Get Mystery Box with random crypto!

ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች | telebirr

ኩባንያችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በይፋ አስጀመረ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያን ለማዳረስ የታቀደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ኩባንያችን በወር በአማካይ 1 ሚሊዮን ዜጎችን በመመዝገብ ለ32 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የሀገራዊ ዕቅዱን 36% ለማከናወን የአገልግሎት ማዕከላትን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን ስራውን ያስጀመረ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ከተሞች አገልግሎቱን ይቀጥላል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ የዲጂታል መታወቂያ አንዱ ሲሆን ለአካታች የዲጂታል ማህበራዊና ኢኮኖሚ ግንባታ፣ ለቢዝነስ ትስስር፣ ለኢ-ጋቨርመንት፣ በዳታ ለሚመራ የኢኮኖሚ ሥርአት፣ ለቀልጣፋ አገልግሎት፣ ለተሻለ የዜጎች ህይወት እንዲሁም የሳይበር ማጭበርበርን ለመከላከል ካለው የላቀ ሀገራዊ ሚና በተጨማሪ ለላቀ የደንበኞች ተሞክሮ፣ ለሥራ ፈጠራ፣ ለኢ-ኮሜርስ፣ የፋይናንስ አካታችነት የሚጨምሩ የማይክሮ ብድር አገልግሎቶች ለማቅረብ፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን የዲጂታል መታወቂያ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገልግሎት ማዕከላት፣ የፍራንቻይዝ ማዕከላት፣ ወኪሎች እንዲሁም የገነባውን ግዙፍ የዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ሰርቪስና የዲጂታል መሰረተ ልማት አስቻይ ሁኔታ እንደሚፈጥሩለት ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ምዝገባ የሚደረግባቸውን ማዕከላት ለመመልከት ቴሌብር ሱፐርአፕን http://onelink.to/fpgu4m ወይም ድረ-ገጻችንን www.ethiotelecom.et ይጎብኙ
ለተጨማሪ https://bit.ly/3QfPuVg