Get Mystery Box with random crypto!

ኩባንያችን በመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2 | telebirr

ኩባንያችን በመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጉዞን ለመቃኘት በተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ ከታዳሚዎቹ በዲጂታል መንገድ ግብዓት የሚሰበሰብበት የዲጂታል ፖርታል ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል።

ፖርታሉ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ለማፋጠን በቀጣይ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው አስፈላጊ እርምጃዎች ዜጎች በቀላሉ ካሉበት ሆነው አስተያየት ለመስጠት እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን እርስዎም ማስፈንጠሪያውን https://bit.ly/49eSBn1 በመጠቀም ወይም QR Code ስካን በማድረግ ግብዓትዎን እንዲሰጡን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ጉባኤ ላይ በመገኘት ገንቢ አስተያየታችሁን ለሰጣችሁን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የግሉ ዘርፍ አጋሮች፣ ወጣት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እና መላው ታዳሚዎች ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica