Get Mystery Box with random crypto!

በትላንትናው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉ | telebirr

በትላንትናው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ክቡር አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ እና በትምህርት ሚኒስቴር የአይ.ሲ.ቲ እና ዲጂታል ትምህርት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ የፓነል ውይይት አካሂደዋል፡፡

በፓነሉ የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኙ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኩባንያችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንደ ቴሌኮም፣ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ዳታ ሴንተር፣ ክላውድ ያሉ ዲጂታል መሰረተ ልማቶች እንዲሁም እንደ ዲጂታል መታወቂያ፣ ዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ያሉ አስቻይ ሲስተሞች የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን ዕውን ለማድረግ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

“ዲጂታል ኢትዮጵያን መገንባት ጉዞ ነው” በማለት የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚያችን "በየምዕራፉ የምናሳካቸው ፍሬዎች አሉ" በማለት በኃይል አቅርቦት እና በቴሌኮም ተደራሽነት ዙሪያ የተሰሩት የማስፋፊያ ስራዎችን አብራርተው በንፅፅር የታዩ እድገቶች አበረታች መሆናቸውን በመግለጽ መሰረተ ልማቶች ላይ የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን መቀጠል እና አካታች ማድረግ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡


#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica