Get Mystery Box with random crypto!

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችንን | telebirr

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችንን በማስከተል ምዝገባ በተጀመረባቸው ማዕከላት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተገኝተው አተገባበሩን ተመልክተዋል።

በዚህም ወቅት ለምዝገባው አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸው እና የምዝገባ አገልግሎቱ በላቀ ፍጥነት መስጠት መቻሉን በተግባር መመልከት ችለዋል፡፡

አገልግሎቱ በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት የሚስፋፋ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ተገልጋዮች ስለዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ እንዲረዱ የማድረግ ሥራ በስፋት እንደሚከናወን ተነግሯል።

ዜጎች በአቅራቢያቸው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንበትን የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከል ለማወቅ ቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ውስጥ የተካተተውን አዲስ የአቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ ዳታ በማብራት ብቻ በነጻ መጠቀም ይችላሉ።

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #NIDP