Get Mystery Box with random crypto!

የ85 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ አቶ ባፋ ባጋጃ ይባላሉ። የ85 ዓመት አዛውንት ናቸው። በወላይ | ትምህርት በቤቴ🔝

የ85 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

አቶ ባፋ ባጋጃ ይባላሉ። የ85 ዓመት አዛውንት ናቸው። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሚወስዱ ተፈታኞች መካከል አንዱ ናቸው።

የስምንት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ባፋ፤ በ1949 ዓ.ም የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይገልጻሉ።

የ85 ዓመቱ አዛውንት በ2009 ዓ.ም ከ66 ዓመት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በድጋሚ በመጀመር በባይራ ኮይሻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

"እውቀት መቅሰም በእድሜ አይገደብም" የሚሉት አቶ ባፋ፤ ዓላማቸው ተምረው ለአገር ውለታ መስራት መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሀድያ እና ከወላይታ ዞኖች የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በመቀበል ላይ ነው።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete