከወራት በፊት ከወረዳ ደረጃ አንስቶ ገለጻ ተሰጥቷል፤መመሪያም ሆኖ ወርዷል ብሏል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፡፡

ሆኖም ለመፈተን ወደዩኒቨርሲቲ ከመጡ ተፈታኞች መካከል ወደ ተቋማቱ እንደደረሱ የወለዱ እንዳሉ ሪፖርት ደርሶናል ያለ ሲሆን ስለሆነም እነዚህ ወላድ ተፈታኞች የቤተሰብ እንክብካቤና ፈተናውን ለመፈተንም አካላዊ ማገገሚያ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው እሙን ነው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ እንደመደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ አገልግሎቱ ዕድል የሰጣቸው መሆኑ ታውቆ ቀድሞ በተላለፈው መመሪያ መሠረት በመጀመሪያው ዙር መፈተን የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ሲል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete