Get Mystery Box with random crypto!

በ2014 ዓ.ም የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው እርምት እንዲያደርጉ ውሳኔ ተላልፎባቸው ተግባራዊ ያላደረጉ | ትምህርት በቤቴ🔝

በ2014 ዓ.ም የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው እርምት እንዲያደርጉ ውሳኔ ተላልፎባቸው ተግባራዊ ያላደረጉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በወንጀልና በፍትሐ ብሔር ተጠያቂ ሊደረጉ ነው፡፡ 

የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ነው ተቋማቱን ተጠያቂ የሚያደርገው።

ባለሥልጣኑ በ2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ የሥነ ሥርዓት መመርያ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የማስተካከያ ዕርምጃ እና ማጋለጥ ሲያደረግ ቆይቷል።

ውሳኔውን ተግባራዊ ያላደረጉ ተቋማትን በወንጀል እና በፍትሐ ብሔር ተጠያቂ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የባለሥልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ታረቀኝ ገረሱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ የመመርያ ጥሰቶች በፈጸሙ 373 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶች ላይ ባለሥልጣኑ በ2014 ዓ.ም ዕርምጃ መውሰዱን ኃላፊው አስታውሰዋል።

ተማሪዎችን እንዲበትኑ፣ ካምፓሶቻቸውን እንዲዘጉ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ተቋማቸውን እንዲዘጉ ትዕዛዝ የተላለፈባቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተላለፈባቸው ውሳኔ ተገዥ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ክትትል ማድረግ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete